Ibisobanuro bya qoran ntagatifu - Ibisobanuro bya Qur'an Ntagatifu mu rurimi rw'iki Amharike - Akademiya y'Afurika.

numero y'urupapuro:close

external-link copy
79 : 12

قَالَ مَعَاذَ ٱللَّهِ أَن نَّأۡخُذَ إِلَّا مَن وَجَدۡنَا مَتَٰعَنَا عِندَهُۥٓ إِنَّآ إِذٗا لَّظَٰلِمُونَ

79. «ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ያገኘንበትን ሰው እንጂ ሌላን ከመያዝ በአላህ እንጠበቃለን:: እኛ ያን ባደረግን ጊዜ በእርግጥ በዳዮች ነን።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
80 : 12

فَلَمَّا ٱسۡتَيۡـَٔسُواْ مِنۡهُ خَلَصُواْ نَجِيّٗاۖ قَالَ كَبِيرُهُمۡ أَلَمۡ تَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ أَبَاكُمۡ قَدۡ أَخَذَ عَلَيۡكُم مَّوۡثِقٗا مِّنَ ٱللَّهِ وَمِن قَبۡلُ مَا فَرَّطتُمۡ فِي يُوسُفَۖ فَلَنۡ أَبۡرَحَ ٱلۡأَرۡضَ حَتَّىٰ يَأۡذَنَ لِيٓ أَبِيٓ أَوۡ يَحۡكُمَ ٱللَّهُ لِيۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡحَٰكِمِينَ

80. ከእርሱም ተስፋን በቆረጡ ጊዜ የሚመካከሩ ሆነው ገለል አሉ:: ታላቃቸውም አለ: «አባታችሁ በእናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መተማመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑንና ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለእኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለእኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የምስርን (የግብጽን) ምድር አልለይም:: እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
81 : 12

ٱرۡجِعُوٓاْ إِلَىٰٓ أَبِيكُمۡ فَقُولُواْ يَٰٓأَبَانَآ إِنَّ ٱبۡنَكَ سَرَقَ وَمَا شَهِدۡنَآ إِلَّا بِمَا عَلِمۡنَا وَمَا كُنَّا لِلۡغَيۡبِ حَٰفِظِينَ

81. «ወደ አባታችሁ ተመለሱ:: በሉትም: ‹አባታችን ሆይ ልጅህ ሰረቀ፤ ባወቅነዉም ነገር እንጂ አልመሰከርንም:: ሩቁንም ነገር ምስጢሩን አዋቂዎች አልነበርንም። info
التفاسير:

external-link copy
82 : 12

وَسۡـَٔلِ ٱلۡقَرۡيَةَ ٱلَّتِي كُنَّا فِيهَا وَٱلۡعِيرَ ٱلَّتِيٓ أَقۡبَلۡنَا فِيهَاۖ وَإِنَّا لَصَٰدِقُونَ

82. «‹ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን።›» info
التفاسير:

external-link copy
83 : 12

قَالَ بَلۡ سَوَّلَتۡ لَكُمۡ أَنفُسُكُمۡ أَمۡرٗاۖ فَصَبۡرٞ جَمِيلٌۖ عَسَى ٱللَّهُ أَن يَأۡتِيَنِي بِهِمۡ جَمِيعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡحَكِيمُ

83. ያዕቁብም፡- «አይደለም። ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለእናንተ ሸለሙላቸሁና ሠራችሁት እንጂ:: እናም መልካም ትዕግስት ማድረግ አለብኝ:: እነርሱን ሁሉንም የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል:: እነሆ እርሱ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።» አላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
84 : 12

وَتَوَلَّىٰ عَنۡهُمۡ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبۡيَضَّتۡ عَيۡنَاهُ مِنَ ٱلۡحُزۡنِ فَهُوَ كَظِيمٞ

84. ከነርሱም ዞር አለና፡- «በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ:: ዓይኖቹም ከሐዘን የተነሳ ነጡ:: እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
85 : 12

قَالُواْ تَٱللَّهِ تَفۡتَؤُاْ تَذۡكُرُ يُوسُفَ حَتَّىٰ تَكُونَ حَرَضًا أَوۡ تَكُونَ مِنَ ٱلۡهَٰلِكِينَ

85. እነርሱም፡- «በአላህ እንምላለን! ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ ዩሱፍን ከማውሳት አትወገድም።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
86 : 12

قَالَ إِنَّمَآ أَشۡكُواْ بَثِّي وَحُزۡنِيٓ إِلَى ٱللَّهِ وَأَعۡلَمُ مِنَ ٱللَّهِ مَا لَا تَعۡلَمُونَ

86. «ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው። ከአላህ በኩል የማታውቁትን ነገር እኔ አውቃለሁና።» አላቸው። info
التفاسير: