Ibisobanuro bya qoran ntagatifu - Ibisobanuro bya Qur'an Ntagatifu mu rurimi rw'iki Amharike - Muhammad Sadeq.

numero y'urupapuro:close

external-link copy
12 : 35

وَمَا يَسۡتَوِي ٱلۡبَحۡرَانِ هَٰذَا عَذۡبٞ فُرَاتٞ سَآئِغٞ شَرَابُهُۥ وَهَٰذَا مِلۡحٌ أُجَاجٞۖ وَمِن كُلّٖ تَأۡكُلُونَ لَحۡمٗا طَرِيّٗا وَتَسۡتَخۡرِجُونَ حِلۡيَةٗ تَلۡبَسُونَهَاۖ وَتَرَى ٱلۡفُلۡكَ فِيهِ مَوَاخِرَ لِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

ሁለቱ ባሕሮችም አይተካከሉም! ይህ ጣፋጭ፣ ጥምን ቆራጭ፣ መጠጡ በገር ተዋጭ ነው፡፡ ይህኛውም ጨው መርጋጋ ነው፡፡ እርጥብ ስጋንም ከሁሉም ትበላላችሁ፡፡ (ከጨው ባሕር) የምትለብሷትንም ጌጥ ታወጣላችሁ፡፡ ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም መርከቦችን በእርሱ ውስጥ ውሃውን ቀዳጆች ኾነው (ሲንሻለሉ) ታያለህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 35

يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ يَجۡرِي لِأَجَلٖ مُّسَمّٗىۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ لَهُ ٱلۡمُلۡكُۚ وَٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا يَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِيرٍ

ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል፡፡ ቀንንም በሌሊት ውሰጥ ያስገባል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፡፡ ሁሉም እተወሰነ ጊዜ ድረስ ይሮጣሉ፡፡ ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳ አይኖራቸውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 35

إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا يَسۡمَعُواْ دُعَآءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُواْ مَا ٱسۡتَجَابُواْ لَكُمۡۖ وَيَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِيرٖ

ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 35

۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ أَنتُمُ ٱلۡفُقَرَآءُ إِلَى ٱللَّهِۖ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلۡغَنِيُّ ٱلۡحَمِيدُ

እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁል ጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 35

إِن يَشَأۡ يُذۡهِبۡكُمۡ وَيَأۡتِ بِخَلۡقٖ جَدِيدٖ

ቢሻ ያስወግዳችኋል፡፡ አዲስንም ፍጡር ያመጣል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 35

وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ بِعَزِيزٖ

ይህም በአላህ ላይ ምንም አስቸጋሪ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 35

وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۚ وَإِن تَدۡعُ مُثۡقَلَةٌ إِلَىٰ حِمۡلِهَا لَا يُحۡمَلۡ مِنۡهُ شَيۡءٞ وَلَوۡ كَانَ ذَا قُرۡبَىٰٓۗ إِنَّمَا تُنذِرُ ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُم بِٱلۡغَيۡبِ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَۚ وَمَن تَزَكَّىٰ فَإِنَّمَا يَتَزَكَّىٰ لِنَفۡسِهِۦۚ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلۡمَصِيرُ

ኀጢአትን ተሸካሚም (ነፍስ) የሌላዋን ሸክም አትሸከምም፡፡ የተከበደችም (ነፍስ) ወደ ሸክሟ ብትጣራ (ተጠሪው) የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢኾንም እንኳ ከእርሷ አንዳችን የሚሸከምላት አታገኝም፡፡ የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን በሩቅ የሚፈሩትን፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱትን ብቻ ነው፡፡ የተጥራራም ሰው የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ info
التفاسير: