Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África

አዝ ዙመር

external-link copy
1 : 39

تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ

1. የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 39

إِنَّآ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ بِٱلۡحَقِّ فَٱعۡبُدِ ٱللَّهَ مُخۡلِصٗا لَّهُ ٱلدِّينَ

2. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት የተሞላ ሲሆን አወረድነው:: አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ሆነህ ተገዛው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 39

أَلَا لِلَّهِ ٱلدِّينُ ٱلۡخَالِصُۚ وَٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِهِۦٓ أَوۡلِيَآءَ مَا نَعۡبُدُهُمۡ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَآ إِلَى ٱللَّهِ زُلۡفَىٰٓ إِنَّ ٱللَّهَ يَحۡكُمُ بَيۡنَهُمۡ فِي مَا هُمۡ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ كَٰذِبٞ كَفَّارٞ

3. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ ፍጹም ጥሩ የሆነው ሃይማኖት ለአላህ ብቻ ነው:: እነዚያ ከእርሱ ሌላ ጣዖታትን ረዳቶች አድረገው የያዙት ሁሉ «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቃርቡን በማሰብ እንጂ ለሌላ አንገዛቸዉም።» ይላሉ:: አላህ በዚያ እነርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል:: አላህም ውሸታምንና ከሓዲ የሆነን ሰው አያቀናም:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 39

لَّوۡ أَرَادَ ٱللَّهُ أَن يَتَّخِذَ وَلَدٗا لَّٱصۡطَفَىٰ مِمَّا يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُۚ سُبۡحَٰنَهُۥۖ هُوَ ٱللَّهُ ٱلۡوَٰحِدُ ٱلۡقَهَّارُ

4. አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር:: ጥራት ተገባው:: እርሱ አሸናፊውና ብቸኛው አንዱ አላህ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 39

خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۖ يُكَوِّرُ ٱلَّيۡلَ عَلَى ٱلنَّهَارِ وَيُكَوِّرُ ٱلنَّهَارَ عَلَى ٱلَّيۡلِۖ وَسَخَّرَ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَۖ كُلّٞ يَجۡرِي لِأَجَلٖ مُّسَمًّىۗ أَلَا هُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡغَفَّٰرُ

5. አላህ ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ሌሊቱንም በቀን ላይ ይጠቀልላል:: ቀኑንም በሌሊት ላይ እንዲሁ ይጠቀልላል:: ጸሐይንና ጨረቃንም ገራ:: ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እርሱ አሸናፊዉና መሀሪው ነውና:: info
التفاسير: