Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África

Número de página:close

external-link copy
31 : 33

۞ وَمَن يَقۡنُتۡ مِنكُنَّ لِلَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتَعۡمَلۡ صَٰلِحٗا نُّؤۡتِهَآ أَجۡرَهَا مَرَّتَيۡنِ وَأَعۡتَدۡنَا لَهَا رِزۡقٗا كَرِيمٗا

31. ከናንተም መካከል ለአላህና ለመልዕክተኛው የምትታዘዝ መልካም ስራንም የምትሰራ ሴት ምንዳዋን ሁለት ጊዜ እንሰጣታለን:: ለእርሷም የከበረን ሲሳይ አዘጋጅተንላታል። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 33

يَٰنِسَآءَ ٱلنَّبِيِّ لَسۡتُنَّ كَأَحَدٖ مِّنَ ٱلنِّسَآءِ إِنِ ٱتَّقَيۡتُنَّۚ فَلَا تَخۡضَعۡنَ بِٱلۡقَوۡلِ فَيَطۡمَعَ ٱلَّذِي فِي قَلۡبِهِۦ مَرَضٞ وَقُلۡنَ قَوۡلٗا مَّعۡرُوفٗا

32. እናንተ የነቢዩ ሚስቶች ሆይ! እንደ ማናቸዉም ሴቶች አይደላችሁም:: አላህን ብትፈሩ ትበልጣላችሁ። በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር እንኳን አትለስልሱም:: መልካምንም ንግግር ተናገሩ። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 33

وَقَرۡنَ فِي بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجۡنَ تَبَرُّجَ ٱلۡجَٰهِلِيَّةِ ٱلۡأُولَىٰۖ وَأَقِمۡنَ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتِينَ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَطِعۡنَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓۚ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُذۡهِبَ عَنكُمُ ٱلرِّجۡسَ أَهۡلَ ٱلۡبَيۡتِ وَيُطَهِّرَكُمۡ تَطۡهِيرٗا

33. በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ:: እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገላለጥም (በመጌጥ) አትገለጡ:: ሶላትንም በደንቡ ስገዱ:: ዘካንም ስጡ:: አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ:: የነብዩ ቤተሰቦች ሆይ! አላህ የሚሻው ከናንተ ላይ ርክሰትን ሊያስወግድና ማጥራትንም ሊያጠራችሁ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 33

وَٱذۡكُرۡنَ مَا يُتۡلَىٰ فِي بُيُوتِكُنَّ مِنۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ وَٱلۡحِكۡمَةِۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ لَطِيفًا خَبِيرًا

34. ከአላህ አናቅጽና ከጥበቡም በቤቶቻችሁ የሚነበበውን አስታውሱ:: አላህ እዝነቱ ረቂቅና ውስጠ አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
35 : 33

إِنَّ ٱلۡمُسۡلِمِينَ وَٱلۡمُسۡلِمَٰتِ وَٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ وَٱلۡقَٰنِتِينَ وَٱلۡقَٰنِتَٰتِ وَٱلصَّٰدِقِينَ وَٱلصَّٰدِقَٰتِ وَٱلصَّٰبِرِينَ وَٱلصَّٰبِرَٰتِ وَٱلۡخَٰشِعِينَ وَٱلۡخَٰشِعَٰتِ وَٱلۡمُتَصَدِّقِينَ وَٱلۡمُتَصَدِّقَٰتِ وَٱلصَّٰٓئِمِينَ وَٱلصَّٰٓئِمَٰتِ وَٱلۡحَٰفِظِينَ فُرُوجَهُمۡ وَٱلۡحَٰفِظَٰتِ وَٱلذَّٰكِرِينَ ٱللَّهَ كَثِيرٗا وَٱلذَّٰكِرَٰتِ أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُم مَّغۡفِرَةٗ وَأَجۡرًا عَظِيمٗا

35. ሙስሊም ወንዶችና ሙስሊም ሴቶች፤ ምእምናንና ምዕመናትም፤ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፤ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፤ ታጋሽ ወንዶችና ታጋሽ ሴቶችም፤ አላህን ፈሪ ወንዶችና አላህን ፈሪ ሴቶችም፤ መጽዋች ወንዶችና መጽዋች ሴቶችም፤ ጿሚ ወንዶችና ጿሚ ሴቶችም፤ ካልተፈቀደ ስራ ብልቶቻቸውን ጠባቂ ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፤ አላህን በብዙ አውሺ ወንዶችና አውሺ ሴቶችም አላህ ለእነርሱ ምህረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል:: info
التفاسير: