Tradução dos significados do Nobre Qur’an. - Tradução do amárico - Academia África

Número de página:close

external-link copy
23 : 3

أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ أُوتُواْ نَصِيبٗا مِّنَ ٱلۡكِتَٰبِ يُدۡعَوۡنَ إِلَىٰ كِتَٰبِ ٱللَّهِ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَهُمۡ ثُمَّ يَتَوَلَّىٰ فَرِيقٞ مِّنۡهُمۡ وَهُم مُّعۡرِضُونَ

23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ ከመጽሐፍ (ትምህርት) ድረሻን ወደ ተሰጡት ሰዎች አላየህምን? ወደ አላህ መጽሐፍ በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ይጠራሉ:: ከዚያ ከእነርሱ ገሚሶቹ (ከፊሎቹ) እውነቱን ወደ ጎን የተው ሆነው ይሸሻሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 3

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَالُواْ لَن تَمَسَّنَا ٱلنَّارُ إِلَّآ أَيَّامٗا مَّعۡدُودَٰتٖۖ وَغَرَّهُمۡ فِي دِينِهِم مَّا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ

24. ይህም እነርሱ «የገሀነም እሳት የተቆጠሩ ቀናትን ብቻ እንጂ አትነካንም።» በማለታቸው ነው:: በሀይማኖታቸዉም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር አታለላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 3

فَكَيۡفَ إِذَا جَمَعۡنَٰهُمۡ لِيَوۡمٖ لَّا رَيۡبَ فِيهِ وَوُفِّيَتۡ كُلُّ نَفۡسٖ مَّا كَسَبَتۡ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ

25. በእርሱ መምጣት ጥርጥር የሌለበት በሆነው ቀን በሰበሰብናቸውና ነፍስ ሁሉ የሰራችውን ስራ በተሞላች ጊዜ እንዴት ይሆናሉ? እነርሱም ቅንጣትንም አይበደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 3

قُلِ ٱللَّهُمَّ مَٰلِكَ ٱلۡمُلۡكِ تُؤۡتِي ٱلۡمُلۡكَ مَن تَشَآءُ وَتَنزِعُ ٱلۡمُلۡكَ مِمَّن تَشَآءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَآءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَآءُۖ بِيَدِكَ ٱلۡخَيۡرُۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል: «የንግስና ባለቤት የሆንከው አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግስናን ትሰጣለህ:: ከምትሻዉም ሰው ንግስናን ትገፋለህ:: የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ:: የምትሻውንም ሰው ደግሞ ታዋርዳለህ:: መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ብቻ ነው:: አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና። info
التفاسير:

external-link copy
27 : 3

تُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَتُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِۖ وَتُخۡرِجُ ٱلۡحَيَّ مِنَ ٱلۡمَيِّتِ وَتُخۡرِجُ ٱلۡمَيِّتَ مِنَ ٱلۡحَيِّۖ وَتَرۡزُقُ مَن تَشَآءُ بِغَيۡرِ حِسَابٖ

27. «ሌሊቱን በቀን ውስጥ ታስገባለህ:: ቀኑንም በሌሊት ውስጥ ታስገባለህ:: ሕያውንም ከሙት ታወጣለህ:: ሙታንንም ከሕያው ታወጣለህ፤ ለምትሻውም ሁሉ መጠን የለሽ ሲሳይ ትሰጣለህ።» በል። info
التفاسير:

external-link copy
28 : 3

لَّا يَتَّخِذِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ ٱلۡكَٰفِرِينَ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَۖ وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ فَلَيۡسَ مِنَ ٱللَّهِ فِي شَيۡءٍ إِلَّآ أَن تَتَّقُواْ مِنۡهُمۡ تُقَىٰةٗۗ وَيُحَذِّرُكُمُ ٱللَّهُ نَفۡسَهُۥۗ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلۡمَصِيرُ

28. አማኞች ከሓዲያንን ከአማኞች ሌላ ረዳቶች አድርገው አይያዙ። ይህንን የሚሰራ ከአላህ ሀይማኖት በምንም ውስጥ አይደለም:: ከእነርሱ መጠበቅን ብትጠበቁ እንጂ:: አላህ ከእርሱው ያስጠነቅቃችኋል:: መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 3

قُلۡ إِن تُخۡفُواْ مَا فِي صُدُورِكُمۡ أَوۡ تُبۡدُوهُ يَعۡلَمۡهُ ٱللَّهُۗ وَيَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ብትደብቁት ወይም ብትገልጹት አላህ ያውቀዋል:: በሰማያት ውስጥ ያለውንና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።» በል። info
التفاسير: