د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي

د مخ نمبر:close

external-link copy
77 : 19

أَفَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي كَفَرَ بِـَٔايَٰتِنَا وَقَالَ لَأُوتَيَنَّ مَالٗا وَوَلَدًا

77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በአናቅጻችን የካደውንና «በትንሣኤ ቀን ገንዘብም ሆነ ልጅ በእርግጥ እሰጣለሁ» ያለውን አየህን? info
التفاسير:

external-link copy
78 : 19

أَطَّلَعَ ٱلۡغَيۡبَ أَمِ ٱتَّخَذَ عِندَ ٱلرَّحۡمَٰنِ عَهۡدٗا

78. ሩቁን ምስጢር አወቀን ? ወይስ አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ? info
التفاسير:

external-link copy
79 : 19

كَلَّاۚ سَنَكۡتُبُ مَا يَقُولُ وَنَمُدُّ لَهُۥ مِنَ ٱلۡعَذَابِ مَدّٗا

79. ከዚህ አቋሙ ይታቀብ:: አይሰጠዉም:: የሚለውን ሁሉ በእርግጥ እንጽፋለን:: ለእርሱም ከቅጣት ጭማሬን እንጨምርለታለን:: info
التفاسير:

external-link copy
80 : 19

وَنَرِثُهُۥ مَا يَقُولُ وَيَأۡتِينَا فَرۡدٗا

80. አለኝ የሚለውንም ሁሉ እንወርሰዋለን ወደ እኛም ብቻውን ሆኖ ይመጣል:: info
التفاسير:

external-link copy
81 : 19

وَٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةٗ لِّيَكُونُواْ لَهُمۡ عِزّٗا

81. ከአላህ ሌላ አማልክትን ለእነርሱ መከበሪያ አማላጅ እንዲሆኗቸው ያዙ:: info
التفاسير:

external-link copy
82 : 19

كَلَّاۚ سَيَكۡفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمۡ وَيَكُونُونَ عَلَيۡهِمۡ ضِدًّا

82. ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ (ይታቀቡ):: መገዛታቸውን በእርግጥ ወደፊት ይከዷቸዋል:: በእነርሱም ላይ ተቃራኒ (ባላጋራ) ይሆኑባቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
83 : 19

أَلَمۡ تَرَ أَنَّآ أَرۡسَلۡنَا ٱلشَّيَٰطِينَ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ تَؤُزُّهُمۡ أَزّٗا

83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰይጣናትን በከሓዲያን ላይ በመጥፎ ሥራ የሚገፋፏቸው ሲሆኑ የላክንባቸው መሆናችንን አላየህምን:: info
التفاسير:

external-link copy
84 : 19

فَلَا تَعۡجَلۡ عَلَيۡهِمۡۖ إِنَّمَا نَعُدُّ لَهُمۡ عَدّٗا

84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም መቀጣት ላይ አትቸኩል:: ለእነርሱ ቀንን እንቆጥርላቸዋለንና:: info
التفاسير:

external-link copy
85 : 19

يَوۡمَ نَحۡشُرُ ٱلۡمُتَّقِينَ إِلَى ٱلرَّحۡمَٰنِ وَفۡدٗا

85. ትክክለኛ አማኞችን የተከበሩ ቡድኖች ሆነው ወደ አዛኙ አምላክ የምንሰበሰብበትንና: info
التفاسير:

external-link copy
86 : 19

وَنَسُوقُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ إِلَىٰ جَهَنَّمَ وِرۡدٗا

86. ከሓዲያንን የተጠሙ ሆነው ወደገሀነም የምንነዳበትን ቀን አስታውስ። info
التفاسير:

external-link copy
87 : 19

لَّا يَمۡلِكُونَ ٱلشَّفَٰعَةَ إِلَّا مَنِ ٱتَّخَذَ عِندَ ٱلرَّحۡمَٰنِ عَهۡدٗا

87. አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ቢሆን እንጂ ሌሎች ማማለድን አይችሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
88 : 19

وَقَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَلَدٗا

88. አጋሪዎች «አዛኙ አምላክ አላህ ልጅ ወለደ።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
89 : 19

لَّقَدۡ جِئۡتُمۡ شَيۡـًٔا إِدّٗا

89.(አጋሪዎች ሆይ!) እጅግ ከባድና መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
90 : 19

تَكَادُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ يَتَفَطَّرۡنَ مِنۡهُ وَتَنشَقُّ ٱلۡأَرۡضُ وَتَخِرُّ ٱلۡجِبَالُ هَدًّا

90. ከዚህ ንግግራቸው ሰማያት ሊቀደዱ፤ ምድርም ልትሰነጠቅ፤ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
91 : 19

أَن دَعَوۡاْ لِلرَّحۡمَٰنِ وَلَدٗا

91. ይህም ለአዛኙ አምላክ ልጅ አለው ስላሉ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
92 : 19

وَمَا يَنۢبَغِي لِلرَّحۡمَٰنِ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا

92. አዛኙ ጌታ ልጅን መያዝ አይገባዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
93 : 19

إِن كُلُّ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّآ ءَاتِي ٱلرَّحۡمَٰنِ عَبۡدٗا

93. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በትንሣኤ ቀን (ለአር-ረህማን) ለአዛኙ ጌታ ባሪያ ሆነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
94 : 19

لَّقَدۡ أَحۡصَىٰهُمۡ وَعَدَّهُمۡ عَدّٗا

94. አላህ በእርግጥ በዕውቀቱ ከቧቸዋል:: መቁጠርንም ቆጥሯቸዋል:: info
التفاسير:

external-link copy
95 : 19

وَكُلُّهُمۡ ءَاتِيهِ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فَرۡدًا

95. ሁሉም በትንሳኤ ቀን ለየብቻ ሆነው ወደ እርሱ መጪዎች ናቸው:: info
التفاسير: