د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي

መርየም

external-link copy
1 : 19

كٓهيعٓصٓ

1. ካፍ፤ ሃ፤ ያ፤ ዐይን፤ ሷድ፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 19

ذِكۡرُ رَحۡمَتِ رَبِّكَ عَبۡدَهُۥ زَكَرِيَّآ

2. ይህ ጌታህ ባርያውን ዘከሪያን በችሮታው ያወሳበት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 19

إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ نِدَآءً خَفِيّٗا

3. ጌታውን የሚስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 19

قَالَ رَبِّ إِنِّي وَهَنَ ٱلۡعَظۡمُ مِنِّي وَٱشۡتَعَلَ ٱلرَّأۡسُ شَيۡبٗا وَلَمۡ أَكُنۢ بِدُعَآئِكَ رَبِّ شَقِيّٗا

4. (እንዲህም) አለ: «ጌታዬ ሆይ! እኔ አጥንቴም ደከመ:: ራሴም በሽበት ተንቀለቀለ። ጌታዬ ሆይ! አንተንም በመለመኔ፤ ምንጊዜም ዕድለ ቢስ እልሆንኩም። info
التفاسير:

external-link copy
5 : 19

وَإِنِّي خِفۡتُ ٱلۡمَوَٰلِيَ مِن وَرَآءِي وَكَانَتِ ٱمۡرَأَتِي عَاقِرٗا فَهَبۡ لِي مِن لَّدُنكَ وَلِيّٗا

5. «እኔም ከበኋላዬ (ከሞትኩ በኋላ) ዘመዶቼን (ከእምነት እንዳይወጡ) ፈራሁ:: ሚስቴም መካን ነበረች:: ስለዚህ ካንተ ዘንድ ለእኔ ልጅን ስጠኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 19

يَرِثُنِي وَيَرِثُ مِنۡ ءَالِ يَعۡقُوبَۖ وَٱجۡعَلۡهُ رَبِّ رَضِيّٗا

6. «የሚወርሰኝ ከየዕቁብ ቤተሰቦችም የእምነትን ሃላፊነት የሚወርስን ልጅ ስጠኝ:: ጌታዬ ሆይ! ተወዳጅም አድርገው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
7 : 19

يَٰزَكَرِيَّآ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَٰمٍ ٱسۡمُهُۥ يَحۡيَىٰ لَمۡ نَجۡعَل لَّهُۥ مِن قَبۡلُ سَمِيّٗا

7. «ዘከሪያ ሆይ! እኛ ስሙ የሕያ በሆነና ከዚያ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት ወንድ ልጅ እናበስርሃለን።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 19

قَالَ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي غُلَٰمٞ وَكَانَتِ ٱمۡرَأَتِي عَاقِرٗا وَقَدۡ بَلَغۡتُ مِنَ ٱلۡكِبَرِ عِتِيّٗا

8. «ጌታዬ ሆይ! ሚስቴ መካን እኔም ከእርጅና የተነሳ ድርቀትን የደረስኩ ስሆን እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 19

قَالَ كَذَٰلِكَ قَالَ رَبُّكَ هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٞ وَقَدۡ خَلَقۡتُكَ مِن قَبۡلُ وَلَمۡ تَكُ شَيۡـٔٗا

9. (ጅብሪልም) አለ: «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው። ጌታህ ‹ከዚህ በፊት ምንም ያልነበርከውን የፈጠርኩህ ስሆን እርሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው።› ብሏል።» info
التفاسير:

external-link copy
10 : 19

قَالَ رَبِّ ٱجۡعَل لِّيٓ ءَايَةٗۖ قَالَ ءَايَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ ٱلنَّاسَ ثَلَٰثَ لَيَالٖ سَوِيّٗا

10. እርሱም «ጌታዬ ሆይ! እንግዲያውስ ምልክት አድርግልኝ።» አለ። «ምልክትህ (ጤናማ ሆነህ ሳለህ) ሶስት ሌሊት ከነቀናቸው ሰዎችን ማነጋገር አለመቻልህ ነው።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 19

فَخَرَجَ عَلَىٰ قَوۡمِهِۦ مِنَ ٱلۡمِحۡرَابِ فَأَوۡحَىٰٓ إِلَيۡهِمۡ أَن سَبِّحُواْ بُكۡرَةٗ وَعَشِيّٗا

11. እርሱም ከምኩራቡ ወደ ህዝቦቹ ወጣ:: ጧትና ማታ ጌታችሁን አውሱ አጥሩትም በማለትም ወደ እነርሱ ጠቀሰ። info
التفاسير: