ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ

ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ: 213:208 close

external-link copy
43 : 10

وَمِنۡهُم مَّن يَنظُرُ إِلَيۡكَۚ أَفَأَنتَ تَهۡدِي ٱلۡعُمۡيَ وَلَوۡ كَانُواْ لَا يُبۡصِرُونَ

43. ከእነርሱም መካከል ወደ አንተ የሚመለከቱ አሉ:: አንተ ልበ እውራንን የማያዩ ቢሆኑም ትመራለህን? info
التفاسير:

external-link copy
44 : 10

إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَظۡلِمُ ٱلنَّاسَ شَيۡـٔٗا وَلَٰكِنَّ ٱلنَّاسَ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ

44. አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም:: ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 10

وَيَوۡمَ يَحۡشُرُهُمۡ كَأَن لَّمۡ يَلۡبَثُوٓاْ إِلَّا سَاعَةٗ مِّنَ ٱلنَّهَارِ يَتَعَارَفُونَ بَيۡنَهُمۡۚ قَدۡ خَسِرَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِلِقَآءِ ٱللَّهِ وَمَا كَانُواْ مُهۡتَدِينَ

45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንን ከቀን አንዲትን ሰዓት እንጂ አንዳልቆዩ መስለው በመካከላቸው የሚተዋወቁ ሲሆኑ በምንሰበስባቸው ቀን የሚከሰተውን አስታውስ:: እነዚያ በአላህ መገናኘት ያስተባበሉት ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: የተመሩም አልነበሩምና:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 10

وَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعۡضَ ٱلَّذِي نَعِدُهُمۡ أَوۡ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيۡنَا مَرۡجِعُهُمۡ ثُمَّ ٱللَّهُ شَهِيدٌ عَلَىٰ مَا يَفۡعَلُونَ

46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያንም የምናስፈራራባቸውን ነገር ውጤት ከፊሉን (በሕይወትህ ሳለህ) ብናሳይህ (መልካም ነው):: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ (ጉዳዩ የእኔ ነው):: መመለሻቸው ወደ እኛ ነውና:: ከዚያ አላህ በሚሠሩት ሥራ ላይ ሁሉ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
47 : 10

وَلِكُلِّ أُمَّةٖ رَّسُولٞۖ فَإِذَا جَآءَ رَسُولُهُمۡ قُضِيَ بَيۡنَهُم بِٱلۡقِسۡطِ وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ

47. ለሕዝቦችም ሁሉ መልዕክተኛ አላቸው:: መልዕክተኛቸው በመጣ ጊዜ (ሲያስተባብሉት) በመካከላቸው በትክክል ይፈረዳል:: እነርሱም ፍጹም አይበደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 10

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

48. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እውነተኞች ከሆናችሁ የቅጣቱ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 10

قُل لَّآ أَمۡلِكُ لِنَفۡسِي ضَرّٗا وَلَا نَفۡعًا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۗ لِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌۚ إِذَا جَآءَ أَجَلُهُمۡ فَلَا يَسۡتَـٔۡخِرُونَ سَاعَةٗ وَلَا يَسۡتَقۡدِمُونَ

49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለራሴ ጉዳትን ማድረስም ሆነ ጥቅምን ማስከበር አላህ ከሻው በስተቀር አልችልም:: ለህዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው:: ጊዜያቸው በደረሰ ወቅት አንዲትን ሰዓት እንኳን አይቆዩም:: አይቀደሙምም።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 10

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِنۡ أَتَىٰكُمۡ عَذَابُهُۥ بَيَٰتًا أَوۡ نَهَارٗا مَّاذَا يَسۡتَعۡجِلُ مِنۡهُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ

50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እስቲ ንገሩኝ ቅጣቱ በሌሊት ወይም በቀን ቢመጣባችሁ አጋሪዎቹ የሚያስቸኩላቸው ነገር ምንድን ነው?» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 10

أَثُمَّ إِذَا مَا وَقَعَ ءَامَنتُم بِهِۦٓۚ ءَآلۡـَٰٔنَ وَقَدۡ كُنتُم بِهِۦ تَسۡتَعۡجِلُونَ

51. «ከዚያም ቅጣቱ በወደቀ ጊዜ በእርሱ አመናችሁበትን? በእርግጥ በእርሱ የምትቻኮሉ የነበራችሁ ስትሆኑ አሁን ነው የምታምኑትን?» ይባላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
52 : 10

ثُمَّ قِيلَ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ ذُوقُواْ عَذَابَ ٱلۡخُلۡدِ هَلۡ تُجۡزَوۡنَ إِلَّا بِمَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ

52. ከዚያ ለእነዚያ ለበደሉት ሰዎች «ዘውታሪውን ቅጣት ቅመሱ። ትሠሩ የነበራችሁትን እኩይ ተግባር ዋጋ እንጂ ትመነዳላችሁን? (አትመነዱም)።» ይባላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 10

۞ وَيَسۡتَنۢبِـُٔونَكَ أَحَقٌّ هُوَۖ قُلۡ إِي وَرَبِّيٓ إِنَّهُۥ لَحَقّٞۖ وَمَآ أَنتُم بِمُعۡجِزِينَ

53. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «(ከሞት በኋላ መቀስቀስ) እውነት ነውን?» ሲሉ ይጠይቁሃል:: «አዎን! በጌታዬ እምላለሁ እርሱ እውነት ነው:: እናንተም የምታቅቱ አይደላችሁም።» በላቸው። info
التفاسير: