ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ

ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ: 209:208 close

external-link copy
15 : 10

وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَاتُنَا بَيِّنَٰتٖ قَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرۡجُونَ لِقَآءَنَا ٱئۡتِ بِقُرۡءَانٍ غَيۡرِ هَٰذَآ أَوۡ بَدِّلۡهُۚ قُلۡ مَا يَكُونُ لِيٓ أَنۡ أُبَدِّلَهُۥ مِن تِلۡقَآيِٕ نَفۡسِيٓۖ إِنۡ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَيَّۖ إِنِّيٓ أَخَافُ إِنۡ عَصَيۡتُ رَبِّي عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ

15. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን ግልጽ ሆነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩት (የማይሹት) ሰዎች «ከዚህ ሌላ የሆነን ቁርኣን አምጣልን ወይም ለውጠው።» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከራሴ በኩል ልለውጠው አይገባኝም:: ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ አልከተልም:: እኔ በጌታዬ ትዕዛዝ ላይ ባምጽ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 10

قُل لَّوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَا تَلَوۡتُهُۥ عَلَيۡكُمۡ وَلَآ أَدۡرَىٰكُم بِهِۦۖ فَقَدۡ لَبِثۡتُ فِيكُمۡ عُمُرٗا مِّن قَبۡلِهِۦٓۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

16. (መልዕከተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባላነበብኩትና አላህ እርሱን ባላሳወቃችሁ ነበር:: በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት ምንም ሳልል ብዙን እድሜ በእርግጥ ኖሬያለሁ። አታውቁምን?» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 10

فَمَنۡ أَظۡلَمُ مِمَّنِ ٱفۡتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ كَذِبًا أَوۡ كَذَّبَ بِـَٔايَٰتِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ

17. በአላህ ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይ ከአናቅ ጹ መካከል (በአንዷ እንኳን) ካስተባበለ ይበልጥ በዳይ ማን ነው? እነሆ አመጸኞች አይድኑም:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 10

وَيَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمۡ وَلَا يَنفَعُهُمۡ وَيَقُولُونَ هَٰٓؤُلَآءِ شُفَعَٰٓؤُنَا عِندَ ٱللَّهِۚ قُلۡ أَتُنَبِّـُٔونَ ٱللَّهَ بِمَا لَا يَعۡلَمُ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ سُبۡحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشۡرِكُونَ

18. አጋሪዎች ከአላህ ሌላ የማይጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውን ይገዛሉ:: «እነዚህ አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው።» ይላሉም። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ እናንተ ትነግሩታላችሁን?» በላቸው:: አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ:: ላቀም:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 10

وَمَا كَانَ ٱلنَّاسُ إِلَّآ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ فَٱخۡتَلَفُواْۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡ فِيمَا فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ

19. ሰዎች አንድ ህዝብ እንጂ ሌላ አልነበሩም:: ከዚያ ተለያዩ:: ከጌታህ ያለፈ ቃልም ባልነበረ ኖሮ በዚያ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው በቶሎ በተፈረደ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 10

وَيَقُولُونَ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٞ مِّن رَّبِّهِۦۖ فَقُلۡ إِنَّمَا ٱلۡغَيۡبُ لِلَّهِ فَٱنتَظِرُوٓاْ إِنِّي مَعَكُم مِّنَ ٱلۡمُنتَظِرِينَ

20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ተዓምር ለምን አትወረድለትም?» ይላሉ:: «ሩቅ ነገር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው:: እናንተም ተጠባበቁ እኔም ከናንተው ጋር ከሚጠባበቁት ነኝ።» በላቸው። info
التفاسير: