पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी ।

رقم الصفحة:close

external-link copy
53 : 3

رَبَّنَآ ءَامَنَّا بِمَآ أَنزَلۡتَ وَٱتَّبَعۡنَا ٱلرَّسُولَ فَٱكۡتُبۡنَا مَعَ ٱلشَّٰهِدِينَ

53. («ጌታችን ሆይ! ባወረድከው አምነን መልዕክተኛውን ተከትለናል::( እኛንም ባንተ ብቸኛ አምላክነት በነብያት መልዕክተኛነት) ከመስካሪዎች ጋራ መዝግበን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
54 : 3

وَمَكَرُواْ وَمَكَرَ ٱللَّهُۖ وَٱللَّهُ خَيۡرُ ٱلۡمَٰكِرِينَ

54.አይሁድም በዒሳ ላይ አደሙ:: አላህ ግን አድማቸውን አከሸፈባቸው። አላህ የአድመኞችን ሴራ በማክሸፍ ከሁሉ የበለጠ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
55 : 3

إِذۡ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّي مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَيَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَجَاعِلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوكَ فَوۡقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِۖ ثُمَّ إِلَيَّ مَرۡجِعُكُمۡ فَأَحۡكُمُ بَيۡنَكُمۡ فِيمَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ

55. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡- «ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጅህና ከምድር ወደ እኔ አንሽህ ነኝ:: ከነዚያም በእኔ ከካዱ ሰዎች (ተንኮል) አጥሪህ ነኝ። እነዚያ የተከተሉህንም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ:: ከዚያ የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው:: ያን ትለያዩበት በነበራችሁበት ነገርም በመካከላችሁ እፈርዳለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
56 : 3

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَأُعَذِّبُهُمۡ عَذَابٗا شَدِيدٗا فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ

56.«እነዚያማ የካዱትን በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱ ቅጣትን እቀጣቸዋለሁ:: ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸዉም» info
التفاسير:

external-link copy
57 : 3

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَيُوَفِّيهِمۡ أُجُورَهُمۡۗ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

57. እነዚያማ አምነው መልካም ስራዎችን የሰሩትን አላህ ምንዳቸውን ይሞላላቸዋል:: አላህም በዳዮችን አይወድምና። info
التفاسير:

external-link copy
58 : 3

ذَٰلِكَ نَتۡلُوهُ عَلَيۡكَ مِنَ ٱلۡأٓيَٰتِ وَٱلذِّكۡرِ ٱلۡحَكِيمِ

58.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይህ ተዓምራትና ጥበብን ከያዘው ተግሳጽ በአንተ ላይ የምናነበው ነው። info
التفاسير:

external-link copy
59 : 3

إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٖ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

59. አላህ ዘንድ የዒሳ (ያለ አባት መፈጠሩ) ምሳሌው ልክ እንደ (ያለ አባትና ያለ እናት እንደተፈጠሩት አባታችን) አደም ቢጤ ነው:: አላህ ከአፈር ፈጠረውና ከዚያም «ሁን» አለው። ከዚያ ሰው ሆነ። info
التفاسير:

external-link copy
60 : 3

ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلۡمُمۡتَرِينَ

60.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውነታው ከጌታህ ዘንድ የመጣልህ እውነት ነው። እናም ከተጠራጣሪዎች አትሁን። info
التفاسير:

external-link copy
61 : 3

فَمَنۡ حَآجَّكَ فِيهِ مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلۡعِلۡمِ فَقُلۡ تَعَالَوۡاْ نَدۡعُ أَبۡنَآءَنَا وَأَبۡنَآءَكُمۡ وَنِسَآءَنَا وَنِسَآءَكُمۡ وَأَنفُسَنَا وَأَنفُسَكُمۡ ثُمَّ نَبۡتَهِلۡ فَنَجۡعَل لَّعۡنَتَ ٱللَّهِ عَلَى ٱلۡكَٰذِبِينَ

61.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እውቀት ከመጣልህ በኋላ በእርሱ (በዒሳ) የተከራከሩህን «ኑ ልጆቻችንንና ልጆቻችሁን፣ ሴቶቻችንንና (ሚስቶቻችንና) ሴቶቻችሁን (ሚስቶቻችሁን)፣ ነፍሶቻችንንና ነፍሶቻችሁን እንጥራና ከዚያ አላህን እንለምን:: የአላህንም ቁጣ በውሸታሞች ላይ እናድርግ።» በላቸው። info
التفاسير: