पवित्र कुरअानको अर्थको अनुवाद - अम्हरी अनुवाद : अफ्रिका एकेडेमी ।

رقم الصفحة:close

external-link copy
174 : 3

فَٱنقَلَبُواْ بِنِعۡمَةٖ مِّنَ ٱللَّهِ وَفَضۡلٖ لَّمۡ يَمۡسَسۡهُمۡ سُوٓءٞ وَٱتَّبَعُواْ رِضۡوَٰنَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ ذُو فَضۡلٍ عَظِيمٍ

174. ከዚያም የአላህን ጸጋና ችሮታ ይዘው ምንም ክፉ ነገር ሳይነካቸው በሰላም ተመለሱ:: የአላህን ውዴታም ተከተሉ:: አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
175 : 3

إِنَّمَا ذَٰلِكُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ يُخَوِّفُ أَوۡلِيَآءَهُۥ فَلَا تَخَافُوهُمۡ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

175. ይህ የሚያስፈራራችሁ ሰይጣን ብቻ ነው። ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል። (አማኞች ሆይ!) የሰይጣንን ወዳጆችን አትፍሯቸው:: ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁም እኔን ብቻ ፍሩኝ:: info
التفاسير:

external-link copy
176 : 3

وَلَا يَحۡزُنكَ ٱلَّذِينَ يُسَٰرِعُونَ فِي ٱلۡكُفۡرِۚ إِنَّهُمۡ لَن يَضُرُّواْ ٱللَّهَ شَيۡـٔٗاۚ يُرِيدُ ٱللَّهُ أَلَّا يَجۡعَلَ لَهُمۡ حَظّٗا فِي ٱلۡأٓخِرَةِۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٌ

176. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የእነዚያ ወደ ክህደት የሚቻኮሉ ሰዎች አድራጎት (ተግባር) አያሳዝንህ:: እነርሱ ፈጽሞ አላህን በምንም አይጎዱትምና:: አላህ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ እድልን ላያደርግ ይሻልና:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
177 : 3

إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱشۡتَرَوُاْ ٱلۡكُفۡرَ بِٱلۡإِيمَٰنِ لَن يَضُرُّواْ ٱللَّهَ شَيۡـٔٗاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

177. እነዚያ ክህደትን በእምነት የለወጡ ክፍሎች ሁሉ አላህን በምንም ነገር ፈጽሞ አይጎዱትም:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
178 : 3

وَلَا يَحۡسَبَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَنَّمَا نُمۡلِي لَهُمۡ خَيۡرٞ لِّأَنفُسِهِمۡۚ إِنَّمَا نُمۡلِي لَهُمۡ لِيَزۡدَادُوٓاْ إِثۡمٗاۖ وَلَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ

178. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎች ሁሉ እነርሱን ማዘግየታችንን ለነፍሶቻችን ደግ ነገር ነው ብለው አያስቡ:: እነርሱን የምናዘገያቸው ኃጢአትን እንዲጨምሩ ብቻ ነውና:: ለእነርሱም አዋራጅ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
179 : 3

مَّا كَانَ ٱللَّهُ لِيَذَرَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ عَلَىٰ مَآ أَنتُمۡ عَلَيۡهِ حَتَّىٰ يَمِيزَ ٱلۡخَبِيثَ مِنَ ٱلطَّيِّبِۗ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُطۡلِعَكُمۡ عَلَى ٱلۡغَيۡبِ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَجۡتَبِي مِن رُّسُلِهِۦ مَن يَشَآءُۖ فَـَٔامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرُسُلِهِۦۚ وَإِن تُؤۡمِنُواْ وَتَتَّقُواْ فَلَكُمۡ أَجۡرٌ عَظِيمٞ

179. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) አላህ መጥፎውን ከመልካሙ እስከሚለይ ድረስ አማኞችን እናንተ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ የሚተዋቸው አይደለም:: አላህም ሩቁን ነገር የሚያሳውቃችሁ አይደለም:: ግን አላህ ከመልዕክተኞቹ የሚሻውን ይመርጣል:: እናም በአላህና በመልዕክተኞቹም እመኑ:: ብታምኑና ብትጠነቀቁ ለእናንተ ታላቅ ምንዳ አለላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
180 : 3

وَلَا يَحۡسَبَنَّ ٱلَّذِينَ يَبۡخَلُونَ بِمَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦ هُوَ خَيۡرٗا لَّهُمۖ بَلۡ هُوَ شَرّٞ لَّهُمۡۖ سَيُطَوَّقُونَ مَا بَخِلُواْ بِهِۦ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ وَلِلَّهِ مِيرَٰثُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ

180. እነዚያ አላህ ከችሮታው ከሰጣቸው ገንዘብ የሚነፍጉ ሰዎች ንፉግነት ደግ ተግባር አይምሰላቸው:: ይልቁንም እርሱ ለእነርሱ መጥፎ ባህሪ ነው:: ያንን በእርሱ የነፈጉበት ገንዘብ በትንሳኤ ቀን (እባብ ሆኖ) በአንገታቸው ይጠለቃሉ:: የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ነው:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና:: info
التفاسير: