Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija

Puslapio numeris:close

external-link copy
62 : 8

وَإِن يُرِيدُوٓاْ أَن يَخۡدَعُوكَ فَإِنَّ حَسۡبَكَ ٱللَّهُۚ هُوَ ٱلَّذِيٓ أَيَّدَكَ بِنَصۡرِهِۦ وَبِٱلۡمُؤۡمِنِينَ

62. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሊያታልሉህ ቢፈልጉ አላህ በቂህ ነው:: እርሱ ያ በእርዳታውና በምዕምናን ያበረታህ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 8

وَأَلَّفَ بَيۡنَ قُلُوبِهِمۡۚ لَوۡ أَنفَقۡتَ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا مَّآ أَلَّفۡتَ بَيۡنَ قُلُوبِهِمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ أَلَّفَ بَيۡنَهُمۡۚ إِنَّهُۥ عَزِيزٌ حَكِيمٞ

63. በልቦቻቸውም መካከል ያስማማ ነው፡፡ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምድር ያለውን ሁሉ ሀብት ብትለገስ ኖሮ እንኳን በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር:: ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ:: እርሱ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 8

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَسۡبُكَ ٱللَّهُ وَمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ

64. አንተ ነብይ ሆይ! ለሁሉ ነገር በቂህ አላህ ነው:: ለተከተሉህም ምዕምናን በቂያቸው አላህ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 8

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَرِّضِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ عَلَى ٱلۡقِتَالِۚ إِن يَكُن مِّنكُمۡ عِشۡرُونَ صَٰبِرُونَ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ

65. አንተ ነብይ ሆይ! አማኞችን ጠላቶቻቸውን በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው:: ከናንተ ውስጥ ሃያ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ:: ከናንተም መካከል መቶ ሰዎች ቢኖሩ ከእነዚያ ከካዱት ሕዝቦች መካከል አንድ ሺሕን ያሸንፋሉ:: ምክንያቱም እነርሱ የማይገነዘቡ ህዝቦች ናቸዉና:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 8

ٱلۡـَٰٔنَ خَفَّفَ ٱللَّهُ عَنكُمۡ وَعَلِمَ أَنَّ فِيكُمۡ ضَعۡفٗاۚ فَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ صَابِرَةٞ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُمۡ أَلۡفٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفَيۡنِ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّٰبِرِينَ

66. አሁን አላህ ከናንተ ላይ አቀለለላችሁ:: በእናንተ ውስጥም ድክመት መኖሩን አወቀ:: ስለዚህ ከናንተ መካካል መቶ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ:: ከናንተም አንድ ሺህ ቢኖሩ በአላህ ፍቃድ ሁለት ሺዎችን ያሸንፋሉ:: አላህ ከታጋሾቹ ጋር ነዉና:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 8

مَا كَانَ لِنَبِيٍّ أَن يَكُونَ لَهُۥٓ أَسۡرَىٰ حَتَّىٰ يُثۡخِنَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ تُرِيدُونَ عَرَضَ ٱلدُّنۡيَا وَٱللَّهُ يُرِيدُ ٱلۡأٓخِرَةَۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٞ

67. ለነብይ በምድር ላይ ጠላቶቹን እስኪያደክም ድረስ ለእርሱ ምረኮኞች ሊኖሩት አይገባም:: (አማኞች ሆይ!) የቅርቢቱን ዓለም ጠፊ ጥቅም ትፈልጋላችሁ:: አላህ መጨረሻይቱን ይሻል:: አላህም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
68 : 8

لَّوۡلَا كِتَٰبٞ مِّنَ ٱللَّهِ سَبَقَ لَمَسَّكُمۡ فِيمَآ أَخَذۡتُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ

68. ከአላህ ያለፈ ውሳኔ ባልነበረ ኖሮ በወሰዳችሁት ቤዛ ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
69 : 8

فَكُلُواْ مِمَّا غَنِمۡتُمۡ حَلَٰلٗا طَيِّبٗاۚ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٞ

69. (አማኞች ሆይ!) ያ! ከጠላት የማረካችሁትን ሀብት የተፈቀደና መልካም ሲሆን ብሉ:: አላህንም ፍሩ:: አላህም መሓሪና አዛኝ ነውና:: info
التفاسير: