Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija

Puslapio numeris:close

external-link copy
13 : 67

وَأَسِرُّواْ قَوۡلَكُمۡ أَوِ ٱجۡهَرُواْ بِهِۦٓۖ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

13. (ሰዎች ሆይ!) ቃላችሁንም መስጥሩ:: ወይም በእርሱ ጩሁ:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 67

أَلَا يَعۡلَمُ مَنۡ خَلَقَ وَهُوَ ٱللَّطِيفُ ٱلۡخَبِيرُ

14. የፈጠረን አምላክ እርሱ እውቀተ ረቂቁ ውስጠ አዋቂው ሲሆን (ሚስጢርን) ሁሉ አያውቅምን? info
التفاسير:

external-link copy
15 : 67

هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ ذَلُولٗا فَٱمۡشُواْ فِي مَنَاكِبِهَا وَكُلُواْ مِن رِّزۡقِهِۦۖ وَإِلَيۡهِ ٱلنُّشُورُ

15. እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው:: በጋራዎቿና በመንገዶቿም ሂዱ:: ከሲሳዮም ብሉ:: (ኋላ) መመለሻችሁም ወደ እርሱ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 67

ءَأَمِنتُم مَّن فِي ٱلسَّمَآءِ أَن يَخۡسِفَ بِكُمُ ٱلۡأَرۡضَ فَإِذَا هِيَ تَمُورُ

16. በሰማይ ያለው ጌታ በእናንተ ምድርን እንደማያሰምጥባችሁ ወዲያዉም እርሷም (እናንተኑ ውጣ) የምታረገርግ እንደማትሆን ትተማመናላችሁን? (አትፈሩምን?)። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 67

أَمۡ أَمِنتُم مَّن فِي ٱلسَّمَآءِ أَن يُرۡسِلَ عَلَيۡكُمۡ حَاصِبٗاۖ فَسَتَعۡلَمُونَ كَيۡفَ نَذِيرِ

17. ወይስ በሰማይ ያለው ጌታ በእናንተ ላይ ጠጠርን ያዘለች ንፋስን እንደማልክባችሁ ትተማመናላችሁ? (አትፈሩም?) ማስጠንቀቄም እንዴት እንደሆነ ወደ ፊት ታውቃላችሁ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 67

وَلَقَدۡ كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَكَيۡفَ كَانَ نَكِيرِ

18. እነዚያ ከእነርሱ በስተፊት የነበሩትም አስተባበሉ:: ጥላቻየም እንዴት ነበር (አስተዉል)፤ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 67

أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ إِلَى ٱلطَّيۡرِ فَوۡقَهُمۡ صَٰٓفَّٰتٖ وَيَقۡبِضۡنَۚ مَا يُمۡسِكُهُنَّ إِلَّا ٱلرَّحۡمَٰنُۚ إِنَّهُۥ بِكُلِّ شَيۡءِۭ بَصِيرٌ

19. ከበላያቸው ሰልፍ ሰርተው ወዳሉ ወፎች አይመለከቱምን? ክንፎቻቸውን ያጥፋሉ:: ከአር-ረህማን ሌላ የሚይዛቸው የለም:: እርሱ ሁሉን ነገር አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 67

أَمَّنۡ هَٰذَا ٱلَّذِي هُوَ جُندٞ لَّكُمۡ يَنصُرُكُم مِّن دُونِ ٱلرَّحۡمَٰنِۚ إِنِ ٱلۡكَٰفِرُونَ إِلَّا فِي غُرُورٍ

20. በእውነት ያ እርሱ ከአር-ረህማን ሌላ የሚረዳችሁ ለእናንተ የሆነ ሰራዊት ማነው? ከሓዲያን በመታለል ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 67

أَمَّنۡ هَٰذَا ٱلَّذِي يَرۡزُقُكُمۡ إِنۡ أَمۡسَكَ رِزۡقَهُۥۚ بَل لَّجُّواْ فِي عُتُوّٖ وَنُفُورٍ

21. ወይም ሲሳዮን ቢይዝባችሁ ያ ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? በእውነት እነርሱ በሞገድና በመደንበር ውስጥ ጸኑ:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 67

أَفَمَن يَمۡشِي مُكِبًّا عَلَىٰ وَجۡهِهِۦٓ أَهۡدَىٰٓ أَمَّن يَمۡشِي سَوِيًّا عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ

22. በፊቱ ላይ ተደፍቶ የሚሄድ ሰው ይበልጥ የተቀና ነውን? ወይስ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ተስተካክሎ የሚሄድ? info
التفاسير:

external-link copy
23 : 67

قُلۡ هُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَكُمۡ وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَٰرَ وَٱلۡأَفۡـِٔدَةَۚ قَلِيلٗا مَّا تَشۡكُرُونَ

23. እርሱ! ያ አላህ የፈጠራችሁ፤ ለእናተም መስሚያና ማያዎች፤ ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው:: ጥቂትንም አታመሰግኑምን በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 67

قُلۡ هُوَ ٱلَّذِي ذَرَأَكُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَإِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ

24. እርሱ ያ በምድር ላይ የበተናችሁ ነው:: ወደ እርሱም ትሰበሰባላችሁ በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 67

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا ٱلۡوَعۡدُ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ

25. «እውነተኞችም እንደሆናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው ተፈፃሚ የሚሆነው?» ይላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 67

قُلۡ إِنَّمَا ٱلۡعِلۡمُ عِندَ ٱللَّهِ وَإِنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٞ مُّبِينٞ

26. እውቀቱ ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: እኔ ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም በላቸው:: info
التفاسير: