Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija

አር ረሕማን

external-link copy
1 : 55

ٱلرَّحۡمَٰنُ

1. አር-ረህማን info
التفاسير:

external-link copy
2 : 55

عَلَّمَ ٱلۡقُرۡءَانَ

2. ቁርኣንን አስተማረ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 55

خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ

3. ሰውን ፈጠረ:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 55

عَلَّمَهُ ٱلۡبَيَانَ

4. መግለፅንም አስተማረው:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 55

ٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُ بِحُسۡبَانٖ

5. ጸሐይና ጨረቃ በተወሰነ (በየሂሳባቸው) ልክ ይሄዳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 55

وَٱلنَّجۡمُ وَٱلشَّجَرُ يَسۡجُدَانِ

6. የሰማይ ከዋክብትና የምድር ዛፎችም ለእርሱ ይሰግዳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 55

وَٱلسَّمَآءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ ٱلۡمِيزَانَ

7. ሰማይንም ከፍ አደረጋት:: የትክክለኛነትን ሚዛንንም አስቀመጠ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 55

أَلَّا تَطۡغَوۡاْ فِي ٱلۡمِيزَانِ

8. በሚዛን ስትመዝኑም እንዳትበድሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 55

وَأَقِيمُواْ ٱلۡوَزۡنَ بِٱلۡقِسۡطِ وَلَا تُخۡسِرُواْ ٱلۡمِيزَانَ

9. መመዘንንም በትክክል መዝኑ:: ስትመዝኑም አታጉድሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 55

وَٱلۡأَرۡضَ وَضَعَهَا لِلۡأَنَامِ

10. ምድርንም ለፍጡር አደላደላት:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 55

فِيهَا فَٰكِهَةٞ وَٱلنَّخۡلُ ذَاتُ ٱلۡأَكۡمَامِ

11. በውስጧ እሸትም ባለ ሽፍን የሆኑ ዘንባባዎችም ያሉባት ስትሆን፤ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 55

وَٱلۡحَبُّ ذُو ٱلۡعَصۡفِ وَٱلرَّيۡحَانُ

12. ባለቅርፊት ቅንጣትና ባለ መልካም መዓዛ ቅጠሎችም ያሉባት ስትሆን፤ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

13. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች መካከል በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
14 : 55

خَلَقَ ٱلۡإِنسَٰنَ مِن صَلۡصَٰلٖ كَٱلۡفَخَّارِ

14. ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 55

وَخَلَقَ ٱلۡجَآنَّ مِن مَّارِجٖ مِّن نَّارٖ

15. ጂንንም ከጭስ አልባ የእሳት ነበልባል ፈጠረው:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

16. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ ? info
التفاسير:

external-link copy
17 : 55

رَبُّ ٱلۡمَشۡرِقَيۡنِ وَرَبُّ ٱلۡمَغۡرِبَيۡنِ

17. የሁለቱ ምስራቆችና የሁለቱ ምዕራቦች ጌታ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

18. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
19 : 55

مَرَجَ ٱلۡبَحۡرَيۡنِ يَلۡتَقِيَانِ

19. ሁለቱም ባህሮች የሚገናኙ ሲሆኑ ለቀቃቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 55

بَيۡنَهُمَا بَرۡزَخٞ لَّا يَبۡغِيَانِ

20. እንዳይዋሀዱ በመካከላቸው የማይታይ መጋረጃ አለ:: አንዱ በሌላው ላይ ወሰን አያልፉም:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

21. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
22 : 55

يَخۡرُجُ مِنۡهُمَا ٱللُّؤۡلُؤُ وَٱلۡمَرۡجَانُ

22. ሉልና መርጃን የተባሉት ማዕድናት ከሁለቱ (ባህሮች) ይወጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

23. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
24 : 55

وَلَهُ ٱلۡجَوَارِ ٱلۡمُنشَـَٔاتُ فِي ٱلۡبَحۡرِ كَٱلۡأَعۡلَٰمِ

24. እንደ ጋራዎች ሆነው በባህር ውስጥ የተሰሩት ተንሻላዮችም (ታንኳዎች) የእርሱ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

25. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
26 : 55

كُلُّ مَنۡ عَلَيۡهَا فَانٖ

26. በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 55

وَيَبۡقَىٰ وَجۡهُ رَبِّكَ ذُو ٱلۡجَلَٰلِ وَٱلۡإِكۡرَامِ

27. የልቅና እና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊት ብቻ ይቀራል (አይጠፋም):: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

28. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
29 : 55

يَسۡـَٔلُهُۥ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ كُلَّ يَوۡمٍ هُوَ فِي شَأۡنٖ

29.በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል። በየቀኑ ሁሉ እርሱ በስራ ላይ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
30 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

30. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
31 : 55

سَنَفۡرُغُ لَكُمۡ أَيُّهَ ٱلثَّقَلَانِ

31. እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ መቆጣጠር በእርግጥ እንገኛለን:: info
التفاسير:

external-link copy
32 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

32. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
33 : 55

يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ إِنِ ٱسۡتَطَعۡتُمۡ أَن تَنفُذُواْ مِنۡ أَقۡطَارِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ فَٱنفُذُواْۚ لَا تَنفُذُونَ إِلَّا بِسُلۡطَٰنٖ

33. የአጋንንትና የሰው ስብስቦች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ከቻላችሁ ውጡ:: በአላህ ስልጣን እንጂ አትወጡም:: info
التفاسير:

external-link copy
34 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

34. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
35 : 55

يُرۡسَلُ عَلَيۡكُمَا شُوَاظٞ مِّن نَّارٖ وَنُحَاسٞ فَلَا تَنتَصِرَانِ

35. በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበላባልና ጭስን ይላክባችኋል:: ሁለታችሁም ድል አታደርጉም:: info
التفاسير:

external-link copy
36 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

36. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ !) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
37 : 55

فَإِذَا ٱنشَقَّتِ ٱلسَّمَآءُ فَكَانَتۡ وَرۡدَةٗ كَٱلدِّهَانِ

37. ሰማይ በተሰነጠቀችና እንደጽጌረዳ እንደታረበ ቆዳ በሆነች ጊዜ (ጭንቁን ምን አበረታው):: info
التفاسير:

external-link copy
38 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

38. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
39 : 55

فَيَوۡمَئِذٖ لَّا يُسۡـَٔلُ عَن ذَنۢبِهِۦٓ إِنسٞ وَلَا جَآنّٞ

39. በዚያ ቀን ሰዉም ጂንም ከሐጢአት አይጠየቅም:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

40. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
41 : 55

يُعۡرَفُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ بِسِيمَٰهُمۡ فَيُؤۡخَذُ بِٱلنَّوَٰصِي وَٱلۡأَقۡدَامِ

41. ከሓዲያን በምልክታቸው ይታወቃሉ:: ከዚያ አናቶቻቸውንና እግሮቻቸውን ይያዛሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

42. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
43 : 55

هَٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِي يُكَذِّبُ بِهَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ

43. "ይህች ያቺ አመጸኞች በእርሷ ያስተባብሉባት የነበረችው ገሀነም ናት" (ይባላሉ):: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 55

يَطُوفُونَ بَيۡنَهَا وَبَيۡنَ حَمِيمٍ ءَانٖ

44. በእርሷና በጣም ሞቃት በሆነ ፍል ውሃ መካከል ይመላለሳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
45 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

45. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
46 : 55

وَلِمَنۡ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ جَنَّتَانِ

46. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታዉም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁሉ ሁለት ገነቶች አሉት፡ info
التفاسير:

external-link copy
47 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

47. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
48 : 55

ذَوَاتَآ أَفۡنَانٖ

48. የቀንዘሎች ባለቤቶች የሆኑ ገነቶች፤ info
التفاسير:

external-link copy
49 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

49. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
50 : 55

فِيهِمَا عَيۡنَانِ تَجۡرِيَانِ

50. በሁለቱ ውስጥ የሚፈሱ ሁለት ምንጮች አሉ፤ info
التفاسير:

external-link copy
51 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

51. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
52 : 55

فِيهِمَا مِن كُلِّ فَٰكِهَةٖ زَوۡجَانِ

52. በሁለቱ ውስጥ ከየፍራፍሬው ሁለት ዓይነቶች (እርጥብና ደረቅ) አሉ፤ info
التفاسير:

external-link copy
53 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

53. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
54 : 55

مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ فُرُشِۭ بَطَآئِنُهَا مِنۡ إِسۡتَبۡرَقٖۚ وَجَنَى ٱلۡجَنَّتَيۡنِ دَانٖ

54. የውስጥ ጉዝጉዛቸው ከወፍራም ሀር በሆኑ ምንጣፎች ላይ የተመቻቸ ሲሆን ይንፈላሰሳሉ፤ የሁለቱም ገነቶች ፍሬ ለለቃሚ ቅርብ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
55 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

55. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
56 : 55

فِيهِنَّ قَٰصِرَٰتُ ٱلطَّرۡفِ لَمۡ يَطۡمِثۡهُنَّ إِنسٞ قَبۡلَهُمۡ وَلَا جَآنّٞ

56. በውስጣቸው ከባሎቻቸው በፊት ሰዉም ጂንም ያልዳሰሳቸው (ያልገሰሳቸው) ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ ብቻ) አሳጣሪዎች ሴቶች አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
57 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

57. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
58 : 55

كَأَنَّهُنَّ ٱلۡيَاقُوتُ وَٱلۡمَرۡجَانُ

58. ልክ የያቁትንና የመርጃንን ማዕድናት ይመስላሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
59 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

59. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
60 : 55

هَلۡ جَزَآءُ ٱلۡإِحۡسَٰنِ إِلَّا ٱلۡإِحۡسَٰنُ

60. የበጎ ስራ ዋጋ በጎ እንጂ ሌላ ነውን? info
التفاسير:

external-link copy
61 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

61. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
62 : 55

وَمِن دُونِهِمَا جَنَّتَانِ

62. ከሁለት ገነቶች ሌላም ሁለት ገነቶች አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
63 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

63. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
64 : 55

مُدۡهَآمَّتَانِ

64. ከልምላሜዎቻቸው የተነሳ ወደ ጥቁረት ያዘነበሉ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

65. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
66 : 55

فِيهِمَا عَيۡنَانِ نَضَّاخَتَانِ

66. በውስጣቸው ሁለት የሚንፏፉ ምንጮች አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

67. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
68 : 55

فِيهِمَا فَٰكِهَةٞ وَنَخۡلٞ وَرُمَّانٞ

68. በውስጣቸው ፍራፍሬ ዘንባባና ሩማን አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
69 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

69. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
70 : 55

فِيهِنَّ خَيۡرَٰتٌ حِسَانٞ

70. በውስጣቸው ጸባየ መልካሞችና መልከ ውብ ሴቶች አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
71 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

71. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
72 : 55

حُورٞ مَّقۡصُورَٰتٞ فِي ٱلۡخِيَامِ

72. በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቸቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የሆኑ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
73 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

73. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
74 : 55

لَمۡ يَطۡمِثۡهُنَّ إِنسٞ قَبۡلَهُمۡ وَلَا جَآنّٞ

74. ከእነርሱ በፊት ሰዉም ሆነ ጃን አልዳሰሳቸዉም (አልገሰሳቸዉም) :: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

75. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
76 : 55

مُتَّكِـِٔينَ عَلَىٰ رَفۡرَفٍ خُضۡرٖ وَعَبۡقَرِيٍّ حِسَانٖ

76. በሚያረገርጉ አረንጓዴ ምንጣፎችና በሚያማምሩ ስጋጃዎች ላይ የተደላደሉ ሲሆኑ ይቀመጣሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
77 : 55

فَبِأَيِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

77. (ሰዎችና ጋኔኖች ሆይ!) ከጌታችሁ ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? info
التفاسير:

external-link copy
78 : 55

تَبَٰرَكَ ٱسۡمُ رَبِّكَ ذِي ٱلۡجَلَٰلِ وَٱلۡإِكۡرَامِ

78. የግርማ የመከበር ባለቤት የሆነው ጌታህ ስም ላቀ። info
التفاسير: