Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija

Puslapio numeris: 86:77 close

external-link copy
52 : 4

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُۖ وَمَن يَلۡعَنِ ٱللَّهُ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ نَصِيرًا

52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ አላህ የረገማቸው ናቸው:: አላህ የረገመውን ደግሞ ለርሱ ፈጽሞ ረዳት አታገኝለትም። info
التفاسير:

external-link copy
53 : 4

أَمۡ لَهُمۡ نَصِيبٞ مِّنَ ٱلۡمُلۡكِ فَإِذٗا لَّا يُؤۡتُونَ ٱلنَّاسَ نَقِيرًا

53. በእውነቱ ለእነርሱ ከንግስናው ፈንታ አላቸውን? ያን ጊዜማ ለሰዎች በተምር ፍሬ ላይ ያለችውን ነጥብ ያህል እንኳን አይሰጡም ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
54 : 4

أَمۡ يَحۡسُدُونَ ٱلنَّاسَ عَلَىٰ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦۖ فَقَدۡ ءَاتَيۡنَآ ءَالَ إِبۡرَٰهِيمَ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَءَاتَيۡنَٰهُم مُّلۡكًا عَظِيمٗا

54. ይልቁንም ለሰዎች አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ላይ ይመቀኛሉን? ለኢብራሂምም ቤተሰቦች መጽሐፍንና ጥበብን በእርግጥ ሰጠን:: ታላቅንም ንግስናን ሰጠናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
55 : 4

فَمِنۡهُم مَّنۡ ءَامَنَ بِهِۦ وَمِنۡهُم مَّن صَدَّ عَنۡهُۚ وَكَفَىٰ بِجَهَنَّمَ سَعِيرًا

55. ከነሱም (ከአይሁድ) መካከል በነብዩ ሙሐመድ ያመነ አለ:: ከእነርሱም ከዚህ እምነት ያፈገፈገ አለ። አቃጣይነት በገሀነም በቃ። info
التفاسير:

external-link copy
56 : 4

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا سَوۡفَ نُصۡلِيهِمۡ نَارٗا كُلَّمَا نَضِجَتۡ جُلُودُهُم بَدَّلۡنَٰهُمۡ جُلُودًا غَيۡرَهَا لِيَذُوقُواْ ٱلۡعَذَابَۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَزِيزًا حَكِيمٗا

56. እነዚያን በተዐምራታችን የካዱትን ሁሉ በእርግጥ እሳትን እናስገባቸዋለን:: ስቃይን እንዲቀምሱም ቆዳዎቻቸው በተቃጠሉ ቁጥር ሌሎችን ቆዳዎች እንለውጥላቸዋለን:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
57 : 4

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ سَنُدۡخِلُهُمۡ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۖ لَّهُمۡ فِيهَآ أَزۡوَٰجٞ مُّطَهَّرَةٞۖ وَنُدۡخِلُهُمۡ ظِلّٗا ظَلِيلًا

57. እነዚያ በአላህ አንድነት ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ከስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ በእርግጥ እናስገባቸዋለን:: ለእነርሱ በውስጧ ንጹህ ሚስቶችም አሏቸው:: የምታስጠልልን ጥላም እናስገባቸዋለን:: info
التفاسير:

external-link copy
58 : 4

۞ إِنَّ ٱللَّهَ يَأۡمُرُكُمۡ أَن تُؤَدُّواْ ٱلۡأَمَٰنَٰتِ إِلَىٰٓ أَهۡلِهَا وَإِذَا حَكَمۡتُم بَيۡنَ ٱلنَّاسِ أَن تَحۡكُمُواْ بِٱلۡعَدۡلِۚ إِنَّ ٱللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِۦٓۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ سَمِيعَۢا بَصِيرٗا

58. አላህ አደራዎችን ወደ የባለቤቶቻቸው እንድታደርሱና በሰዎች መካከል በፈረዳችሁ ጊዜም በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል:: አላህ በእርሱ የሚገስፃችሁ ነገር ምን ያምር ነው! አላህ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
59 : 4

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَ وَأُوْلِي ٱلۡأَمۡرِ مِنكُمۡۖ فَإِن تَنَٰزَعۡتُمۡ فِي شَيۡءٖ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمۡ تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡيَوۡمِ ٱلۡأٓخِرِۚ ذَٰلِكَ خَيۡرٞ وَأَحۡسَنُ تَأۡوِيلًا

59. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ታዘዙ:: መልዕክተኛውን እና ከመካከላችሁም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ:: በማንኛዉም ነገር ብትከራከሩም በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ከሆናችሁ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው መልሱት:: ይህ የተሻለ እና መጨረሻዉም ያማረ ነው:: info
التفاسير: