Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Afrikos akademija

Puslapio numeris:close

external-link copy
49 : 2

وَإِذۡ نَجَّيۡنَٰكُم مِّنۡ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ يَسُومُونَكُمۡ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ يُذَبِّحُونَ أَبۡنَآءَكُمۡ وَيَسۡتَحۡيُونَ نِسَآءَكُمۡۚ وَفِي ذَٰلِكُم بَلَآءٞ مِّن رَّبِّكُمۡ عَظِيمٞ

49. ከፈርዖን ቤተሰቦች (ከጎሳዎቹ) ብርቱን ቅጣት የሚያቀምሷችሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁን የሚያርዱና ሴቶቻችሁን የሚተዉ ሲሆኑ ከእነርሱ ባዳንናችሁ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። ያ ክስተት ከጌታችሁ ለእናንተ ታላቅ ፈተና ነበር። info
التفاسير:

external-link copy
50 : 2

وَإِذۡ فَرَقۡنَا بِكُمُ ٱلۡبَحۡرَ فَأَنجَيۡنَٰكُمۡ وَأَغۡرَقۡنَآ ءَالَ فِرۡعَوۡنَ وَأَنتُمۡ تَنظُرُونَ

50. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) በእናንተ ምክንያት ባህሩን በከፈልን ጊዜ የሆነውን ታሪክም አስታውሱ:: ወዲያውኑም አዳንናችሁ:: የፈርዖንንም ቤተሰቦች ዓይናችሁ እያየ አሰመጥናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
51 : 2

وَإِذۡ وَٰعَدۡنَا مُوسَىٰٓ أَرۡبَعِينَ لَيۡلَةٗ ثُمَّ ٱتَّخَذۡتُمُ ٱلۡعِجۡلَ مِنۢ بَعۡدِهِۦ وَأَنتُمۡ ظَٰلِمُونَ

51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳ የአርባ ሌሊትን ቀጠሮ ከእኛ በወሰደበት ጊዜ (የሆነውን ታሪክ ለህዝቦችህ አስታውስ):: ከዚያም ከእርሱ (መሄድ) በኋላ እናንተ ራሳችሁን በዳዩች ስትሆኑ ወይፈንን አምላክ አደረጋችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
52 : 2

ثُمَّ عَفَوۡنَا عَنكُم مِّنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

52. (ቢሆንም) ከዚያ በኋላ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ምህረትን አደርግን:: info
التفاسير:

external-link copy
53 : 2

وَإِذۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡفُرۡقَانَ لَعَلَّكُمۡ تَهۡتَدُونَ

53. (እናንተ የኢስራኢል ልጆች ሆይ! ወደ ትክክለኛው መንገድ) ትመሩ ዘንድ ለሙሳ እውነትንና ውሸትን የሚለይን መጽሐፍ በሰጠነው ጊዜ (የዋልንላችሁን ውለታ አስታውሱ):: info
التفاسير:

external-link copy
54 : 2

وَإِذۡ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوۡمِهِۦ يَٰقَوۡمِ إِنَّكُمۡ ظَلَمۡتُمۡ أَنفُسَكُم بِٱتِّخَاذِكُمُ ٱلۡعِجۡلَ فَتُوبُوٓاْ إِلَىٰ بَارِئِكُمۡ فَٱقۡتُلُوٓاْ أَنفُسَكُمۡ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ عِندَ بَارِئِكُمۡ فَتَابَ عَلَيۡكُمۡۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ

54. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ሙሳ ለሕዝቦቹ (እንዲህ) ባለም ጊዜ የዋልነውን ውለታ አስታውሱ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን አምላክ በማድረጋችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ:: በመሆኑም ወደ ፈጣሪያችሁ ተመለሱ:: ከመካከላችሁ ወንጀለኛ ወገኖቻችሁን ግደሉ:: ይሃችሁ ድርጊት በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለእንናተ በላጭ ነው። በእናንተም ላይ ምህረቱን አወረደ:: እነሆ እርሱ (አላህ) ጸጸትን ተቀባይ ምህረተኛ አዛኝ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
55 : 2

وَإِذۡ قُلۡتُمۡ يَٰمُوسَىٰ لَن نُّؤۡمِنَ لَكَ حَتَّىٰ نَرَى ٱللَّهَ جَهۡرَةٗ فَأَخَذَتۡكُمُ ٱلصَّٰعِقَةُ وَأَنتُمۡ تَنظُرُونَ

55. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) «ሙሳ ሆይ! አላህን በይፋ እስከምናይ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም።» ባላችሁ ጊዜ (የሆነውን ታሪክ አስታውሱ)። እናንተም በዓይናችሁ እየተመለከታችሁ መብረቅ መታችሁ። info
التفاسير:

external-link copy
56 : 2

ثُمَّ بَعَثۡنَٰكُم مِّنۢ بَعۡدِ مَوۡتِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ

56. ከዚያም ታመሰግኑ ዘንድ ከሞታችሁ በኋላ አስነሳናችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 2

وَظَلَّلۡنَا عَلَيۡكُمُ ٱلۡغَمَامَ وَأَنزَلۡنَا عَلَيۡكُمُ ٱلۡمَنَّ وَٱلسَّلۡوَىٰۖ كُلُواْ مِن طَيِّبَٰتِ مَا رَزَقۡنَٰكُمۡۚ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ

57. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) በናንተ ላይ ዳመናን አጠለልን:: እንደ ነጭ ማር ያለ «መንን» እና ድርጭትን ለምግብነት አወረድን:: «ከሰጠናችሁም ጣፋጮችን።» ብሉ አልን:: እኛን አልበደሉንም:: ነፍሶቻቸውን ግን ይበድሉ ነበር:: info
التفاسير: