Kilniojo Korano reikšmių vertimas - Vertimas į amharų k. - Muchamed Sadik

አል መዓሪጅ

external-link copy
1 : 70

سَأَلَ سَآئِلُۢ بِعَذَابٖ وَاقِعٖ

ወዳቂ ከኾነው ቅጣት ጠያቂ ጠየቀ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 70

لِّلۡكَٰفِرِينَ لَيۡسَ لَهُۥ دَافِعٞ

በከሓዲዎች ላይ (ወዳቂ ከኾነው) ለእርሱ መላሽ የለውም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
3 : 70

مِّنَ ٱللَّهِ ذِي ٱلۡمَعَارِجِ

የ(ሰማያት) መሰላሎች ባለቤት ከኾነው አላህ (መላሽ የለውም)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 70

تَعۡرُجُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ إِلَيۡهِ فِي يَوۡمٖ كَانَ مِقۡدَارُهُۥ خَمۡسِينَ أَلۡفَ سَنَةٖ

መላእክቱና መንፈሱም ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደእርሱ ያርጋሉ፤ (ይወጣሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 70

فَٱصۡبِرۡ صَبۡرٗا جَمِيلًا

መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
6 : 70

إِنَّهُمۡ يَرَوۡنَهُۥ بَعِيدٗا

እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 70

وَنَرَىٰهُ قَرِيبٗا

እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 70

يَوۡمَ تَكُونُ ٱلسَّمَآءُ كَٱلۡمُهۡلِ

ሰማይ እንደ ዘይት አተላ በምትኾንበት ቀን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 70

وَتَكُونُ ٱلۡجِبَالُ كَٱلۡعِهۡنِ

ጋራዎችም በተለያዩ ቀለማት እንደ ተነከረ ሱፍ (ነፋስ እንደሚያበረው) በሚኾኑበት ቀን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 70

وَلَا يَسۡـَٔلُ حَمِيمٌ حَمِيمٗا

ዘመድም ዘመድን በማይጠይቅበት ቀን፤ (መላሽ የለውም)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 70

يُبَصَّرُونَهُمۡۚ يَوَدُّ ٱلۡمُجۡرِمُ لَوۡ يَفۡتَدِي مِنۡ عَذَابِ يَوۡمِئِذِۭ بِبَنِيهِ

(ዘመዶቻቸውን) ያዩዋቸዋል፡፡ አመጸኛው ከዚያ ቀን ስቃይ (ነፍሱን) በልጆቹ ሊበዥ ይመኛል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 70

وَصَٰحِبَتِهِۦ وَأَخِيهِ

በሚስቱም በወንድሙም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 70

وَفَصِيلَتِهِ ٱلَّتِي تُـٔۡوِيهِ

በዚያችም በምታስጠጋው ጎሳው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 70

وَمَن فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا ثُمَّ يُنجِيهِ

በምድርም ላይ ባለው ሁሉ (ሊበዥ) ከዚያም ሊያድነው (ይመኛል)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 70

كَلَّآۖ إِنَّهَا لَظَىٰ

ይተው! እርሷ (እሳቲቱ) ለዟ ናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
16 : 70

نَزَّاعَةٗ لِّلشَّوَىٰ

የራስን ቅል ቆዳ የምትሞሽልቅ ስትኾን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
17 : 70

تَدۡعُواْ مَنۡ أَدۡبَرَ وَتَوَلَّىٰ

(ከእምነት) የዞረንና የሸሸን ሰው (ወደእርሷ) ትጠራለች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
18 : 70

وَجَمَعَ فَأَوۡعَىٰٓ

ገንዘብን የሰበሰበንና (ዘካውን ሳይሰጥ) የቆጠረንም፤ (ትጠራለች)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
19 : 70

۞ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ خُلِقَ هَلُوعًا

ሰው ቅጠ ቢስ ኾኖ ተፈጠረ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
20 : 70

إِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ جَزُوعٗا

ክፉ ነገር ባገኘው ጊዜ ብስጪተኛ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
21 : 70

وَإِذَا مَسَّهُ ٱلۡخَيۡرُ مَنُوعًا

መልካምም ነገር (ድሎት) ባገኘ ጊዜ ከልካይ (ኾኖ ተፈጠረ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
22 : 70

إِلَّا ٱلۡمُصَلِّينَ

ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
23 : 70

ٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ دَآئِمُونَ

እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
24 : 70

وَٱلَّذِينَ فِيٓ أَمۡوَٰلِهِمۡ حَقّٞ مَّعۡلُومٞ

እነዚያም በገንዘቦቻቸው ላይ የታወቀ መብት ያለባቸው የኾኑት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
25 : 70

لِّلسَّآئِلِ وَٱلۡمَحۡرُومِ

ለለማኝ ከልመና ለሚከለከልም (መብት ያለባቸው የኾኑት)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
26 : 70

وَٱلَّذِينَ يُصَدِّقُونَ بِيَوۡمِ ٱلدِّينِ

እነዚያም በፍርዱ ቀን እውነት የሚሉት (የሚያረጋግጡት)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 70

وَٱلَّذِينَ هُم مِّنۡ عَذَابِ رَبِّهِم مُّشۡفِقُونَ

እነዚያም እነርሱ ከጌታቸው ቅጣት ፈሪዎች የኾኑት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 70

إِنَّ عَذَابَ رَبِّهِمۡ غَيۡرُ مَأۡمُونٖ

የጌታቸው ቅጣት (መምጣቱ) የማያስተማምን ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 70

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِفُرُوجِهِمۡ حَٰفِظُونَ

እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 70

إِلَّا عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِهِمۡ أَوۡ مَا مَلَكَتۡ أَيۡمَٰنُهُمۡ فَإِنَّهُمۡ غَيۡرُ مَلُومِينَ

በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሪያዎች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በእነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 70

فَمَنِ ٱبۡتَغَىٰ وَرَآءَ ذَٰلِكَ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡعَادُونَ

ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው እነዚያ እነሱ ድንበር አላፊዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 70

وَٱلَّذِينَ هُمۡ لِأَمَٰنَٰتِهِمۡ وَعَهۡدِهِمۡ رَٰعُونَ

እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 70

وَٱلَّذِينَ هُم بِشَهَٰدَٰتِهِمۡ قَآئِمُونَ

እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 70

وَٱلَّذِينَ هُمۡ عَلَىٰ صَلَاتِهِمۡ يُحَافِظُونَ

እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 70

أُوْلَٰٓئِكَ فِي جَنَّٰتٖ مُّكۡرَمُونَ

እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
36 : 70

فَمَالِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ قِبَلَكَ مُهۡطِعِينَ

ለእነዚያም ለካዱት ወደ አንተ በኩል አንገቶቻቸውን መዝዘው የሚያተኩሩት ምን አላቸው? info
التفاسير:

external-link copy
37 : 70

عَنِ ٱلۡيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ عِزِينَ

ከቀኝና ከግራ ክፍልፍል ጭፍሮች ሲኾኑ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
38 : 70

أَيَطۡمَعُ كُلُّ ٱمۡرِيٕٖ مِّنۡهُمۡ أَن يُدۡخَلَ جَنَّةَ نَعِيمٖ

ከእነርሱ እያንዳንዱ ሰው የጸጋይቱን ገነት መግባትን ይከጅላልን? info
التفاسير:

external-link copy
39 : 70

كَلَّآۖ إِنَّا خَلَقۡنَٰهُم مِّمَّا يَعۡلَمُونَ

ይከልከል፤ እኛ ከሚያውቁት ነገር (ከፍቶት ጠብታ) ፈጠርናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
40 : 70

فَلَآ أُقۡسِمُ بِرَبِّ ٱلۡمَشَٰرِقِ وَٱلۡمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ

በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
41 : 70

عَلَىٰٓ أَن نُّبَدِّلَ خَيۡرٗا مِّنۡهُمۡ وَمَا نَحۡنُ بِمَسۡبُوقِينَ

ከእነርሱ የተሻለን በመለወጥ ላይ፡፡ እኛም ተሸናፊዎች አይደለንም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
42 : 70

فَذَرۡهُمۡ يَخُوضُواْ وَيَلۡعَبُواْ حَتَّىٰ يُلَٰقُواْ يَوۡمَهُمُ ٱلَّذِي يُوعَدُونَ

ያንንም የሚስፈራሩበትን ቀናቸውን እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው፡፡ ይዋኙ ይጫወቱም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
43 : 70

يَوۡمَ يَخۡرُجُونَ مِنَ ٱلۡأَجۡدَاثِ سِرَاعٗا كَأَنَّهُمۡ إِلَىٰ نُصُبٖ يُوفِضُونَ

ወደ ጣዖቶች እንደሚሽቀዳደሙ ኾነው ከመቃብሮቻቸው ፈጥነው የሚወጡበትን ቀን (እስከሚገናኙ ድረስ ተዋቸው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
44 : 70

خَٰشِعَةً أَبۡصَٰرُهُمۡ تَرۡهَقُهُمۡ ذِلَّةٞۚ ذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمُ ٱلَّذِي كَانُواْ يُوعَدُونَ

ዓይኖቻቸው ያፈሩ ኾነው ውርደት ትሸፍናቸዋለች፡፡ ይህ ቀን ያ ይስፈራሩበት የነበሩት ነው፡፡ info
التفاسير: