وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا

ژمارەی پەڕە:close

external-link copy
11 : 43

وَٱلَّذِي نَزَّلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءَۢ بِقَدَرٖ فَأَنشَرۡنَا بِهِۦ بَلۡدَةٗ مَّيۡتٗاۚ كَذَٰلِكَ تُخۡرَجُونَ

11. ያም ከሰማይ ውሃን በልክ ያወረደላችሁ ነው። በእርሱም (በውሀው) የሞተችውን አገር ህያው አደረግን:: (ሰዎች ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ከየመቃብሮቻችሁ ትወጣለችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 43

وَٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡأَزۡوَٰجَ كُلَّهَا وَجَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلۡفُلۡكِ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ مَا تَرۡكَبُونَ

12. ያም የፍጡር ዓይነቶችን ሁሉ (ጥንድ) አድርጎ የፈጠረ ለእናንተም ከመርከቦችና ከቤት እንሰሳዎች መካከል የምትጋልቧቸውን ያደረገላችሁ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 43

لِتَسۡتَوُۥاْ عَلَىٰ ظُهُورِهِۦ ثُمَّ تَذۡكُرُواْ نِعۡمَةَ رَبِّكُمۡ إِذَا ٱسۡتَوَيۡتُمۡ عَلَيۡهِ وَتَقُولُواْ سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِي سَخَّرَ لَنَا هَٰذَا وَمَا كُنَّا لَهُۥ مُقۡرِنِينَ

13. በጀርባዎቻቸው ላይ እንድትደላደሉ ከዚያም በእርሱ ላይ በተደላደላችሁ ጊዜ የጌታችሁን ጸጋ እንድታስታውሱ፤ እንድትሉም «ይህንን የማንችለው ስንሆን ለእኛ ያገራልን ጌታ ጥራት ተገባው:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 43

وَإِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا لَمُنقَلِبُونَ

14. እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን አላህ ተመላሾች ነን» እንድትሉ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 43

وَجَعَلُواْ لَهُۥ مِنۡ عِبَادِهِۦ جُزۡءًاۚ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَكَفُورٞ مُّبِينٌ

15. ከባሮቹም መካከል ለእርሱ ክፋይን (የተወሰነን) ብቻ አደረጉለት:: ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 43

أَمِ ٱتَّخَذَ مِمَّا يَخۡلُقُ بَنَاتٖ وَأَصۡفَىٰكُم بِٱلۡبَنِينَ

16. አላህ ከሚፈጥረው ፍጡር መካከል ሴቶች ልጆችን ብቻ ለይቶ የራሱ ልጅ አድርጎ ያዘን? (ከዚያም) እናንተን በወንዶች ልጆች መረጣችሁን? (አይደለም)። info
التفاسير:

external-link copy
17 : 43

وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِمَا ضَرَبَ لِلرَّحۡمَٰنِ مَثَلٗا ظَلَّ وَجۡهُهُۥ مُسۡوَدّٗا وَهُوَ كَظِيمٌ

17. አንዳቸዉም ለአር-ረህማን ምሳሌ ባደረገው ነገር (በሴት ልጅ) በተበሰረ ጊዜ በቁጭት የተሞላ ሆኖ ፊቱ ጥቁር ይሆናል:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 43

أَوَمَن يُنَشَّؤُاْ فِي ٱلۡحِلۡيَةِ وَهُوَ فِي ٱلۡخِصَامِ غَيۡرُ مُبِينٖ

18. በጌጣጌጥ ተከልሶ እንዲያድግ የሚደረገውን ክፍል እርሱም ከደካማነቱ የተነሳ በክርክር የማያብራራውን ፍጡር ለይተው ለአላህ ያደርጋሉን? info
التفاسير:

external-link copy
19 : 43

وَجَعَلُواْ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ ٱلَّذِينَ هُمۡ عِبَٰدُ ٱلرَّحۡمَٰنِ إِنَٰثًاۚ أَشَهِدُواْ خَلۡقَهُمۡۚ سَتُكۡتَبُ شَهَٰدَتُهُمۡ وَيُسۡـَٔلُونَ

19. እነዚያን የአር-ረሕማን ቅን ባሮች የሆኑትን መላእክትንም ሴቶች አደረጓቸው። ለመሆኑ እነርሱ መላእክት ሲፈጠሩ አብረው ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትፃፋለች:: ስለ እርሷም ይጠየቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 43

وَقَالُواْ لَوۡ شَآءَ ٱلرَّحۡمَٰنُ مَا عَبَدۡنَٰهُمۗ مَّا لَهُم بِذَٰلِكَ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِنۡ هُمۡ إِلَّا يَخۡرُصُونَ

20. «አር-ረሕማንም በፈለገ ኖሮ ባልተገዛናቸው ነበር» አሉ። ለእነርሱም በዚህ ምንም እውቀት የላቸዉም፤ እነርሱ የሚዋሹ ህዝቦች እንጂ ሌላ አይደሉም። info
التفاسير:

external-link copy
21 : 43

أَمۡ ءَاتَيۡنَٰهُمۡ كِتَٰبٗا مِّن قَبۡلِهِۦ فَهُم بِهِۦ مُسۡتَمۡسِكُونَ

21. ከእርሱ (ቁርኣን) በፊት መጽሐፍን ሰጠናቸውና እሱን አጥብቀው የያዙ ናቸውን? info
التفاسير:

external-link copy
22 : 43

بَلۡ قَالُوٓاْ إِنَّا وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا عَلَىٰٓ أُمَّةٖ وَإِنَّا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُّهۡتَدُونَ

22. ከቶውንም «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘናቸው:: እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተመሪዎች ነን» አሉ እንጂ። info
التفاسير: