وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - ئەکادیمیای ئەفریقا

ژمارەی پەڕە:close

external-link copy
25 : 14

تُؤۡتِيٓ أُكُلَهَا كُلَّ حِينِۭ بِإِذۡنِ رَبِّهَاۗ وَيَضۡرِبُ ٱللَّهُ ٱلۡأَمۡثَالَ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ

25. ፍሬዋን (ምግቧን) በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች:: አላህም ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 14

وَمَثَلُ كَلِمَةٍ خَبِيثَةٖ كَشَجَرَةٍ خَبِيثَةٍ ٱجۡتُثَّتۡ مِن فَوۡقِ ٱلۡأَرۡضِ مَا لَهَا مِن قَرَارٖ

26. የመጥፎ ቃል ምሳሌ ከምድር በላይ የተገረሰሰች ለእርሷ ምንም መደላደል የሌላት እንደ ሆነች መጥፎ ዛፍ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 14

يُثَبِّتُ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ بِٱلۡقَوۡلِ ٱلثَّابِتِ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِۖ وَيُضِلُّ ٱللَّهُ ٱلظَّٰلِمِينَۚ وَيَفۡعَلُ ٱللَّهُ مَا يَشَآءُ

27. አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት ሆነ በመጨረሻይቱም በመቃብር በተረጋገጠው ቃል (በሸሀዳ) ላይ ያደርጋቸዋል (ያጸናቸዋል):: ከሓዲያንንም አላህ ያሳስታቸዋል፤ አላህም የሚሻውን ይሰራልና:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 14

۞ أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ بَدَّلُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ كُفۡرٗا وَأَحَلُّواْ قَوۡمَهُمۡ دَارَ ٱلۡبَوَارِ

28. ወደ እነዚያ የአላህን ጸጋ በክህደት ወደ ለወጡትና ህዝቦቻቸውን በጥፋት ሀገር ወዳሰፈሩት (ወደ ቁረይሾች) አላየህምን? (አልተመለከትክምን?) info
التفاسير:

external-link copy
29 : 14

جَهَنَّمَ يَصۡلَوۡنَهَاۖ وَبِئۡسَ ٱلۡقَرَارُ

29. ሀገሪቱም የሚገቡባት ስትሆን ገሀነም ናት:: መርጊያነቷ ምንኛ ትከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
30 : 14

وَجَعَلُواْ لِلَّهِ أَندَادٗا لِّيُضِلُّواْ عَن سَبِيلِهِۦۗ قُلۡ تَمَتَّعُواْ فَإِنَّ مَصِيرَكُمۡ إِلَى ٱلنَّارِ

30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአላህ ከመንገዱ ያሳስቱ ዘንድ ባላንጣዎችን አደረጉለት:: (ሙሐመድ ሆይ!) «ጥቂትን ተጠቀሙ መመለሻችሁም ወደ እሳት ነው።» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
31 : 14

قُل لِّعِبَادِيَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ يُقِيمُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُنفِقُواْ مِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ سِرّٗا وَعَلَانِيَةٗ مِّن قَبۡلِ أَن يَأۡتِيَ يَوۡمٞ لَّا بَيۡعٞ فِيهِ وَلَا خِلَٰلٌ

31. መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ለእነዚያ ላመኑት ባሮቼ ሽያጭና ወዳጅነት የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ሶላትን በደንቡ እንዲሰግዱ፤ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጢርም ሆነ በግልጽ እንዲለግሱም ንገራቸው። info
التفاسير:

external-link copy
32 : 14

ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَأَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَخۡرَجَ بِهِۦ مِنَ ٱلثَّمَرَٰتِ رِزۡقٗا لَّكُمۡۖ وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلۡفُلۡكَ لِتَجۡرِيَ فِي ٱلۡبَحۡرِ بِأَمۡرِهِۦۖ وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلۡأَنۡهَٰرَ

32. አላህ ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ከሰማይ ዳመናም ውሃን ያወረደ፤ በእርሱም ከፍሬዎች ሁሉ ለእናንተ ሲሳይን ያወጣላችሁ፤ መርከቦችንም በፈቃዱ በባህር ላይ ይንሳፈፉ ዘንድ ለእናንተ ያገራ፤ ወንዞችንም ለናንተ ያገራ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 14

وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ دَآئِبَيۡنِۖ وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ

33. ጸሓይንና ጨረቃንም ዘወትር ሒያጆች ሲሆኑ ለእናንተ የገራ፤ ሌሊትንና ቀንንም ለእናንተ የገራላችሁ ነው:: info
التفاسير: