وه‌رگێڕانی ماناكانی قورئانی پیرۆز - وەرگێڕاوی ئەمهەری - محمد سادق

አል ቀድር

external-link copy
1 : 97

إِنَّآ أَنزَلۡنَٰهُ فِي لَيۡلَةِ ٱلۡقَدۡرِ

እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡ {1} info

{1} ይህች ሌሊት በሮመዳን ውስጥ ትገኛለች ። በመጨረሻዎቹ አስርት ሌሊቶች ከነሱም በኢተጋማሽ ሌሊቶች በ21፣ 23፣ 25፣ 27፣ 29 ውስጥ ትገኛለች ። እርሷን በሶላትና በኢባዳ ያሳለፋ ሰው ያለፈው ሃጥአቱ ምህረት ይደረግለታል።

التفاسير:

external-link copy
2 : 97

وَمَآ أَدۡرَىٰكَ مَا لَيۡلَةُ ٱلۡقَدۡرِ

መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? info
التفاسير:

external-link copy
3 : 97

لَيۡلَةُ ٱلۡقَدۡرِ خَيۡرٞ مِّنۡ أَلۡفِ شَهۡرٖ

መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 97

تَنَزَّلُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ فِيهَا بِإِذۡنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمۡرٖ

በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 97

سَلَٰمٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطۡلَعِ ٱلۡفَجۡرِ

እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡ info
التفاسير: