ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
109 : 5

۞ يَوۡمَ يَجۡمَعُ ٱللَّهُ ٱلرُّسُلَ فَيَقُولُ مَاذَآ أُجِبۡتُمۡۖ قَالُواْ لَا عِلۡمَ لَنَآۖ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّٰمُ ٱلۡغُيُوبِ

109. (መልዕክተኛችን ሆይ!) አላህ መልዕክተኞቹን ሰብስቦ እንዲህ ባለ ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ፡- «ሕዝቦቻችሁ ምን መለሱላችሁ?» መልዕክተኞቹም: «እኛ እውቀቱ የለንም:: ሩቅ ሚስጥሮችን ሁሉ የምታውቀው አንተው ነህ።» ይላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
110 : 5

إِذۡ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبۡنَ مَرۡيَمَ ٱذۡكُرۡ نِعۡمَتِي عَلَيۡكَ وَعَلَىٰ وَٰلِدَتِكَ إِذۡ أَيَّدتُّكَ بِرُوحِ ٱلۡقُدُسِ تُكَلِّمُ ٱلنَّاسَ فِي ٱلۡمَهۡدِ وَكَهۡلٗاۖ وَإِذۡ عَلَّمۡتُكَ ٱلۡكِتَٰبَ وَٱلۡحِكۡمَةَ وَٱلتَّوۡرَىٰةَ وَٱلۡإِنجِيلَۖ وَإِذۡ تَخۡلُقُ مِنَ ٱلطِّينِ كَهَيۡـَٔةِ ٱلطَّيۡرِ بِإِذۡنِي فَتَنفُخُ فِيهَا فَتَكُونُ طَيۡرَۢا بِإِذۡنِيۖ وَتُبۡرِئُ ٱلۡأَكۡمَهَ وَٱلۡأَبۡرَصَ بِإِذۡنِيۖ وَإِذۡ تُخۡرِجُ ٱلۡمَوۡتَىٰ بِإِذۡنِيۖ وَإِذۡ كَفَفۡتُ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ عَنكَ إِذۡ جِئۡتَهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۡهُمۡ إِنۡ هَٰذَآ إِلَّا سِحۡرٞ مُّبِينٞ

110. አላህ እንዲህ በሚልበት ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ላንተና ለእናትህ የዋልኩላችሁን ውለታ አስታውስ:: በሩሀል ቁዱስ (በጅብሪል) አጠነከርኩህ:: በሕጻንነትህም አድገህም ሰዎችን ማናገር ቻልክ። መጽሐፉንና ጥበብን ተውራትንና ኢንጂልንም አስተማርኩህ:: ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ዓይነት በፈቃዴ መሥራት ቻልክ:: በሷ ውስጥ ነፈህ:: በፈቃዴም እውነተኛ በራሪ ሆነች:: እውር ሆኖ የተወለደንና ለምጻምን በፈቃዴ መፈወስ ቻልክ:: ሟችንም በፈቃዴ አስነሳህ:: የኢስራኢልንም ልጆች ግልጽ መረጃ ባመጣህላቸው ጊዜ ሊያጠቁህ ሲያስቡ አቀብኩልህ:: ከመካከላቸዉም እነዚያ በአላህ የካዱት ‹ይህ ግልጽ ድግምት ነው› አሉ:: ይህን ሁሉ ውለታዬን አስታውስ:: info
التفاسير:

external-link copy
111 : 5

وَإِذۡ أَوۡحَيۡتُ إِلَى ٱلۡحَوَارِيِّـۧنَ أَنۡ ءَامِنُواْ بِي وَبِرَسُولِي قَالُوٓاْ ءَامَنَّا وَٱشۡهَدۡ بِأَنَّنَا مُسۡلِمُونَ

111. «ለሃዋሪያቱም፡- ‹በእኔና በመልዕክተኛዬ እመኑ።› የሚል ራዕይ በገለጽኩ ጊዜም የሆነውን አስታውስ። ‹አምነናል:: እኛ ሙስሊሞች ለመሆናችን ምስክር ሁን› አሉም። info
التفاسير:

external-link copy
112 : 5

إِذۡ قَالَ ٱلۡحَوَارِيُّونَ يَٰعِيسَى ٱبۡنَ مَرۡيَمَ هَلۡ يَسۡتَطِيعُ رَبُّكَ أَن يُنَزِّلَ عَلَيۡنَا مَآئِدَةٗ مِّنَ ٱلسَّمَآءِۖ قَالَ ٱتَّقُواْ ٱللَّهَ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

112. «ሃዋሪያቶቹም፡- ‹የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ጌታህ ከሰማይ ማዕድ ሊያወርድልን ይቻላልን?› ባሉ ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ዒሳም፡-‹ትክክለኛ አማኞች ከሆናችሁ አላህን ብቻ ፍሩ።› አለ። info
التفاسير:

external-link copy
113 : 5

قَالُواْ نُرِيدُ أَن نَّأۡكُلَ مِنۡهَا وَتَطۡمَئِنَّ قُلُوبُنَا وَنَعۡلَمَ أَن قَدۡ صَدَقۡتَنَا وَنَكُونَ عَلَيۡهَا مِنَ ٱلشَّٰهِدِينَ

113. «‹ከእርሱ ልንመገብ ልቦቻችንም እርካታን ይጎናጸፉ ዘንድ ብቻ ነው ይህን የጠየቅነው:: የነገርከንም ተጨባጭ እውነት መሆኑን ልናውቅና ለዚህም መስካሪዎች ለመሆን ፈልገን ነው።› አሉ:: info
التفاسير: