ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
78 : 5

لُعِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِنۢ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ عَلَىٰ لِسَانِ دَاوُۥدَ وَعِيسَى ٱبۡنِ مَرۡيَمَۚ ذَٰلِكَ بِمَا عَصَواْ وَّكَانُواْ يَعۡتَدُونَ

78. ከኢስራኢል ልጆች መካከል እነዚያ በአላህ የካዱት በዳውድና በመርየም ልጅ ዒሳ አንደበት ተረገሙ:: ይህም የአላህን ትዕዛዝ በመጣሳቸውና ወሰን የሚያልፉ በመሆናቸው ነው። info
التفاسير:

external-link copy
79 : 5

كَانُواْ لَا يَتَنَاهَوۡنَ عَن مُّنكَرٖ فَعَلُوهُۚ لَبِئۡسَ مَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ

79. ይሰሩት ከነበረው መጥፎ ነገር አይከላከሉም ነበር:: ይሰሩት የነበረው ነገር በእርግጥ ከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
80 : 5

تَرَىٰ كَثِيرٗا مِّنۡهُمۡ يَتَوَلَّوۡنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۚ لَبِئۡسَ مَا قَدَّمَتۡ لَهُمۡ أَنفُسُهُمۡ أَن سَخِطَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ وَفِي ٱلۡعَذَابِ هُمۡ خَٰلِدُونَ

80. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ ብዙዎቹን ከእነዚያ ከካዱት ጋር ሲወዳጁ ታያለህ:: በእነርሱ ላይ አላህ በመቆጣቱ ለእነርሱ ነፍሶቻቸው ያስቀደሙት ስራ በጣም ከፋ። እነርሱም በቅጣቱ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው። info
التفاسير:

external-link copy
81 : 5

وَلَوۡ كَانُواْ يُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلنَّبِيِّ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيۡهِ مَا ٱتَّخَذُوهُمۡ أَوۡلِيَآءَ وَلَٰكِنَّ كَثِيرٗا مِّنۡهُمۡ فَٰسِقُونَ

81. በአላህና በነቢዩ ወደርሱም በተወረደው ቁርኣን የሚያምኑ በኾኑ ኖሮ ወዳጆች አድርገው ባልያዙዋቸው ነበር፡፡ ግን ከእነርሱ ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
82 : 5

۞ لَتَجِدَنَّ أَشَدَّ ٱلنَّاسِ عَدَٰوَةٗ لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱلۡيَهُودَ وَٱلَّذِينَ أَشۡرَكُواْۖ وَلَتَجِدَنَّ أَقۡرَبَهُم مَّوَدَّةٗ لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱلَّذِينَ قَالُوٓاْ إِنَّا نَصَٰرَىٰۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّ مِنۡهُمۡ قِسِّيسِينَ وَرُهۡبَانٗا وَأَنَّهُمۡ لَا يَسۡتَكۡبِرُونَ

82. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አይሁድና እነዚያ በአላህ ያጋሩት ለእነዚያ ላመኑት በጠላትነት ከሌሎች ሁሉ የበረቱ ሆነው ታገኛቸዋለህ:: ከእነርሱ መካከል እነዚያ «እኛ ክርስቲያኖች ነን።» ያሉትን ደግሞ ለእነዚያ ላመኑት በወዳጅነት ይበልጥ የቀረቧቸው ሆነው ታገኛቸዋለህ:: ይህም ከእነርሱ መካከል ቀሳውስትና መነኮሳት በመኖራቸውና እነርሱም የማይኮሩ በመሆናቸው ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
83 : 5

وَإِذَا سَمِعُواْ مَآ أُنزِلَ إِلَى ٱلرَّسُولِ تَرَىٰٓ أَعۡيُنَهُمۡ تَفِيضُ مِنَ ٱلدَّمۡعِ مِمَّا عَرَفُواْ مِنَ ٱلۡحَقِّۖ يَقُولُونَ رَبَّنَآ ءَامَنَّا فَٱكۡتُبۡنَا مَعَ ٱلشَّٰهِدِينَ

83. ወደ መልዕክተኛው የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከመረዳታቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ:: ይላሉም: «ጌታችን ሆይ! ባንተ አምነናልና ከመስካሪዎች ጋር ፃፈን። info
التفاسير: