ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
67 : 40

هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ مِنۡ عَلَقَةٖ ثُمَّ يُخۡرِجُكُمۡ طِفۡلٗا ثُمَّ لِتَبۡلُغُوٓاْ أَشُدَّكُمۡ ثُمَّ لِتَكُونُواْ شُيُوخٗاۚ وَمِنكُم مَّن يُتَوَفَّىٰ مِن قَبۡلُۖ وَلِتَبۡلُغُوٓاْ أَجَلٗا مُّسَمّٗى وَلَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ

67. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ (አላህ) ያ ከዐፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው:: ከዚያም ህፃን አድርጎ ያወጣችኋል:: ከዚያም ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፤ ከዚያም ሽማግሌዎች ትሆኑ ዘንድ ያቆያችኋል:: ከናንተም ውስጥ ከዚህ በፊት የሚሞት አለ:: ይህንንም ያደረገው ኑራችሁ የተወሰነ ጊዜም ልትደርሱ ታውቁም ዘንድ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
68 : 40

هُوَ ٱلَّذِي يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ فَإِذَا قَضَىٰٓ أَمۡرٗا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

68. እርሱ (አላህ) ያ ህያው የሚያደርግና የሚያሞትም ነው:: አንዳችን ነገር በሻም ጊዜ ለእርሱ የሚለው ሁን ነው ወዲያዉም ይሆናል:: info
التفاسير:

external-link copy
69 : 40

أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِيٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ أَنَّىٰ يُصۡرَفُونَ

69.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ በአላህ አናቅጽ ወደሚከራከሩት ከእምነት እንዴት እንደሚመለሱ አታይምን? info
التفاسير:

external-link copy
70 : 40

ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِٱلۡكِتَٰبِ وَبِمَآ أَرۡسَلۡنَا بِهِۦ رُسُلَنَاۖ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ

70. ወደ እነዚያ በመጽሐፉ በዚያም መልዕክተኞቻችንን በእርሱ በላክንበት ወዳስተባበሉበት አታይምን? ወደፊትም ያውቃሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
71 : 40

إِذِ ٱلۡأَغۡلَٰلُ فِيٓ أَعۡنَٰقِهِمۡ وَٱلسَّلَٰسِلُ يُسۡحَبُونَ

71. እንዘዝላዎቹና ሰንሰለቶቹ በአንገቶቻቸው ላይ በተደረጉ ጊዜ (በእርሷ) ይጎተታሉ። info
التفاسير:

external-link copy
72 : 40

فِي ٱلۡحَمِيمِ ثُمَّ فِي ٱلنَّارِ يُسۡجَرُونَ

72. በገሀነም ውስጥ ይጎተታሉ፤ ከዚያም በእሳት ውስጥ ይማገዳሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
73 : 40

ثُمَّ قِيلَ لَهُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡ تُشۡرِكُونَ

73. ከዚያም ለእነርሱ ይባላሉ፡- «(በአላህ) ታጋሯቸው የነበራችሁት የታሉ? info
التفاسير:

external-link copy
74 : 40

مِن دُونِ ٱللَّهِۖ قَالُواْ ضَلُّواْ عَنَّا بَل لَّمۡ نَكُن نَّدۡعُواْ مِن قَبۡلُ شَيۡـٔٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ ٱلۡكَٰفِرِينَ

74. ከአላህ ሌላ የምታጋሩዋቸው (የት አሉ)?» «ከእኛ ተሰወሩብን፤ ከቶ ከዚህ በፊት ምንም የምንገዛ አልነበርንም» ይላሉ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ካሐዲያንን ያሳስታል:: info
التفاسير:

external-link copy
75 : 40

ذَٰلِكُم بِمَا كُنتُمۡ تَفۡرَحُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَبِمَا كُنتُمۡ تَمۡرَحُونَ

75. «ይህ (ቅጣታችሁ) ያላአግባብ በምድር ውስጥ ትደሰቱ በነበራችሁትና ትንበጣረሩ በነበራችሁት ነው። info
التفاسير:

external-link copy
76 : 40

ٱدۡخُلُوٓاْ أَبۡوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ فَبِئۡسَ مَثۡوَى ٱلۡمُتَكَبِّرِينَ

76. የገሀነምን በሮች ውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ ግቡ።» (ይባላሉ)። የትዕቢተኞችም መኖሪያ (ገሀነም) ምን ትከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
77 : 40

فَٱصۡبِرۡ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞۚ فَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعۡضَ ٱلَّذِي نَعِدُهُمۡ أَوۡ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيۡنَا يُرۡجَعُونَ

77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፤ የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን በህይወትህ ብናሳይህ መልካም ነው:: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ ወደ እኛ ይመለሳሉ:: info
التفاسير: