ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
17 : 40

ٱلۡيَوۡمَ تُجۡزَىٰ كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا كَسَبَتۡۚ لَا ظُلۡمَ ٱلۡيَوۡمَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ

17. «ዛሬ ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ትመነዳለች፤ ዛሬ በደል የለም:: አላህ በእርግጥ ምርመራው ፈጣን ነው።» ይባላል:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 40

وَأَنذِرۡهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡأٓزِفَةِ إِذِ ٱلۡقُلُوبُ لَدَى ٱلۡحَنَاجِرِ كَٰظِمِينَۚ مَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنۡ حَمِيمٖ وَلَا شَفِيعٖ يُطَاعُ

18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቅርቢቱንም የትንሳኤ ቀን ልቦች ጭንቀትን የተሞሉ ሆነው ላንቃዎች ዘንድ የሚደርሱበትን ጊዜ አስጠንቅቃቸው:: ለበዳዮች ምንም ወዳጅና ተሰሚ አማላጅ የላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 40

يَعۡلَمُ خَآئِنَةَ ٱلۡأَعۡيُنِ وَمَا تُخۡفِي ٱلصُّدُورُ

19. አላህ የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 40

وَٱللَّهُ يَقۡضِي بِٱلۡحَقِّۖ وَٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَقۡضُونَ بِشَيۡءٍۗ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ

20. አላህም በእውነት ይፈርዳል:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚገዟቸው በምንም አይፈርዱም:: አላህ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 40

۞ أَوَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ كَانُواْ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَانُواْ هُمۡ أَشَدَّ مِنۡهُمۡ قُوَّةٗ وَءَاثَارٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمۡ وَمَا كَانَ لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن وَاقٖ

21. የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? በሀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶች ከእነርሱም ይበልጥ የበረቱ ነበሩ:: አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው። ለእነርሱም ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ አልነበራቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 40

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَانَت تَّأۡتِيهِمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَكَفَرُواْ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُۚ إِنَّهُۥ قَوِيّٞ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ

22. ይህ (መያዝ) እነርሱ መልዕክተኞቻቸው በተዓምራት ይመጡባቸው ስለ ነበሩና ስለካዱ ነው:: አላህም ያዛቸው። እርሱ ኃያል፤ ቅጣተ ብርቱ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 40

وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ

23. ሙሳንም በተዓምራቶቻችንና በግልጽ ማስረጃ በእርግጥ ላክነው:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 40

إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَهَٰمَٰنَ وَقَٰرُونَ فَقَالُواْ سَٰحِرٞ كَذَّابٞ

24. ወደ ፈርዖን ወደ ሃማን እና ወደ ቃሩንም ላክነው:: «ድግምተኛ እና ውሸታም ነው» አሉ:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 40

فَلَمَّا جَآءَهُم بِٱلۡحَقِّ مِنۡ عِندِنَا قَالُواْ ٱقۡتُلُوٓاْ أَبۡنَآءَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ وَٱسۡتَحۡيُواْ نِسَآءَهُمۡۚ وَمَا كَيۡدُ ٱلۡكَٰفِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَٰلٖ

25. ከእኛ ዘንድ እውነትን ይዞ በመጣላቸውም ጊዜ: «የእነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑት ሰዎች ወንድ ልጆች ግደሉ፤ ሴቶቻቸውንም አስቀሩ።» አሉ፤ የከሓዲያንም ተንኮል በጥፋት ውስጥ እንጂ ሌላ አይደለም:: info
التفاسير: