ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
38 : 20

إِذۡ أَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰٓ أُمِّكَ مَا يُوحَىٰٓ

38. «ለእናትህ በራእይ ባሳወቅን ጊዜ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
39 : 20

أَنِ ٱقۡذِفِيهِ فِي ٱلتَّابُوتِ فَٱقۡذِفِيهِ فِي ٱلۡيَمِّ فَلۡيُلۡقِهِ ٱلۡيَمُّ بِٱلسَّاحِلِ يَأۡخُذۡهُ عَدُوّٞ لِّي وَعَدُوّٞ لَّهُۥۚ وَأَلۡقَيۡتُ عَلَيۡكَ مَحَبَّةٗ مِّنِّي وَلِتُصۡنَعَ عَلَىٰ عَيۡنِيٓ

39. «‹ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ አስገቢው እርሱንም (ሳጥኑን) በባህር ላይ ጣይው፤ ባህሩም በዳርቻው ይጥለዋል (ይተፋዋል):: ለእኔም ለእርሱም ጠላት የሆነ ሰው ይይዘዋልና› በማለት (ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ)። ልትወደድና በዐይኔ እይታ (በእኔም ጥበቃ) ታድግ ዘንድ ባንተ ላይም ከእኔ የሆነ መወደድን ጣልኩብህ:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 20

إِذۡ تَمۡشِيٓ أُخۡتُكَ فَتَقُولُ هَلۡ أَدُلُّكُمۡ عَلَىٰ مَن يَكۡفُلُهُۥۖ فَرَجَعۡنَٰكَ إِلَىٰٓ أُمِّكَ كَيۡ تَقَرَّ عَيۡنُهَا وَلَا تَحۡزَنَۚ وَقَتَلۡتَ نَفۡسٗا فَنَجَّيۡنَٰكَ مِنَ ٱلۡغَمِّ وَفَتَنَّٰكَ فُتُونٗاۚ فَلَبِثۡتَ سِنِينَ فِيٓ أَهۡلِ مَدۡيَنَ ثُمَّ جِئۡتَ عَلَىٰ قَدَرٖ يَٰمُوسَىٰ

40. «እህትህ በምትሄድና ‹የሚያሳድገውን ሰው ላመላክታችሁን?› ባለች ጊዜ (መወደድን ጣልኩብህ):: ወደ እናትህም ዓይኗ እንዲረጋና እርሷ እንዳታዝንም መለስንህ:: ነፍስንም ገደልክ ከጭንቅም አዳንንህ:: ፈተናዎችንም ፈተንህ:: በመድየን ቤተሰቦችም ውስጥ ብዙ ዓመታትን ተቀመጥክ:: ከዚያ ሙሳ ሆይ! በተወሰነ ጊዜ ላይ መጣህ:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 20

وَٱصۡطَنَعۡتُكَ لِنَفۡسِي

41. «ለራሴም ለመልዕክተኝነት መረጥኩህ:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 20

ٱذۡهَبۡ أَنتَ وَأَخُوكَ بِـَٔايَٰتِي وَلَا تَنِيَا فِي ذِكۡرِي

42. «አንተና ወንድምህ በተዓምራቴ ሆናችሁ ሂዱ:: እኔንም ከማውሳትም አትቦዝኑ:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 20

ٱذۡهَبَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ إِنَّهُۥ طَغَىٰ

43. «ወደ ፈርዖን ሂዱ:: እርሱ ወሰን አልፏልና:: info
التفاسير:

external-link copy
44 : 20

فَقُولَا لَهُۥ قَوۡلٗا لَّيِّنٗا لَّعَلَّهُۥ يَتَذَكَّرُ أَوۡ يَخۡشَىٰ

44. «እርሱ ምን አልባትም ይገሰጥ ወይም ይፈራ ዘንድ:: ለእርሱ ለስላሳን ቃል ተናገሩት።» info
التفاسير:

external-link copy
45 : 20

قَالَا رَبَّنَآ إِنَّنَا نَخَافُ أَن يَفۡرُطَ عَلَيۡنَآ أَوۡ أَن يَطۡغَىٰ

45. «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ክፋት በመስራት መቸኮሉን ወይም ኩራትን መጨመሩን እንፈራለን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
46 : 20

قَالَ لَا تَخَافَآۖ إِنَّنِي مَعَكُمَآ أَسۡمَعُ وَأَرَىٰ

46. አላህም አለ: «እኔ በእርግጥ ከናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ:: የሚለውንም ሁሉ እሰማለሁ። የሚፈጸመዉንም አያለሁም። info
التفاسير:

external-link copy
47 : 20

فَأۡتِيَاهُ فَقُولَآ إِنَّا رَسُولَا رَبِّكَ فَأَرۡسِلۡ مَعَنَا بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ وَلَا تُعَذِّبۡهُمۡۖ قَدۡ جِئۡنَٰكَ بِـَٔايَةٖ مِّن رَّبِّكَۖ وَٱلسَّلَٰمُ عَلَىٰ مَنِ ٱتَّبَعَ ٱلۡهُدَىٰٓ

47. እናም ወደ እርሱም ሂዱና (እንዲህ) በሉት: ‹እኛ የጌታህ መልዕክተኞች ነንና የኢስራኢልን ልጆች ሁሉ ከእኛ ጋር ልቀቅ። አታሰቃያቸዉም:: ከጌታህ በሆነው ተዓምር በእርግጥ መጥተንሃልና:: ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን። info
التفاسير:

external-link copy
48 : 20

إِنَّا قَدۡ أُوحِيَ إِلَيۡنَآ أَنَّ ٱلۡعَذَابَ عَلَىٰ مَن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ

48. «‹እነሆ የአላህ ቅጣት እውነትን ባስተባበለና እምቢ ባለ ሰው ላይ እንደሆነ በእርግጥ አያሌ መልዕክት ተወረደልን።› በሉት።» info
التفاسير:

external-link copy
49 : 20

قَالَ فَمَن رَّبُّكُمَا يَٰمُوسَىٰ

49. ፈርዖንም «ሙሳ ሆይ! ጌታችሁ ማነው?» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
50 : 20

قَالَ رَبُّنَا ٱلَّذِيٓ أَعۡطَىٰ كُلَّ شَيۡءٍ خَلۡقَهُۥ ثُمَّ هَدَىٰ

50. «ጌታችን ያ ለፍጥረቱ ሁሉ የሚያስፈልገውን ቅርጹንና ባህሪውን የሰጠው ከዚያም ሁሉንም ለተፈጠረለት የመራው ነው።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
51 : 20

قَالَ فَمَا بَالُ ٱلۡقُرُونِ ٱلۡأُولَىٰ

51. ፈርዖንም «የመጀመሪያይቱ ዘመናት ህዝቦች ሁኔታስ ምንድን ነው?» አለ:: info
التفاسير: