ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
126 : 20

قَالَ كَذَٰلِكَ أَتَتۡكَ ءَايَٰتُنَا فَنَسِيتَهَاۖ وَكَذَٰلِكَ ٱلۡيَوۡمَ تُنسَىٰ

126. «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው:: ተዓምራቶቻችን መጡልህና ተውካቸውም:: ልክ እንደዚሁም ዛሬ ትተዋለህ።» ይለዋል። info
التفاسير:

external-link copy
127 : 20

وَكَذَٰلِكَ نَجۡزِي مَنۡ أَسۡرَفَ وَلَمۡ يُؤۡمِنۢ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِۦۚ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَشَدُّ وَأَبۡقَىٰٓ

127.እንደዚሁም ያጋራንና በጌታው አናቅጽ ያላመነን እንቀጣዋለን:: የመጨረሻይቱ ዓለም ቅጣት በጣም ብርቱና ለሁልጊዜም ዘውታሪ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
128 : 20

أَفَلَمۡ يَهۡدِ لَهُمۡ كَمۡ أَهۡلَكۡنَا قَبۡلَهُم مِّنَ ٱلۡقُرُونِ يَمۡشُونَ فِي مَسَٰكِنِهِمۡۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّأُوْلِي ٱلنُّهَىٰ

128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ቁረይሾች) ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሆነው ሳሉ ለእነርሱ አልተገለጸላቸዉምን? በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ መልዕክቶች አሉበት:: info
التفاسير:

external-link copy
129 : 20

وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَكَانَ لِزَامٗا وَأَجَلٞ مُّسَمّٗى

129.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ያለፈች ቃልና የተወሰነ ጊዜ ባልነበረ ኖሮ ቅጣቱ አሁኑኑ የሚይዛቸው ይሆን ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
130 : 20

فَٱصۡبِرۡ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ قَبۡلَ طُلُوعِ ٱلشَّمۡسِ وَقَبۡلَ غُرُوبِهَاۖ وَمِنۡ ءَانَآيِٕ ٱلَّيۡلِ فَسَبِّحۡ وَأَطۡرَافَ ٱلنَّهَارِ لَعَلَّكَ تَرۡضَىٰ

130. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) በሚሉትም ሁሉ ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ጸሐይ ከመውጣቷ በፊትና ከመግባቷም በፊት የምታመሰግን ሆነህ አጥራው:: ከሌሊት ሰዓቶችም በቀን ጫፎችም አጥራው:: በሚሰጥህ ምንዳ ልትወድ ይከጀላልና:: info
التفاسير:

external-link copy
131 : 20

وَلَا تَمُدَّنَّ عَيۡنَيۡكَ إِلَىٰ مَا مَتَّعۡنَا بِهِۦٓ أَزۡوَٰجٗا مِّنۡهُمۡ زَهۡرَةَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا لِنَفۡتِنَهُمۡ فِيهِۚ وَرِزۡقُ رَبِّكَ خَيۡرٞ وَأَبۡقَىٰ

131.ዐይኖችህን ከሰዎች የተወሰኑ ክፍሎችን ልንፈትናቸው ወደ አጣቀምንበት ወደ ቅርቢቱ ህይወት ጌጦች አትዘርጋ:: የጌታህ ሲሳይ በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
132 : 20

وَأۡمُرۡ أَهۡلَكَ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱصۡطَبِرۡ عَلَيۡهَاۖ لَا نَسۡـَٔلُكَ رِزۡقٗاۖ نَّحۡنُ نَرۡزُقُكَۗ وَٱلۡعَٰقِبَةُ لِلتَّقۡوَىٰ

132.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቤተሰብህንም በሶላት ላይ እዘዝ:: አንተም በእርሷ ላይ ዘውትር:: ሲሳይን አንጠይቅህም:: እኛ እንሰጥሃለን:: መልካሚቱ መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
133 : 20

وَقَالُواْ لَوۡلَا يَأۡتِينَا بِـَٔايَةٖ مِّن رَّبِّهِۦٓۚ أَوَلَمۡ تَأۡتِهِم بَيِّنَةُ مَا فِي ٱلصُّحُفِ ٱلۡأُولَىٰ

133. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተከራካሪዎችህ «ከጌታው በሆነ ተዓምር አይመጣምን?» አሉ:: በመጀመሪያዎቹ ጹሁፎች ውስጥ ያለችው ማስረጃ አልመጣቻቸዉምን? info
التفاسير:

external-link copy
134 : 20

وَلَوۡ أَنَّآ أَهۡلَكۡنَٰهُم بِعَذَابٖ مِّن قَبۡلِهِۦ لَقَالُواْ رَبَّنَا لَوۡلَآ أَرۡسَلۡتَ إِلَيۡنَا رَسُولٗا فَنَتَّبِعَ ءَايَٰتِكَ مِن قَبۡلِ أَن نَّذِلَّ وَنَخۡزَىٰ

134. እኛም (ከሙሐመድ መላክ) በፊት በቅጣት ባጠፋናቸው ኖሮ «ጌታችን ሆይ! ከመዋረዳችንና ከማፈራችን በፊት አናቅጽህን እንከተል ዘንድ ወደኛ መልዕክተኛን አትልክልንም ነበርን?» ባሉ ነበር:: info
التفاسير:

external-link copy
135 : 20

قُلۡ كُلّٞ مُّتَرَبِّصٞ فَتَرَبَّصُواْۖ فَسَتَعۡلَمُونَ مَنۡ أَصۡحَٰبُ ٱلصِّرَٰطِ ٱلسَّوِيِّ وَمَنِ ٱهۡتَدَىٰ

135. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁሉም ተጠባባቂ ነው:: ተጠባበቁም የቀጥታዉም መንገድ ባለቤቶች እነማን እንደ ሆኑ እነማንም እንደ ተመሩ ወደፊት ታውቃላችሁ።» በላቸው:: info
التفاسير: