ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
32 : 15

قَالَ يَٰٓإِبۡلِيسُ مَا لَكَ أَلَّا تَكُونَ مَعَ ٱلسَّٰجِدِينَ

32. አላህም፡ «ዲያብሎስ ሆይ! ከሰጋጆቹ ጋር የማትሆን ላንተ ምን ምክንያት አለህ?» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
33 : 15

قَالَ لَمۡ أَكُن لِّأَسۡجُدَ لِبَشَرٍ خَلَقۡتَهُۥ مِن صَلۡصَٰلٖ مِّنۡ حَمَإٖ مَّسۡنُونٖ

33. «ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከግም ጭቃ ለፈጠርከው ሰው ልሰግድ አይገባኝም።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
34 : 15

قَالَ فَٱخۡرُجۡ مِنۡهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٞ

34. አላህም አለው: «ከእርሷም ውጣ አንተ የተባረርክ እርጉም ነህና። info
التفاسير:

external-link copy
35 : 15

وَإِنَّ عَلَيۡكَ ٱللَّعۡنَةَ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلدِّينِ

35. «ባንተ ላይም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እርግማን አለብህ።» አለው። info
التفاسير:

external-link copy
36 : 15

قَالَ رَبِّ فَأَنظِرۡنِيٓ إِلَىٰ يَوۡمِ يُبۡعَثُونَ

36. «ጌታዬ ሆይ! እንግዲያውስ እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
37 : 15

قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ ٱلۡمُنظَرِينَ

37. አላህም አለ፡- «አንተ ከሚቆዩት ነህ። info
التفاسير:

external-link copy
38 : 15

إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡوَقۡتِ ٱلۡمَعۡلُومِ

38. «እስከታወቀው ቀን ድረስ።» info
التفاسير:

external-link copy
39 : 15

قَالَ رَبِّ بِمَآ أَغۡوَيۡتَنِي لَأُزَيِّنَنَّ لَهُمۡ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَأُغۡوِيَنَّهُمۡ أَجۡمَعِينَ

39. ዲያብሎስም አለ፡- «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይሁንብኝ ለእነርሱ በምድር ላይ ኃጢአትን እሸልምላቸዋለሁ። ሁላቸውንም አጠማቸዋለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
40 : 15

إِلَّا عِبَادَكَ مِنۡهُمُ ٱلۡمُخۡلَصِينَ

40. «ከእነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ።» info
التفاسير:

external-link copy
41 : 15

قَالَ هَٰذَا صِرَٰطٌ عَلَيَّ مُسۡتَقِيمٌ

41. አላህም አለ፡- «ይህ በእኔ ላይ መጠበቁ የተገባ ቀጥተኛ መንገድ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
42 : 15

إِنَّ عِبَادِي لَيۡسَ لَكَ عَلَيۡهِمۡ سُلۡطَٰنٌ إِلَّا مَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلۡغَاوِينَ

42. «እነሆ ባሮቼ! በእነርሱ ላይ አንተ ስልጣን የለህም። ከጠማሞች የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር። info
التفاسير:

external-link copy
43 : 15

وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوۡعِدُهُمۡ أَجۡمَعِينَ

43. «ገሀነምም ለእርሱና ለተከተሉት ለሁሉም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት። info
التفاسير:

external-link copy
44 : 15

لَهَا سَبۡعَةُ أَبۡوَٰبٖ لِّكُلِّ بَابٖ مِّنۡهُمۡ جُزۡءٞ مَّقۡسُومٌ

44. «ለእርሷ ሰባት በሮች (ደጃፎች ) አሏት። ለየበሮቹም ሁሉ ከሰይጣናት ቡድኖች የተከፋፈለ ድርሻ አለ።» info
التفاسير:

external-link copy
45 : 15

إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ

45. እነዚያ ከኃጢአት የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
46 : 15

ٱدۡخُلُوهَا بِسَلَٰمٍ ءَامِنِينَ

46. «ጸጥተኞች ሆናችሁ በሰላም ግቧት።» ይባላሉ። info
التفاسير:

external-link copy
47 : 15

وَنَزَعۡنَا مَا فِي صُدُورِهِم مِّنۡ غِلٍّ إِخۡوَٰنًا عَلَىٰ سُرُرٖ مُّتَقَٰبِلِينَ

47. በአልጋዎችም ላይ ፊት ለፊት የሚተያዩ ወንድማማቾች ሆነው በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ቂም ሁሉ እናስወግዳለን:: info
التفاسير:

external-link copy
48 : 15

لَا يَمَسُّهُمۡ فِيهَا نَصَبٞ وَمَا هُم مِّنۡهَا بِمُخۡرَجِينَ

48. በእርሷም ውስጥ ምንም ድካም አይነካቸዉም፤ እነርሱም ከእርሷ ለምንጊዜም የሚወጡ አይደሉም:: info
التفاسير:

external-link copy
49 : 15

۞ نَبِّئۡ عِبَادِيٓ أَنِّيٓ أَنَا ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِيمُ

49. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መሃሪና አዛኝ እኔው ብቻ መሆኔን ለባሮቼ ንገር:: info
التفاسير:

external-link copy
50 : 15

وَأَنَّ عَذَابِي هُوَ ٱلۡعَذَابُ ٱلۡأَلِيمُ

50. ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መሆኑንም ንገራቸው። info
التفاسير:

external-link copy
51 : 15

وَنَبِّئۡهُمۡ عَن ضَيۡفِ إِبۡرَٰهِيمَ

51. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢብራሂም እንግዶችም ወሬ ንገራቸው:: info
التفاسير: