ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
16 : 15

وَلَقَدۡ جَعَلۡنَا فِي ٱلسَّمَآءِ بُرُوجٗا وَزَيَّنَّٰهَا لِلنَّٰظِرِينَ

16. በሰማይም ላይ ከዋክብቶችን በእርግጥ አድርገናል (ፈጥረናል):: ለተመልካቾችም በከዋክብት አጊጠናታል:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 15

وَحَفِظۡنَٰهَا مِن كُلِّ شَيۡطَٰنٖ رَّجِيمٍ

17. ከተባረረ ሰይጣንም ሁሉ ጠብቀናታል:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 15

إِلَّا مَنِ ٱسۡتَرَقَ ٱلسَّمۡعَ فَأَتۡبَعَهُۥ شِهَابٞ مُّبِينٞ

18. ግን ወሬ መስማትን የሚሰርቅ ወዲያውኑ አብሪ ችቦ ይከተለዋል:: (ያቃጥለዋል):: info
التفاسير:

external-link copy
19 : 15

وَٱلۡأَرۡضَ مَدَدۡنَٰهَا وَأَلۡقَيۡنَا فِيهَا رَوَٰسِيَ وَأَنۢبَتۡنَا فِيهَا مِن كُلِّ شَيۡءٖ مَّوۡزُونٖ

19. ምድርንም ዘረጋናት:: በውስጧም ኮረብታዎችን ጣልንባት:: በውስጧም የተለካን በቃይ ሁሉ አበቀልንባት:: info
التفاسير:

external-link copy
20 : 15

وَجَعَلۡنَا لَكُمۡ فِيهَا مَعَٰيِشَ وَمَن لَّسۡتُمۡ لَهُۥ بِرَٰزِقِينَ

20.(ሰዎች ሆይ!) በእርሷ ውስጥ ለእናንተ ልዩ ልዩ መኖሪያዎችንና ለእርሱ መጋቢዎቹ ያልሆናችሁትንም እንስሳትን አደረግንላችሁ:: info
التفاسير:

external-link copy
21 : 15

وَإِن مِّن شَيۡءٍ إِلَّا عِندَنَا خَزَآئِنُهُۥ وَمَا نُنَزِّلُهُۥٓ إِلَّا بِقَدَرٖ مَّعۡلُومٖ

21. መጋዘኖቹም መክፈቻቸው እኛው ዘንድ ያልሆነ ምንም ነገር የለም:: በተወሰነም ልክ እንጂ አናወርደዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
22 : 15

وَأَرۡسَلۡنَا ٱلرِّيَٰحَ لَوَٰقِحَ فَأَنزَلۡنَا مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَأَسۡقَيۡنَٰكُمُوهُ وَمَآ أَنتُمۡ لَهُۥ بِخَٰزِنِينَ

22. ንፋስን ደመናን ተሸካሚዎች አድርገን ላክን:: ከሰማይም ከደመና ዝናብን አወረድን:: እርሱንም አጠጣናችሁ:: እናንተ ለእርሱ አድላቢዎች (አከማቾች) አይደላችሁም:: info
التفاسير:

external-link copy
23 : 15

وَإِنَّا لَنَحۡنُ نُحۡيِۦ وَنُمِيتُ وَنَحۡنُ ٱلۡوَٰرِثُونَ

23. እኛ ሕያው የምናደርግና የምንገድል እኛው ብቻ ነን:: እኛው ፍጡርን ሁሉ የምንወርስ ቀሪ ነን:: info
التفاسير:

external-link copy
24 : 15

وَلَقَدۡ عَلِمۡنَا ٱلۡمُسۡتَقۡدِمِينَ مِنكُمۡ وَلَقَدۡ عَلِمۡنَا ٱلۡمُسۡتَـٔۡخِرِينَ

24. ከናንተም ተቀዳሚዎቹን በእርግጥ አውቀናል:: ወደ ኋላ ቀሪዎቹንም በእርግጥ አውቀናል:: info
التفاسير:

external-link copy
25 : 15

وَإِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَحۡشُرُهُمۡۚ إِنَّهُۥ حَكِيمٌ عَلِيمٞ

25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!)ጌታህ ይሰበስባቸዋል:: እርሱ ጥበበኛና ሁሉን አዋቂ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
26 : 15

وَلَقَدۡ خَلَقۡنَا ٱلۡإِنسَٰنَ مِن صَلۡصَٰلٖ مِّنۡ حَمَإٖ مَّسۡنُونٖ

26. ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው:: info
التفاسير:

external-link copy
27 : 15

وَٱلۡجَآنَّ خَلَقۡنَٰهُ مِن قَبۡلُ مِن نَّارِ ٱلسَّمُومِ

27. ጃንን ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው:: info
التفاسير:

external-link copy
28 : 15

وَإِذۡ قَالَ رَبُّكَ لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ إِنِّي خَٰلِقُۢ بَشَرٗا مِّن صَلۡصَٰلٖ مِّنۡ حَمَإٖ مَّسۡنُونٖ

28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ለመላዕክት ባለ ጊዜ (የሆነውን አስታውስ): «እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ። info
التفاسير:

external-link copy
29 : 15

فَإِذَا سَوَّيۡتُهُۥ وَنَفَخۡتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُواْ لَهُۥ سَٰجِدِينَ

29. «ፍጥረቱን ባስተካከልኩትና በውስጡ ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ሆናችሁ ውደቁ።» info
التفاسير:

external-link copy
30 : 15

فَسَجَدَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ كُلُّهُمۡ أَجۡمَعُونَ

30. መላዓክትም ሁሉም ተሰብስበው ሰገዱ:: info
التفاسير:

external-link copy
31 : 15

إِلَّآ إِبۡلِيسَ أَبَىٰٓ أَن يَكُونَ مَعَ ٱلسَّٰجِدِينَ

31. ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር:: እርሱማ ከሰጋጆቹ ጋር ከመሆን እንቢ አለ። info
التفاسير: