ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
144 : 7

قَالَ يَٰمُوسَىٰٓ إِنِّي ٱصۡطَفَيۡتُكَ عَلَى ٱلنَّاسِ بِرِسَٰلَٰتِي وَبِكَلَٰمِي فَخُذۡ مَآ ءَاتَيۡتُكَ وَكُن مِّنَ ٱلشَّٰكِرِينَ

(አላህም) አለው፡- «ሙሳ ሆይ! እኔ በመልክቶቼና በማናገሬ በሰዎች ላይ መረጥኩህ፡፡ የሰጡህንም ያዝ፡፡ ከአመስጋኞቹም ኹን፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
145 : 7

وَكَتَبۡنَا لَهُۥ فِي ٱلۡأَلۡوَاحِ مِن كُلِّ شَيۡءٖ مَّوۡعِظَةٗ وَتَفۡصِيلٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ فَخُذۡهَا بِقُوَّةٖ وَأۡمُرۡ قَوۡمَكَ يَأۡخُذُواْ بِأَحۡسَنِهَاۚ سَأُوْرِيكُمۡ دَارَ ٱلۡفَٰسِقِينَ

ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት፡፡ (አልንም) በብርታትም ያዛት፡፡ ሕዝቦችህንም በመልካሟ እንዲይዙ እዘዛቸው፡፡ የአመጸኞቹን አገር በእርግጥ አሳያችኋለሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
146 : 7

سَأَصۡرِفُ عَنۡ ءَايَٰتِيَ ٱلَّذِينَ يَتَكَبَّرُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَإِن يَرَوۡاْ كُلَّ ءَايَةٖ لَّا يُؤۡمِنُواْ بِهَا وَإِن يَرَوۡاْ سَبِيلَ ٱلرُّشۡدِ لَا يَتَّخِذُوهُ سَبِيلٗا وَإِن يَرَوۡاْ سَبِيلَ ٱلۡغَيِّ يَتَّخِذُوهُ سَبِيلٗاۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَكَانُواْ عَنۡهَا غَٰفِلِينَ

እነዚያን ያለአግባብ በምድር ላይ የሚኮሩትን ከአንቀጾቼ በእርግጥ አዞራቸዋለሁ፡፡ ተዓምርንም ሁሉ ቢያዩ በርሷ አያምኑም፡፡ ቅንንም መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው አይዙትም፡፡ ግን የጥመትን መንገድ ቢያዩ መንገድ አድርገው ይይዙታል፡፡ ይህ እነርሱ በአንቀጾቻችን ስለአስተባበሉና ከእርሷም ዘንጊዎች ስለኾኑ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
147 : 7

وَٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَلِقَآءِ ٱلۡأٓخِرَةِ حَبِطَتۡ أَعۡمَٰلُهُمۡۚ هَلۡ يُجۡزَوۡنَ إِلَّا مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

እነዚያም በአንቀጾቻችንና መጨረሻይቱን ዓለም በመገናኘት ያስተባበሉት ሥራዎቻቸው ተበላሹ፡፡ ይሠሩት የነበረውን እንጂ ይመነዳሉን? info
التفاسير:

external-link copy
148 : 7

وَٱتَّخَذَ قَوۡمُ مُوسَىٰ مِنۢ بَعۡدِهِۦ مِنۡ حُلِيِّهِمۡ عِجۡلٗا جَسَدٗا لَّهُۥ خُوَارٌۚ أَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّهُۥ لَا يُكَلِّمُهُمۡ وَلَا يَهۡدِيهِمۡ سَبِيلًاۘ ٱتَّخَذُوهُ وَكَانُواْ ظَٰلِمِينَ

የሙሳም ሕዝቦች ከእርሱ (መኼድ) በኋላ ከጌጦቻቸው ወይፈንን አካልን ለርሱ ማግሳት ያለውን (አምላክ አድርገው) ያዙ፡፡ እርሱ የማያናግራቸው መንገድንም የማይመራቸው መኾኑን አይመለከቱምን? (አምላክ አድርገው) ያዙት፡፡ በዳዮችም ኾኑ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
149 : 7

وَلَمَّا سُقِطَ فِيٓ أَيۡدِيهِمۡ وَرَأَوۡاْ أَنَّهُمۡ قَدۡ ضَلُّواْ قَالُواْ لَئِن لَّمۡ يَرۡحَمۡنَا رَبُّنَا وَيَغۡفِرۡ لَنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ

በተጸጸቱና እነሱም በእርግጥ የተሳሳቱ መኾናቸውን ባዩ ጊዜ፡- «ጌታችን ባያዝንልንና ባይምረን በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡ info
التفاسير: