ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
82 : 7

وَمَا كَانَ جَوَابَ قَوۡمِهِۦٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓاْ أَخۡرِجُوهُم مِّن قَرۡيَتِكُمۡۖ إِنَّهُمۡ أُنَاسٞ يَتَطَهَّرُونَ

የሕዝቦቹም መልስ « (ሎጥንና ተከታዮቹን) ከከተማችሁ አውጧቸው፡፡ እነሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
83 : 7

فَأَنجَيۡنَٰهُ وَأَهۡلَهُۥٓ إِلَّا ٱمۡرَأَتَهُۥ كَانَتۡ مِنَ ٱلۡغَٰبِرِينَ

እርሱንና ቤተሰቦቹንም አዳንናቸው ሚስቱ ብቻ ስትቀር፡፡ እርሷ (ለጥፋት) ከቀሩት ኾነች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
84 : 7

وَأَمۡطَرۡنَا عَلَيۡهِم مَّطَرٗاۖ فَٱنظُرۡ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ

በእነሱም ላይ (የእሳት) ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
85 : 7

وَإِلَىٰ مَدۡيَنَ أَخَاهُمۡ شُعَيۡبٗاۚ قَالَ يَٰقَوۡمِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنۡ إِلَٰهٍ غَيۡرُهُۥۖ قَدۡ جَآءَتۡكُم بَيِّنَةٞ مِّن رَّبِّكُمۡۖ فَأَوۡفُواْ ٱلۡكَيۡلَ وَٱلۡمِيزَانَ وَلَا تَبۡخَسُواْ ٱلنَّاسَ أَشۡيَآءَهُمۡ وَلَا تُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ بَعۡدَ إِصۡلَٰحِهَاۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ

ወደ መድየንም (ምድያን) ወንድማቸውን ሹዓይብን (ላክን)፤ አላቸው፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ በእርግጥ መጥታላችኋለች፡፡ ስፍርንና ሚዛንን ሙሉ፡፡ ሰዎችንም አንዳቾቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡ ይህ ምእምናን እንደኾናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
86 : 7

وَلَا تَقۡعُدُواْ بِكُلِّ صِرَٰطٖ تُوعِدُونَ وَتَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ مَنۡ ءَامَنَ بِهِۦ وَتَبۡغُونَهَا عِوَجٗاۚ وَٱذۡكُرُوٓاْ إِذۡ كُنتُمۡ قَلِيلٗا فَكَثَّرَكُمۡۖ وَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُفۡسِدِينَ

« (ሰዎችን) የምታስፈራሩና ከአላህም መንገድ በእርሱ ያመኑትን የምታግዱ መጥመሟንም የምትፈልጉዋት ኾናችሁ በየመንገዱ አትቀመጡ፡፡ ጥቂቶችም በነበራችሁና ባበዛችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ የአጥፊዎችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
87 : 7

وَإِن كَانَ طَآئِفَةٞ مِّنكُمۡ ءَامَنُواْ بِٱلَّذِيٓ أُرۡسِلۡتُ بِهِۦ وَطَآئِفَةٞ لَّمۡ يُؤۡمِنُواْ فَٱصۡبِرُواْ حَتَّىٰ يَحۡكُمَ ٱللَّهُ بَيۡنَنَاۚ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلۡحَٰكِمِينَ

«ከእናንተም በዚያ እኔ በእርሱ በተላክሁበት ያመኑ ጭፍሮችና ያላመኑ ጭፍሮችም ቢኖሩ በመካከላችን አላህ እስከሚፈርድ ታገሱ፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው፡፡» info
التفاسير: