ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
34 : 40

وَلَقَدۡ جَآءَكُمۡ يُوسُفُ مِن قَبۡلُ بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَمَا زِلۡتُمۡ فِي شَكّٖ مِّمَّا جَآءَكُم بِهِۦۖ حَتَّىٰٓ إِذَا هَلَكَ قُلۡتُمۡ لَن يَبۡعَثَ ٱللَّهُ مِنۢ بَعۡدِهِۦ رَسُولٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَنۡ هُوَ مُسۡرِفٞ مُّرۡتَابٌ

ዩሱፍም ከዚህ በፊት ግልጽ ማስረጃዎችን በእርግጥ አመጣላቸሁ፡፡ ከዚያም እርሱ ካመጣላችሁ ነገር ከመጠራጠር አልተወገዳችሁም፡፡ በጠፋም ጊዜ «አላህ ከእርሱ ኋላ መልክተኛን በጭራሽ አይልክም» አላችሁ፡፡ አላህ እንደዚሁ ድንበር አላፊ ተጠራጣሪ የኾነን ሰው ያሳስታል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
35 : 40

ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِيٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ بِغَيۡرِ سُلۡطَٰنٍ أَتَىٰهُمۡۖ كَبُرَ مَقۡتًا عِندَ ٱللَّهِ وَعِندَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْۚ كَذَٰلِكَ يَطۡبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ قَلۡبِ مُتَكَبِّرٖ جَبَّارٖ

እነዚያ፤ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ ተዓምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም አመኑት ዘንድ መጠላቱ በጣም ተለቀ፡፡ እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ (ሰው) ልብ ሁሉ ላይ ያትማል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
36 : 40

وَقَالَ فِرۡعَوۡنُ يَٰهَٰمَٰنُ ٱبۡنِ لِي صَرۡحٗا لَّعَلِّيٓ أَبۡلُغُ ٱلۡأَسۡبَٰبَ

ፈርዖንም አለ «ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ ረዢም ሕንጻን ለእኔ ካብልኝ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
37 : 40

أَسۡبَٰبَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ فَأَطَّلِعَ إِلَىٰٓ إِلَٰهِ مُوسَىٰ وَإِنِّي لَأَظُنُّهُۥ كَٰذِبٗاۚ وَكَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِفِرۡعَوۡنَ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ وَصُدَّ عَنِ ٱلسَّبِيلِۚ وَمَا كَيۡدُ فِرۡعَوۡنَ إِلَّا فِي تَبَابٖ

«የሰማያትን መንገዶች (እደርስ ዘንድ)፣ ወደ ሙሳም አምላክ እመለከት ዘንድ፡፡ እኔም ውሸታም ነው ብዬ በእርግጥ እጠረጥረዋለሁ» (አለ)፡፡ እንደዚሁም ለፈርዖን መጥፎ ሥራው ተሸለመለት፡፡ ከቅን መንገድም ታገደ፡፡ የፈርዖንም ተንኮል በከሳራ ውስጥ እንጅ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
38 : 40

وَقَالَ ٱلَّذِيٓ ءَامَنَ يَٰقَوۡمِ ٱتَّبِعُونِ أَهۡدِكُمۡ سَبِيلَ ٱلرَّشَادِ

ያም ያመነው አለ «ወገኖቼ ሆይ! ተከተሉኝ፡፡ ቀጥታውን መንገድ እመራችኋለሁና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
39 : 40

يَٰقَوۡمِ إِنَّمَا هَٰذِهِ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا مَتَٰعٞ وَإِنَّ ٱلۡأٓخِرَةَ هِيَ دَارُ ٱلۡقَرَارِ

«ወገኖቼ ሆይ! ይህቺ ቅርቢቱ ሕይወት (ጥቂት) መጣቀሚያ ብቻ ናት፡፡ መጨረሻይቱም ዓለም እርሷ መርጊያ አገር ናት፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
40 : 40

مَنۡ عَمِلَ سَيِّئَةٗ فَلَا يُجۡزَىٰٓ إِلَّا مِثۡلَهَاۖ وَمَنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِنٞ فَأُوْلَٰٓئِكَ يَدۡخُلُونَ ٱلۡجَنَّةَ يُرۡزَقُونَ فِيهَا بِغَيۡرِ حِسَابٖ

«መጥፎን የሠራ ሰው ብጤዋን እንጅ አይምመነዳም፡፡ እርሱ ምእመን ኾኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ፡፡ info
التفاسير: