ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
26 : 40

وَقَالَ فِرۡعَوۡنُ ذَرُونِيٓ أَقۡتُلۡ مُوسَىٰ وَلۡيَدۡعُ رَبَّهُۥٓۖ إِنِّيٓ أَخَافُ أَن يُبَدِّلَ دِينَكُمۡ أَوۡ أَن يُظۡهِرَ فِي ٱلۡأَرۡضِ ٱلۡفَسَادَ

ፈርዖንም «ተዉኝ፤ ሙሳን ልግደል፡፡ ጌታውንም ይጥራ (ያድነው እንደኾነ)፡፡ እኔ ሃይማኖታችሁን ሊለውጥ፤ ወይም በምድር ውስጥ ጥፋትን ሊያሰራጭ እፈራለሁና» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
27 : 40

وَقَالَ مُوسَىٰٓ إِنِّي عُذۡتُ بِرَبِّي وَرَبِّكُم مِّن كُلِّ مُتَكَبِّرٖ لَّا يُؤۡمِنُ بِيَوۡمِ ٱلۡحِسَابِ

ሙሳም «እኔ በምርመራው ቀን ከማያምን ትዕቢተኛ ሁሉ በጌታዬና በጌታችሁ ተጠበቅሁ» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 40

وَقَالَ رَجُلٞ مُّؤۡمِنٞ مِّنۡ ءَالِ فِرۡعَوۡنَ يَكۡتُمُ إِيمَٰنَهُۥٓ أَتَقۡتُلُونَ رَجُلًا أَن يَقُولَ رَبِّيَ ٱللَّهُ وَقَدۡ جَآءَكُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ مِن رَّبِّكُمۡۖ وَإِن يَكُ كَٰذِبٗا فَعَلَيۡهِ كَذِبُهُۥۖ وَإِن يَكُ صَادِقٗا يُصِبۡكُم بَعۡضُ ٱلَّذِي يَعِدُكُمۡۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهۡدِي مَنۡ هُوَ مُسۡرِفٞ كَذَّابٞ

ከፈርዖንም ቤተሰቦች አንድ እምነቱን የሚደብቅ ምእመን ሰው አለ፡- «ሰውየውን ከጌታችሁ በተዓምራቶች በእርግጥ የመጣለችሁ ሲኾን ‹ጌታዬ አላህ ነው› ስለሚል ትገድላላችሁን? ውሸታምም ቢኾን ውሸቱ በርሱው ላይ ነው፡፡ እውነተኛ ቢኾን ግን የዚያ የሚያሰፈራራችሁ ከፊሉ ያገኛችኋል፡፡ አላህ ያንን እርሱ ድንበር አላፊ ውሸታም የኾነውን አይመራምና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 40

يَٰقَوۡمِ لَكُمُ ٱلۡمُلۡكُ ٱلۡيَوۡمَ ظَٰهِرِينَ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَمَن يَنصُرُنَا مِنۢ بَأۡسِ ٱللَّهِ إِن جَآءَنَاۚ قَالَ فِرۡعَوۡنُ مَآ أُرِيكُمۡ إِلَّا مَآ أَرَىٰ وَمَآ أَهۡدِيكُمۡ إِلَّا سَبِيلَ ٱلرَّشَادِ

«ወገኖቼ ሆይ! በምድር ላይ አሸናፊዎች ስትኾኑ ዛሬ መንግስቱ የእናንተ ነው፡፡ ታዲያ ከአላህ ቅጣት ቢመጣብን የሚያድነን ማን ነው?» (አለ)፡፡ ፈርዖን «የማየውን ነገር እንጅ፤ አላመለክታችሁም፡፡ ቅኑንም መንገድ እንጅ አልመራችሁም» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
30 : 40

وَقَالَ ٱلَّذِيٓ ءَامَنَ يَٰقَوۡمِ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُم مِّثۡلَ يَوۡمِ ٱلۡأَحۡزَابِ

ያም ያመነው ሰው አለ «እኔ በናንተ ላይ የአሕዛቦቹን ቀን ብጤ እፈራላችኋለሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
31 : 40

مِثۡلَ دَأۡبِ قَوۡمِ نُوحٖ وَعَادٖ وَثَمُودَ وَٱلَّذِينَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡۚ وَمَا ٱللَّهُ يُرِيدُ ظُلۡمٗا لِّلۡعِبَادِ

«የኑሕን ሕዝቦች፣ የዓድንና የሰሙድንም፣ የእነዚያንም ከኋላቸው የነበሩትን ልማድ ብጤ (እፈራላችኋለሁ)፡፡ አላህም ለባሮቹ መበደልን የሚሻ አይደለም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 40

وَيَٰقَوۡمِ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ يَوۡمَ ٱلتَّنَادِ

«ወገኖቼ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን እፈራለሁ፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
33 : 40

يَوۡمَ تُوَلُّونَ مُدۡبِرِينَ مَا لَكُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنۡ عَاصِمٖۗ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنۡ هَادٖ

ወደ ኋላ ዞራችሁ በምትሸሹበት ቀን፤ ለናንተ ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ የላችሁም፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡ info
التفاسير: