ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
51 : 30

وَلَئِنۡ أَرۡسَلۡنَا رِيحٗا فَرَأَوۡهُ مُصۡفَرّٗا لَّظَلُّواْ مِنۢ بَعۡدِهِۦ يَكۡفُرُونَ

ነፋስንም (በአዝመራዎች ላይ) ብንልክና ገርጥቶ ቢያዩት ከእርሱ በኋላ በእርግጥ (ችሮታውን) የሚክዱ ይሆናሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
52 : 30

فَإِنَّكَ لَا تُسۡمِعُ ٱلۡمَوۡتَىٰ وَلَا تُسۡمِعُ ٱلصُّمَّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا وَلَّوۡاْ مُدۡبِرِينَ

አንተም ሙታንን አታሰማም፡፡ ደንቆሮዎችንም ዟሪዎች ሆነው በሸሹ ጊዜ ጥሪን አታሰማም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
53 : 30

وَمَآ أَنتَ بِهَٰدِ ٱلۡعُمۡيِ عَن ضَلَٰلَتِهِمۡۖ إِن تُسۡمِعُ إِلَّا مَن يُؤۡمِنُ بِـَٔايَٰتِنَا فَهُم مُّسۡلِمُونَ

አንተ ዕውሮችንም ከጥመታቸው የምታቀና አይደለህም፡፡ በአንቀጾቻችን የሚያምኑትን ሰዎች እንጂ ሌላን አታሰማም፡፡ እነርሱም ታዛዦች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
54 : 30

۞ ٱللَّهُ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن ضَعۡفٖ ثُمَّ جَعَلَ مِنۢ بَعۡدِ ضَعۡفٖ قُوَّةٗ ثُمَّ جَعَلَ مِنۢ بَعۡدِ قُوَّةٖ ضَعۡفٗا وَشَيۡبَةٗۚ يَخۡلُقُ مَا يَشَآءُۚ وَهُوَ ٱلۡعَلِيمُ ٱلۡقَدِيرُ

አላህ ያ ከደካማ (ፍትወት ጠብታ) የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከዚያም ከደካማነት በኋላ ኀይልን አደረገ፡፡ ከዚያም ከብርቱነት በኋላ ደካማነትንና ሽበትን አደረገ፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ እርሱም ዐዋቂው ቻዩ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
55 : 30

وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يُقۡسِمُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ مَا لَبِثُواْ غَيۡرَ سَاعَةٖۚ كَذَٰلِكَ كَانُواْ يُؤۡفَكُونَ

ሰዓቲቱ በምትሆንበት ቀን ከሓዲዎች «ከአንዲት ሰዓት በስተቀር (በመቃብር) አልቆየንም» ብለው ይምላሉ፡፡ እንደዚሁ (ከእውነት) ይመለሱ ነበሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
56 : 30

وَقَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ وَٱلۡإِيمَٰنَ لَقَدۡ لَبِثۡتُمۡ فِي كِتَٰبِ ٱللَّهِ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡبَعۡثِۖ فَهَٰذَا يَوۡمُ ٱلۡبَعۡثِ وَلَٰكِنَّكُمۡ كُنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ

እነዚያንም ዕውቀትንና እምነትን የተሰጡት «በአላህ መጽሐፍ (ፍርድ) እስከ ትንሣኤ ቀን በእርግጥ ቆያችሁ፡፡ ይህም (የካዳችሁት) የትንሣኤ ቀን ነው፡፡ ግን እናንተ የማታውቁ ነበራችሁ» ይሏቸዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 30

فَيَوۡمَئِذٖ لَّا يَنفَعُ ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ مَعۡذِرَتُهُمۡ وَلَا هُمۡ يُسۡتَعۡتَبُونَ

በዚያም ቀን እነዚያን የበደሉትን ማመካኘታቸው አይጠቅማቸውም፡፡ እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 30

وَلَقَدۡ ضَرَبۡنَا لِلنَّاسِ فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٖۚ وَلَئِن جِئۡتَهُم بِـَٔايَةٖ لَّيَقُولَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِنۡ أَنتُمۡ إِلَّا مُبۡطِلُونَ

በዚያም ቁርኣን ውስጥ ከምሳሌ ሁሉ ለሰዎች በእርግጥ ገለጽን፡፡ በተዓምርም ብትመጣባቸው እነዚያ የካዱት ሰዎች «እናንተ አበላሺዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም» ይላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 30

كَذَٰلِكَ يَطۡبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِ ٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَ

እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያውቁት ሰዎች ልቦች ላይ ያትማል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
60 : 30

فَٱصۡبِرۡ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞۖ وَلَا يَسۡتَخِفَّنَّكَ ٱلَّذِينَ لَا يُوقِنُونَ

ስለዚህ ታገስ፡፡ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ እነዚያም በትንሣኤ የማያረጋግጡት አያቅልሉህ፡፡ info
التفاسير: