ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
6 : 30

وَعۡدَ ٱللَّهِۖ لَا يُخۡلِفُ ٱللَّهُ وَعۡدَهُۥ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ

አላህ እርዳታን ቀጠረ፡፡ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 30

يَعۡلَمُونَ ظَٰهِرٗا مِّنَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَهُمۡ عَنِ ٱلۡأٓخِرَةِ هُمۡ غَٰفِلُونَ

ከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ፡፡ እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም እነርሱ ዘንጊዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
8 : 30

أَوَلَمۡ يَتَفَكَّرُواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۗ مَّا خَلَقَ ٱللَّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ وَمَا بَيۡنَهُمَآ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَأَجَلٖ مُّسَمّٗىۗ وَإِنَّ كَثِيرٗا مِّنَ ٱلنَّاسِ بِلِقَآيِٕ رَبِّهِمۡ لَكَٰفِرُونَ

በነፍሶቻቸው (ሁኔታ) አያስተውሉምን? ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ አላህ በእውነትና በተወሰነ ጊዜ እንጂ አልፈጠራቸውም፡፡ ከሰዎቹም ብዙዎቹ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲዎች ናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
9 : 30

أَوَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَانُوٓاْ أَشَدَّ مِنۡهُمۡ قُوَّةٗ وَأَثَارُواْ ٱلۡأَرۡضَ وَعَمَرُوهَآ أَكۡثَرَ مِمَّا عَمَرُوهَا وَجَآءَتۡهُمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِۖ فَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيَظۡلِمَهُمۡ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ

በምድር ላይ አይኼዱምና የእነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ አይመለከቱምን? በኀይል ከእነርሱም ይበልጥ የጠነከሩ ነበሩ፡፡ ምድርንም አረሱ፡፡ (እነዚህ) ከአለሟትም የበዛ አለሟት፡፡ መልዕክተኞቻቸውም በተዓምራቶች መጡባቸው፤ (አስተባበሉምና ጠፉ)፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፤ ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
10 : 30

ثُمَّ كَانَ عَٰقِبَةَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔواْ ٱلسُّوٓأَىٰٓ أَن كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَكَانُواْ بِهَا يَسۡتَهۡزِءُونَ

ከዚያም የእነዚያ ያጠፉት ሰዎች መጨረሻ በአላህ አንቀጾች በማስተባበላቸውና በእርሷ የሚሳለቁ በመኾናቸው ምክንያት መጥፎ ቅጣት ሆነች፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
11 : 30

ٱللَّهُ يَبۡدَؤُاْ ٱلۡخَلۡقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ ثُمَّ إِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ

አላህ መፍጠርን ይጀምራል፡፡ ከዚያም ይመልሰዋል፤ ከዚያም ወደርሱ ትመለሳላችሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
12 : 30

وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يُبۡلِسُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ

ሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
13 : 30

وَلَمۡ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَآئِهِمۡ شُفَعَٰٓؤُاْ وَكَانُواْ بِشُرَكَآئِهِمۡ كَٰفِرِينَ

ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው (ጣዖታት) አማላጆች አይኖሯቸውም፤ በሚያጋሯቸውም (ጣዖታት) ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
14 : 30

وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يَوۡمَئِذٖ يَتَفَرَّقُونَ

ሰዓቲቱ በምትቆምበት ቀንም በዚያ ቀን ይለያያሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
15 : 30

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَهُمۡ فِي رَوۡضَةٖ يُحۡبَرُونَ

እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን ሥራዎች የሠሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ፡፡ info
التفاسير: