ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
50 : 17

۞ قُلۡ كُونُواْ حِجَارَةً أَوۡ حَدِيدًا

በላቸው «ድንጋዮችን ወይም ብረትን ሁኑ» info
التفاسير:

external-link copy
51 : 17

أَوۡ خَلۡقٗا مِّمَّا يَكۡبُرُ فِي صُدُورِكُمۡۚ فَسَيَقُولُونَ مَن يُعِيدُنَاۖ قُلِ ٱلَّذِي فَطَرَكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةٖۚ فَسَيُنۡغِضُونَ إِلَيۡكَ رُءُوسَهُمۡ وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هُوَۖ قُلۡ عَسَىٰٓ أَن يَكُونَ قَرِيبٗا

«ወይም በልቦቻችሁ ውስጥ የሚተልቅን ፍጥረት (ኹኑ መቀስቀሳችሁ አይቀርም)፡፡» «የሚመልሰንም ማነው» ይላሉ፡፡ ያ በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ ነው» በላቸው፡፡ ወደ አንተም ራሶቻቸውን ይነቀንቃሉ፡፡ «እርሱም መቼ ነው» ይላሉ፡፡ «(እርሱ) ቅርብ ሊኾነን ይቻላል በላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
52 : 17

يَوۡمَ يَدۡعُوكُمۡ فَتَسۡتَجِيبُونَ بِحَمۡدِهِۦ وَتَظُنُّونَ إِن لَّبِثۡتُمۡ إِلَّا قَلِيلٗا

(እርሱም) የሚጠራችሁና (አላህን) አመስጋኞቹ ኾናችሁ ጥሪውን የምትቀበሉበት ጥቂትንም (ቀኖች) እንጂ ያልቆያችሁ መኾናችሁን የምትጠራጠሩበት ቀን ነው፤ (በላቸው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
53 : 17

وَقُل لِّعِبَادِي يَقُولُواْ ٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُۚ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ يَنزَغُ بَيۡنَهُمۡۚ إِنَّ ٱلشَّيۡطَٰنَ كَانَ لِلۡإِنسَٰنِ عَدُوّٗا مُّبِينٗا

ለባሮቼም በላቸው፡- ያችን እርሷ መልካም የኾነችውን (ቃል) ይናገሩ፡፡ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና፡፡ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
54 : 17

رَّبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِكُمۡۖ إِن يَشَأۡ يَرۡحَمۡكُمۡ أَوۡ إِن يَشَأۡ يُعَذِّبۡكُمۡۚ وَمَآ أَرۡسَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ وَكِيلٗا

ጌታችሁ በእናንተ (ኹኔታ) ዐዋቂ ነው፡፡ ቢሻ ያዝንላችኋል፤ ወይም ቢሻ ይቀጣችኋል፡፡ በእነሱም ላይ ኃላፊ ኾነህ አላክንህም፡፡ (አታስገድዳቸውም)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
55 : 17

وَرَبُّكَ أَعۡلَمُ بِمَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَلَقَدۡ فَضَّلۡنَا بَعۡضَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ عَلَىٰ بَعۡضٖۖ وَءَاتَيۡنَا دَاوُۥدَ زَبُورٗا

ጌታህም በሰማያትና በምድር ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ ከፊሉንም ነቢያት በከፊሉ ላይ በእርግጥ አብልጠናል፡፡ ዳውድንም ዘቡርን ሰጥተነዋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
56 : 17

قُلِ ٱدۡعُواْ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُم مِّن دُونِهِۦ فَلَا يَمۡلِكُونَ كَشۡفَ ٱلضُّرِّ عَنكُمۡ وَلَا تَحۡوِيلًا

«እነዚያን ከእርሱ ሌላ (አማልክት) የምትሏቸውን ጥሩ፡፡ ከእናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን (ወደ ሌላ) ማዞርንም አይችሉም» በላቸው፡፤ info
التفاسير:

external-link copy
57 : 17

أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ يَبۡتَغُونَ إِلَىٰ رَبِّهِمُ ٱلۡوَسِيلَةَ أَيُّهُمۡ أَقۡرَبُ وَيَرۡجُونَ رَحۡمَتَهُۥ وَيَخَافُونَ عَذَابَهُۥٓۚ إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ كَانَ مَحۡذُورٗا

እነዚያ እነርሱ የሚግገዟቸው ማንኛቸውም (ወደ አላህ) በጣም ቀራቢያቸው ወደ ጌታቸው መቃረቢያን (ሥራ) ይፈልጋሉ፡፡ እዝነቱንም ይከጅላሉ፡፡ ቅጣቱንም ይፈራሉ፡፡ የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 17

وَإِن مِّن قَرۡيَةٍ إِلَّا نَحۡنُ مُهۡلِكُوهَا قَبۡلَ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ أَوۡ مُعَذِّبُوهَا عَذَابٗا شَدِيدٗاۚ كَانَ ذَٰلِكَ فِي ٱلۡكِتَٰبِ مَسۡطُورٗا

አንዲትም ከተማ የለችም እኛ ከትንሣኤ ቀን በፊት አጥፊዎችዋ ወይም ብርቱን ቅጣት ቀጭዎችዋ ብንኾን እንጂ፡፡ ይህ በመጽሐፉ ውስጥ የተጻፈ ነው፡፡ info
التفاسير: