ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
97 : 17

وَمَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَلَن تَجِدَ لَهُمۡ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِهِۦۖ وَنَحۡشُرُهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمۡ عُمۡيٗا وَبُكۡمٗا وَصُمّٗاۖ مَّأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ كُلَّمَا خَبَتۡ زِدۡنَٰهُمۡ سَعِيرٗا

አላህም ያቀናው ሰው ቅኑ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ያጠመማቸውም ሰዎች ከእርሱ ሌላ ለእነርሱ ፈጽሞ ረዳት አታገኝላቸውም፡፡ በትንሣኤ ቀንም ዕውሮች፣ ዲዳዎችም ደንቆሮዎችም ኾነው በፊቶቻቸው ላይ (እየተጎተቱ) እንሰበስባቸዋለን፡፡ መኖሪያቸው ገሀነም ናት፡፡ (ነዲድዋ) በደከመች ቁጥር መንቀልቀልን እንጨምርባቸዋለን፡፤ info
التفاسير:

external-link copy
98 : 17

ذَٰلِكَ جَزَآؤُهُم بِأَنَّهُمۡ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِنَا وَقَالُوٓاْ أَءِذَا كُنَّا عِظَٰمٗا وَرُفَٰتًا أَءِنَّا لَمَبۡعُوثُونَ خَلۡقٗا جَدِيدًا

ይህ (ቅጣት)፤ እነርሱ በአንቀጾቻችን ስለ ካዱና «አጥንቶችና ብስብሶች በኾን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት ኾነን ተቀስቃሾች ነን?» ስላሉም ፍዳቸው ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
99 : 17

۞ أَوَلَمۡ يَرَوۡاْ أَنَّ ٱللَّهَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ قَادِرٌ عَلَىٰٓ أَن يَخۡلُقَ مِثۡلَهُمۡ وَجَعَلَ لَهُمۡ أَجَلٗا لَّا رَيۡبَ فِيهِ فَأَبَى ٱلظَّٰلِمُونَ إِلَّا كُفُورٗا

ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ አላህ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ መኾኑን በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበትም ጊዜ (ለሞትም ለትንሣኤም) ለእነርሱ የወሰነ መኾኑን አላወቁምን? በደለኞችም ከክህደት በቀር እምቢ አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
100 : 17

قُل لَّوۡ أَنتُمۡ تَمۡلِكُونَ خَزَآئِنَ رَحۡمَةِ رَبِّيٓ إِذٗا لَّأَمۡسَكۡتُمۡ خَشۡيَةَ ٱلۡإِنفَاقِۚ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ قَتُورٗا

«እናንተ የጌታዬን የችሮታ መካዚኖች ብትይዙ ኖሮ ያን ጊዜ በማውጣታችሁ (ማለቋን) በመፍራት በጨበጣችሁ ነበር፡፡ ሰውም በጣም ቆጣቢ ነው፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
101 : 17

وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَىٰ تِسۡعَ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖۖ فَسۡـَٔلۡ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ إِذۡ جَآءَهُمۡ فَقَالَ لَهُۥ فِرۡعَوۡنُ إِنِّي لَأَظُنُّكَ يَٰمُوسَىٰ مَسۡحُورٗا

ለሙሳም ግልጽ የኾኑን ዘጠኝ ተዓምራቶች በእርግጥ ሰጠነው፡፡ በመጣቸውም ጊዜ የእስራኤልን ልጆች (ከፈርዖን እንዲለቀቁ) ጠይቅ (አልነው)፡፡ ፈርዖንም «ሙሳ ሆይ! እኔ የተደገመብህ መኾንህን በእርግጥ እጠረጥራለሁ» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
102 : 17

قَالَ لَقَدۡ عَلِمۡتَ مَآ أَنزَلَ هَٰٓؤُلَآءِ إِلَّا رَبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ بَصَآئِرَ وَإِنِّي لَأَظُنُّكَ يَٰفِرۡعَوۡنُ مَثۡبُورٗا

(ሙሳም) «እነዚህን (ተዓምራቶች) መገሰጫዎች ሲኾኑ የሰማያትና የምድር ጌታ እንጂ ሌላ እንዳላወረዳቸው በእርግጥ ዐውቀሃል፡፡ እኔም ፈርዖን ሆይ! የምትጠፋ መኾንህን በእርግጥ እጠረጥርሃለሁ» አለው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
103 : 17

فَأَرَادَ أَن يَسۡتَفِزَّهُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ فَأَغۡرَقۡنَٰهُ وَمَن مَّعَهُۥ جَمِيعٗا

ከምድርም ሊቀሰቅሳቸው አሰበ፡፡ እርሱንና ከእርሱ ጋር የነበሩትንም ሰዎች ሁሉንም አሰጠምናቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
104 : 17

وَقُلۡنَا مِنۢ بَعۡدِهِۦ لِبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ ٱسۡكُنُواْ ٱلۡأَرۡضَ فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ ٱلۡأٓخِرَةِ جِئۡنَا بِكُمۡ لَفِيفٗا

ከእርሱም በኋላ ለእሰራኤል ልጆች «ምድሪቱን ተቀመጡባት የኋለኛይቱም (ሰዓት) ቀጠሮ በመጣ ጊዜ እናንተን የተከማቻችሁ ስትኾኑ እናመጣችኋለን» አልናቸው፡፡ info
التفاسير: