ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
27 : 16

ثُمَّ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ يُخۡزِيهِمۡ وَيَقُولُ أَيۡنَ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ كُنتُمۡ تُشَٰٓقُّونَ فِيهِمۡۚ قَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ إِنَّ ٱلۡخِزۡيَ ٱلۡيَوۡمَ وَٱلسُّوٓءَ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ

ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል፡፡ እነዚያም «በእነሱ (ጉዳይ) ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው» ይላቸዋል፡፡ «እነዚያ ዕውቀትን የተሰጡት ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በእርግጥ በከሓዲዎች ላይ ነው» ይላሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
28 : 16

ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ ظَالِمِيٓ أَنفُسِهِمۡۖ فَأَلۡقَوُاْ ٱلسَّلَمَ مَا كُنَّا نَعۡمَلُ مِن سُوٓءِۭۚ بَلَىٰٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمُۢ بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

(እነርሱ) «እነዚያ ነፍሶቻቸውን በዳይ ኾነው መላእክት የሚገድሏቸው ናቸው፡፡ ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርን» (ሲሉ) ታዛዥነታቸውን ይገልጻሉ፡፡ «በእውነት አላህ ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ዐዋቂ ነው» (ይባላሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
29 : 16

فَٱدۡخُلُوٓاْ أَبۡوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ فَلَبِئۡسَ مَثۡوَى ٱلۡمُتَكَبِّرِينَ

«የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ ግቡ» (ይባላሉ)፡፡ የኩሩዎችም መኖሪያ (ገሀነም) በእርግጥ ከፋች! info
التفاسير:

external-link copy
30 : 16

۞ وَقِيلَ لِلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ مَاذَآ أَنزَلَ رَبُّكُمۡۚ قَالُواْ خَيۡرٗاۗ لِّلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٞۚ وَلَدَارُ ٱلۡأٓخِرَةِ خَيۡرٞۚ وَلَنِعۡمَ دَارُ ٱلۡمُتَّقِينَ

ለእነዚያም ለተጠነቀቁት «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ» ተባሉ፡፡ «መልካምን ነገር» አሉ፡፡ ለእነዚያ ደግ ለሠሩት በዚሀች በቅርቢቱ ዓለም መልካም (ኑሮ) አላቸው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ የጥንቁቆቹም አገር ምን ታምር! info
التفاسير:

external-link copy
31 : 16

جَنَّٰتُ عَدۡنٖ يَدۡخُلُونَهَا تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ لَهُمۡ فِيهَا مَا يَشَآءُونَۚ كَذَٰلِكَ يَجۡزِي ٱللَّهُ ٱلۡمُتَّقِينَ

(እርሷም) የሚገቡዋትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትኾን የመኖሪያ ገነቶች (አትክልቶች) ናት፡፡ ለእነሱም በወስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
32 : 16

ٱلَّذِينَ تَتَوَفَّىٰهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ طَيِّبِينَ يَقُولُونَ سَلَٰمٌ عَلَيۡكُمُ ٱدۡخُلُواْ ٱلۡجَنَّةَ بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚገድሏቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» (ይባላሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
33 : 16

هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَوۡ يَأۡتِيَ أَمۡرُ رَبِّكَۚ كَذَٰلِكَ فَعَلَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۚ وَمَا ظَلَمَهُمُ ٱللَّهُ وَلَٰكِن كَانُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ يَظۡلِمُونَ

(ከሓዲዎች) መላእክት ወደ እነሱ መምጣትን ወይም የጌታህ ትእዛዝ መምጣቱን እንጂ አይጠባበቁም፡፡ ከእነሱ በፊት የነበሩት እንደዚህ ሠርተዋል፡፡ አላህም አልበደላቸውም፤ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
34 : 16

فَأَصَابَهُمۡ سَيِّـَٔاتُ مَا عَمِلُواْ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ

የሠሩዋቸውም ኀጢአቶች (ቅጣት) አገኛቸው፡፡ በእርሱም ይሳለቁበት የነበሩት ሁሉ በነሱ ላይ ወረደባቸው፡፡ info
التفاسير: