ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - ម៉ូហាំម៉ាត់​ សរទីក

លេខ​ទំព័រ:close

external-link copy
88 : 16

ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ زِدۡنَٰهُمۡ عَذَابٗا فَوۡقَ ٱلۡعَذَابِ بِمَا كَانُواْ يُفۡسِدُونَ

እነዚያ የካዱ፣ ከአላህም መንገድ የከለከሉ ያጠፉ በነበሩት ምክንያት ቅጣትን በቅጣት ላይ ጨመርንባቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
89 : 16

وَيَوۡمَ نَبۡعَثُ فِي كُلِّ أُمَّةٖ شَهِيدًا عَلَيۡهِم مِّنۡ أَنفُسِهِمۡۖ وَجِئۡنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَٰٓؤُلَآءِۚ وَنَزَّلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ تِبۡيَٰنٗا لِّكُلِّ شَيۡءٖ وَهُدٗى وَرَحۡمَةٗ وَبُشۡرَىٰ لِلۡمُسۡلِمِينَ

በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ከጎሳቸው በእነሱ ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን አንተንም በእነዚህ (ሕዝቦች) ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣህን ቀን (አስታውስ)፡፡ መጽሐፉንም ለሁሉ ነገር አብራሪ፣ መሪም፣ እዝነትም፣ ለሙስሊሞችም አብሳሪ ኾኖ ባንተ ላይ አወረድነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
90 : 16

۞ إِنَّ ٱللَّهَ يَأۡمُرُ بِٱلۡعَدۡلِ وَٱلۡإِحۡسَٰنِ وَإِيتَآيِٕ ذِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَيَنۡهَىٰ عَنِ ٱلۡفَحۡشَآءِ وَٱلۡمُنكَرِ وَٱلۡبَغۡيِۚ يَعِظُكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ

አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
91 : 16

وَأَوۡفُواْ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ إِذَا عَٰهَدتُّمۡ وَلَا تَنقُضُواْ ٱلۡأَيۡمَٰنَ بَعۡدَ تَوۡكِيدِهَا وَقَدۡ جَعَلۡتُمُ ٱللَّهَ عَلَيۡكُمۡ كَفِيلًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ يَعۡلَمُ مَا تَفۡعَلُونَ

ቃል ኪዳንም በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላ አላህን በእናንተ ላይ በእርግጥ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትኾኑ አታፍርሱ፡፡ አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
92 : 16

وَلَا تَكُونُواْ كَٱلَّتِي نَقَضَتۡ غَزۡلَهَا مِنۢ بَعۡدِ قُوَّةٍ أَنكَٰثٗا تَتَّخِذُونَ أَيۡمَٰنَكُمۡ دَخَلَۢا بَيۡنَكُمۡ أَن تَكُونَ أُمَّةٌ هِيَ أَرۡبَىٰ مِنۡ أُمَّةٍۚ إِنَّمَا يَبۡلُوكُمُ ٱللَّهُ بِهِۦۚ وَلَيُبَيِّنَنَّ لَكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ مَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ

(ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ አንዲቱ) ሕዝብ እርሷ ከ(ሌላይቱ) ሕዝብ የበዛች ለመኾንዋ በመካከላችሁ መሓሎቻችሁን (ለክዳት) መግቢያ አድርጋችሁ የምትይዙ ስትኾኑ እንደዚያች ፈትልዋን ከጠነከረ በኋላ ትርትሮች አድርጋ እንዳፈረሰችው (ሴት) አትኹኑ፡፡ አላህ በእርሱ ይሞክራችኋል፤ በትንሣኤ ቀንም በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር ለእናንተ በእርግጥ ያብራራላችኋል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
93 : 16

وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ لَجَعَلَكُمۡ أُمَّةٗ وَٰحِدَةٗ وَلَٰكِن يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِي مَن يَشَآءُۚ وَلَتُسۡـَٔلُنَّ عَمَّا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ

አላህም በሻ ኖሮ አንዲት ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር፡፡ ግን የሚሻውን ሰው ያጠማል፡፡ የሚሻውንም ሰው ያቀናል፡፡ ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ፡፡ info
التفاسير: