クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー

አት ተጋቡን

external-link copy
1 : 64

يُسَبِّحُ لِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِۖ لَهُ ٱلۡمُلۡكُ وَلَهُ ٱلۡحَمۡدُۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ

1. በሰማያት ውስጥም ሆነ በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ አላህን ያሞግሳል:: ንግስናው የእርሱ ብቻ ነው:: ምስጋናም ለእርሱ ብቻ ነው:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 64

هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُمۡ فَمِنكُمۡ كَافِرٞ وَمِنكُم مُّؤۡمِنٞۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٌ

2. እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው:: ከእናንተም መካከል ከሓዲ አለ:: ከእናተም መካከል አማኝ አለ:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 64

خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّ وَصَوَّرَكُمۡ فَأَحۡسَنَ صُوَرَكُمۡۖ وَإِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ

3. (እርሱ) ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ:: ቀረጻችሁም ቅርጻችሁንም አሳመረ፡፡ መመለሻችሁም ወደ እርሱ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 64

يَعۡلَمُ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَيَعۡلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعۡلِنُونَۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

4. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል:: የምትደብቋትንም ሆነ የምትገልጡትን ያውቃል:: አላህም በልቦች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 64

أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ نَبَؤُاْ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ مِن قَبۡلُ فَذَاقُواْ وَبَالَ أَمۡرِهِمۡ وَلَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ

5. የእነዚያ ከአሁን በፊት የካዱትና የክህደታቸውን ቅጣት የቀመሱ ህዝቦች ወሬ አልመጣላችሁምን? ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 64

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُۥ كَانَت تَّأۡتِيهِمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَقَالُوٓاْ أَبَشَرٞ يَهۡدُونَنَا فَكَفَرُواْ وَتَوَلَّواْۖ وَّٱسۡتَغۡنَى ٱللَّهُۚ وَٱللَّهُ غَنِيٌّ حَمِيدٞ

6. ይህ (ቅጣት) እነርሱ መልዕክተኞቻቸው አስረጂዎችን ይዘው ሲመጡላቸው «ሰዎች ይመሩናልን?» ስላሉና ስለ ካዱ፤ ከእምነትም ስለ ዞሩ ነው:: አላህ ከእነርሱ እምነት ተብቃቃ:: አላህ ተብቃቂና ምስጉን ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 64

زَعَمَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَن لَّن يُبۡعَثُواْۚ قُلۡ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتُبۡعَثُنَّ ثُمَّ لَتُنَبَّؤُنَّ بِمَا عَمِلۡتُمۡۚ وَذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ يَسِيرٞ

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች በፍጹም የማይቀሰቀሱ መሆናቸውን አሰቡ። «(እንዴት አትቀሰቀሱም?) በጌታየ ይሁንብኝ ትቀሰቀሳላችሁ:: ከዚያ ትፈጽሙት የነበረውን ተግባራችሁን ትናገራላችሁ:: ይህ ተግባር ለአላህ ቀላል ነው» በላቸው። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 64

فَـَٔامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱلنُّورِ ٱلَّذِيٓ أَنزَلۡنَاۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ

8. በአላህ በመልዕክተኛውና በዚያም ባወረድነው ብርሃን እመኑም:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 64

يَوۡمَ يَجۡمَعُكُمۡ لِيَوۡمِ ٱلۡجَمۡعِۖ ذَٰلِكَ يَوۡمُ ٱلتَّغَابُنِۗ وَمَن يُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ وَيَعۡمَلۡ صَٰلِحٗا يُكَفِّرۡ عَنۡهُ سَيِّـَٔاتِهِۦ وَيُدۡخِلۡهُ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ

9. (ይኸዉም) ለመሰብሰቢያው ቀን የሚሰበስባችሁ እለት አስታውሱ:: ይህ ቀን የቁጭት ቀን ነው:: በአላህም የሚያምን ሰው መልካምንም የሚሠራ ከርሱ ኃጢአቶቹን ይሰርይለታል፤ (ይፍቅለታል)፤ ከስሮቿ ወንዞች የሚፈሱባት ገነቶች ለዘላለም ያስገባዋል:: ይህ ታላቅ እደለኝነት ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 64

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَكَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَآ أُوْلَٰٓئِكَ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ

10. እነዚያም የካዱትና በአንቀፆቻችንም ያስተባበሉት የዝንታለም እሳት ባለቤቶች ማለት እነርሱ ናቸው:: (ጀሀነም) መመለሻነቷ ምን ይከፋ! info
التفاسير:

external-link copy
11 : 64

مَآ أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَمَن يُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ يَهۡدِ قَلۡبَهُۥۚ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٞ

11. ከመከራም በአላህ ፈቃድ ቢሆን እንጂ ማንንም አይነካም:: በአላህ የሚያምን ሰው አላህ ልቡን ለትግስት ይመራዋል:: አላህም በሁሉም ነገር አዋቂ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
12 : 64

وَأَطِيعُواْ ٱللَّهَ وَأَطِيعُواْ ٱلرَّسُولَۚ فَإِن تَوَلَّيۡتُمۡ فَإِنَّمَا عَلَىٰ رَسُولِنَا ٱلۡبَلَٰغُ ٱلۡمُبِينُ

12. አላህን ታዘዙ መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: ብትዞሩም (መልዕክተኛውን አትጎዱም::) በመልዕክተኛችንም ላይ ያለበት በግልጽ ማድረስ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
13 : 64

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ

13. አላህ ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: ትክክለኛ አማኞች በአላህ ብቻ ይመኩ:: info
التفاسير:

external-link copy
14 : 64

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِنَّ مِنۡ أَزۡوَٰجِكُمۡ وَأَوۡلَٰدِكُمۡ عَدُوّٗا لَّكُمۡ فَٱحۡذَرُوهُمۡۚ وَإِن تَعۡفُواْ وَتَصۡفَحُواْ وَتَغۡفِرُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٞ رَّحِيمٌ

14. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለእናንተ ጠላቶች የሆኑ አሉ:: ስለዚህ ተጠንቀቋቸው:: ይቅርታ ብታደርጉ፤ ብታልፏቸዉም፤ ብትምሩዋቸዉም፤ አላህ በጣም መሀሪ፤ አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
15 : 64

إِنَّمَآ أَمۡوَٰلُكُمۡ وَأَوۡلَٰدُكُمۡ فِتۡنَةٞۚ وَٱللَّهُ عِندَهُۥٓ أَجۡرٌ عَظِيمٞ

15. ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለእናንተ መፈተኛ ብቻ ናቸው:: አላህም ከእርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
16 : 64

فَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ مَا ٱسۡتَطَعۡتُمۡ وَٱسۡمَعُواْ وَأَطِيعُواْ وَأَنفِقُواْ خَيۡرٗا لِّأَنفُسِكُمۡۗ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفۡسِهِۦ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ

16. አላህንም የቻላችሁትን ያህል ፍሩት:: ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ይሰጣችኋልና:: የነፍሶቻቸዉን ንፍገት የሚጠበቁ ሰዎች ሁሉ እነዚያ እነርሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
17 : 64

إِن تُقۡرِضُواْ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗا يُضَٰعِفۡهُ لَكُمۡ وَيَغۡفِرۡ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ شَكُورٌ حَلِيمٌ

17. ለአላህ መልካም ብድርን ብታበድሩት (ምንዳውን) ለእናንተ ይደራርበዋል:: ለእናንተም ይምራል:: አላህ አመስጋኝና ታጋሽ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
18 : 64

عَٰلِمُ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

18. (እርሱ) ስውሩንም ይፋዉንም ሁሉን አዋቂ ኃያልና ጥበበኛ ነዉና። info
التفاسير: