クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー

ሙሀመድ

external-link copy
1 : 47

ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَصَدُّواْ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ أَضَلَّ أَعۡمَٰلَهُمۡ

1. እነዚያ የካዱ እና ከአላህ መንገድ ሌሎችን የከለከሉ አላህ ስራዎቻቸውን አጠፋባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 47

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَءَامَنُواْ بِمَا نُزِّلَ عَلَىٰ مُحَمَّدٖ وَهُوَ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّهِمۡ كَفَّرَ عَنۡهُمۡ سَيِّـَٔاتِهِمۡ وَأَصۡلَحَ بَالَهُمۡ

2. እነዚያም ያመኑ በጎዎችንም ተግባራት የሰሩ በሙሐመድ ላይም የተወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት ስለሆነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያብሳል:: ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 47

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱتَّبَعُواْ ٱلۡبَٰطِلَ وَأَنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّبَعُواْ ٱلۡحَقَّ مِن رَّبِّهِمۡۚ كَذَٰلِكَ يَضۡرِبُ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ أَمۡثَٰلَهُمۡ

3.ይህ እነዚያ የካዱት ውሸትን የተከተሉ በመሆናቸውና እነዚያም ያመኑት ከጌታቸው የሆነን እውነት ስለተከተሉ ነው:: ልክ እንደዚሁ አላህ ለሰዎች ምሳሌዎቻቸውን ያብራራል። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 47

فَإِذَا لَقِيتُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَضَرۡبَ ٱلرِّقَابِ حَتَّىٰٓ إِذَآ أَثۡخَنتُمُوهُمۡ فَشُدُّواْ ٱلۡوَثَاقَ فَإِمَّا مَنَّۢا بَعۡدُ وَإِمَّا فِدَآءً حَتَّىٰ تَضَعَ ٱلۡحَرۡبُ أَوۡزَارَهَاۚ ذَٰلِكَۖ وَلَوۡ يَشَآءُ ٱللَّهُ لَٱنتَصَرَ مِنۡهُمۡ وَلَٰكِن لِّيَبۡلُوَاْ بَعۡضَكُم بِبَعۡضٖۗ وَٱلَّذِينَ قُتِلُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ فَلَن يُضِلَّ أَعۡمَٰلَهُمۡ

4. አማኞች ሆይ! እነዚያንም የካዱትን ሰዎች በጦር ላይ ባገኛችኋቸው ጊዜ ጫንቃዎችን በሀይል ምቱ:: ባደከማችኋቸው ጊዜም አትግደሏቸው፤ ማርኳቸው:: መሳሪያውንም አጥብቁ:: በኋላም በነጻ ትለቋቸዋላችሁ:: ወይም ፊዳ ታስከፍሏቸዋላችሁ:: ይህም ጦሩ መሳሪያዉን እስከሚጥል ድረስ ነው:: ነገሩ ይህ ነው:: አላህም ቢፈልግ ከእነርሱ ያለ ጦር በተበቀለ ነበር ግን ከፊላችሁን በከፊሉ ሊሞክር (በዚህ አዘዛችሁ)። እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉት ሰዎች ስራዎቻቸውን ፈጽሞ አያጠፋባቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 47

سَيَهۡدِيهِمۡ وَيُصۡلِحُ بَالَهُمۡ

5. በእርግጥ ይመራቸዋል:: ሁኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 47

وَيُدۡخِلُهُمُ ٱلۡجَنَّةَ عَرَّفَهَا لَهُمۡ

6. ገነትንም ያገባቸዋል፡፡ ለእነርሱ አስታውቋታል፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
7 : 47

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن تَنصُرُواْ ٱللَّهَ يَنصُرۡكُمۡ وَيُثَبِّتۡ أَقۡدَامَكُمۡ

7. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህን ሃይማኖት ብትረዱ ይረዳችኋል:: ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል።ያጸናላችኋል። info
التفاسير:

external-link copy
8 : 47

وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَتَعۡسٗا لَّهُمۡ وَأَضَلَّ أَعۡمَٰلَهُمۡ

8. እነዚያም የካዱት ለእነርሱ ጥፋት ተገባቸው:: ስራዎቻቸውንም አጠፋባቸው። info
التفاسير:

external-link copy
9 : 47

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَرِهُواْ مَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ فَأَحۡبَطَ أَعۡمَٰلَهُمۡ

9. ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው:: ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 47

۞ أَفَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡۖ دَمَّرَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡۖ وَلِلۡكَٰفِرِينَ أَمۡثَٰلُهَا

10. የእነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩ ከሓዲያን ሁሉ መጨረሻ እንዴት እንደነበር ያዩ ዘንድ በምድር ላይ አልሄዱምን? አላህ ያላቸውን ሁሉ አጠፋባቸው። ለካሓዲያንም ሁሉ የዚሁ ተመሳሳይ አለባቸው። info
التفاسير:

external-link copy
11 : 47

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ مَوۡلَى ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَأَنَّ ٱلۡكَٰفِرِينَ لَا مَوۡلَىٰ لَهُمۡ

11. ይህ አላህ የእነዚያ ያመኑት ረዳት ስለሆነና ከሓዲያንም ለእነርሱ ረዳት ስሌላቸው ነው:: info
التفاسير: