クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー

ፋጢር

external-link copy
1 : 35

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ جَاعِلِ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةِ رُسُلًا أُوْلِيٓ أَجۡنِحَةٖ مَّثۡنَىٰ وَثُلَٰثَ وَرُبَٰعَۚ يَزِيدُ فِي ٱلۡخَلۡقِ مَا يَشَآءُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ

1. ምስጋና ሁሉ ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፤ መላእክትንም ባለ ሁለት ሁለት፤ ባለ ሶስት ሶስትና ባለ አራት አራት ክንፎች የሆኑ መላዕክተኞች አድራጊ ለሆነው አላህ ይገባው:: በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
2 : 35

مَّا يَفۡتَحِ ٱللَّهُ لِلنَّاسِ مِن رَّحۡمَةٖ فَلَا مُمۡسِكَ لَهَاۖ وَمَا يُمۡسِكۡ فَلَا مُرۡسِلَ لَهُۥ مِنۢ بَعۡدِهِۦۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ

2. አላህ ለሰዎች ከችሮታ የሚከፍታትን ለእርሷ ምንም አጋጅ የላትም:: የሚያግደዉም ከእርሱ በኋላ ለእርሱ ምንም ለቃቂ የለዉም:: እርሱ ብቸኛ አሸናፊና ጥበበኛ ው ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
3 : 35

يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱذۡكُرُواْ نِعۡمَتَ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡۚ هَلۡ مِنۡ خَٰلِقٍ غَيۡرُ ٱللَّهِ يَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَأَنَّىٰ تُؤۡفَكُونَ

3. እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ (ያለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ ከአላህ ሌላ ፈጣሪ አለን? ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አለን? ከእርሱ በስተቀር አምላክ (ሰጪም) የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ፡፡ info
التفاسير: