クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー

ページ番号:close

external-link copy
78 : 28

قَالَ إِنَّمَآ أُوتِيتُهُۥ عَلَىٰ عِلۡمٍ عِندِيٓۚ أَوَلَمۡ يَعۡلَمۡ أَنَّ ٱللَّهَ قَدۡ أَهۡلَكَ مِن قَبۡلِهِۦ مِنَ ٱلۡقُرُونِ مَنۡ هُوَ أَشَدُّ مِنۡهُ قُوَّةٗ وَأَكۡثَرُ جَمۡعٗاۚ وَلَا يُسۡـَٔلُ عَن ذُنُوبِهِمُ ٱلۡمُجۡرِمُونَ

78. «(ሀብትን) የተሰጠሁት እኔ ዘንድ ባለው እውቀት ነው።» አለ። አላህ ከእርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች በኃይል ከእርሱ ይበልጥ የበረቱትን ሀብትን በመሰብሰብም ይበልጥ የበዙትን በእርግጥ ያጠፋ መሆኑን አያውቅምን? አመጸኞችም ከኃጢአቶቻቸው ጥያቄ አይጠየቁም። info
التفاسير:

external-link copy
79 : 28

فَخَرَجَ عَلَىٰ قَوۡمِهِۦ فِي زِينَتِهِۦۖ قَالَ ٱلَّذِينَ يُرِيدُونَ ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا يَٰلَيۡتَ لَنَا مِثۡلَ مَآ أُوتِيَ قَٰرُونُ إِنَّهُۥ لَذُو حَظٍّ عَظِيمٖ

79. በህዝቦቹም ላይ በጌጡ ውስጥ ሆኖ ወጣ:: እነዚያ ቅርቢቱን ህይወት የሚፈልጉት «ወይ ምኞታችን! ቃሩን የተሰጠው ቢጤ ምነው ለእኛ በኖረን፤ እርሱ የታላቅ ዕድል ባለቤት ነውና።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
80 : 28

وَقَالَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡعِلۡمَ وَيۡلَكُمۡ ثَوَابُ ٱللَّهِ خَيۡرٞ لِّمَنۡ ءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗاۚ وَلَا يُلَقَّىٰهَآ إِلَّا ٱلصَّٰبِرُونَ

80. እነዚያም ዕውቀትን የተሰጡት «ወዮላችሁ! የአላህ ምንዳ ላመነ ሰው መልካምንም ለሰራ በላጭ ነው:: ታጋሾችም እንጂ ሌላው አያገኛትም።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
81 : 28

فَخَسَفۡنَا بِهِۦ وَبِدَارِهِ ٱلۡأَرۡضَ فَمَا كَانَ لَهُۥ مِن فِئَةٖ يَنصُرُونَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُنتَصِرِينَ

81. በእርሱም በቤትም ምድርን ደረባን (አሰጠምን):: ለእርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ቡድኖች ምንም አልነበሩትም:: ከሚረዱትም አልነበረም:: info
التفاسير:

external-link copy
82 : 28

وَأَصۡبَحَ ٱلَّذِينَ تَمَنَّوۡاْ مَكَانَهُۥ بِٱلۡأَمۡسِ يَقُولُونَ وَيۡكَأَنَّ ٱللَّهَ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦ وَيَقۡدِرُۖ لَوۡلَآ أَن مَّنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡنَا لَخَسَفَ بِنَاۖ وَيۡكَأَنَّهُۥ لَا يُفۡلِحُ ٱلۡكَٰفِرُونَ

82. እነዚያም በትላንትናው ቀን ስፍራውን ይመኙ የነበሩት «ወይ ጉድ! ለካ አላህ ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ሲሳይን ያሰፋል:: ያጠባልም:: አላህ በእኛ ላይ በእምነት ባልለገሰልን ኖሮ ምድርን በእኛ ላይ በገለበጠብን ነበር:: ወይ ጉድ! ከሓዲያን አይድኑም።» የሚሉ ሆነው አነጉ። info
التفاسير:

external-link copy
83 : 28

تِلۡكَ ٱلدَّارُ ٱلۡأٓخِرَةُ نَجۡعَلُهَا لِلَّذِينَ لَا يُرِيدُونَ عُلُوّٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَلَا فَسَادٗاۚ وَٱلۡعَٰقِبَةُ لِلۡمُتَّقِينَ

83. ይህች የመጨረሻይቱ አገር ናት:: ለእነዚያ በምድር ውስጥ ኩራትንና ማመጽን ለማይፈልጉት ሁሉ እናደርጋታለን:: ምስጉኒቱም መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ብቻ ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
84 : 28

مَن جَآءَ بِٱلۡحَسَنَةِ فَلَهُۥ خَيۡرٞ مِّنۡهَاۖ وَمَن جَآءَ بِٱلسَّيِّئَةِ فَلَا يُجۡزَى ٱلَّذِينَ عَمِلُواْ ٱلسَّيِّـَٔاتِ إِلَّا مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ

84. በደግ ስራ የመጣ ለእርሱ ከእርሷ በላጭ ምንዳ አለው:: በክፉም ስራ የመጡ እነዚህ መጥፎዎችን የሰሩ ይሰሩት የነበሩትን እንጂ አይመነዱም:: info
التفاسير: