クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー

ページ番号:close

external-link copy
61 : 26

فَلَمَّا تَرَٰٓءَا ٱلۡجَمۡعَانِ قَالَ أَصۡحَٰبُ مُوسَىٰٓ إِنَّا لَمُدۡرَكُونَ

61. ሁለቱ ቡድኖችም በተያዩ ጊዜ የሙሳ ጓዶች «እኛ (የፈርዖን ሰዎች) የሚደርሱብን ነን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
62 : 26

قَالَ كَلَّآۖ إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهۡدِينِ

62. ሙሳ «በፍፁም! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። በእርግጥ ይመራኛል።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
63 : 26

فَأَوۡحَيۡنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنِ ٱضۡرِب بِّعَصَاكَ ٱلۡبَحۡرَۖ فَٱنفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرۡقٖ كَٱلطَّوۡدِ ٱلۡعَظِيمِ

63. ወደ ሙሳም «ባህሩን በበትርህ ምታው።» ስንል ላክንበት:: ከዚያ መታውና ተከፈለ፤ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ሆነ:: info
التفاسير:

external-link copy
64 : 26

وَأَزۡلَفۡنَا ثَمَّ ٱلۡأٓخَرِينَ

64. እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን:: info
التفاسير:

external-link copy
65 : 26

وَأَنجَيۡنَا مُوسَىٰ وَمَن مَّعَهُۥٓ أَجۡمَعِينَ

65. ሙሳንና ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳን:: info
التفاسير:

external-link copy
66 : 26

ثُمَّ أَغۡرَقۡنَا ٱلۡأٓخَرِينَ

66. ከዚያም ሌሎቹን አሰመጥን:: info
التفاسير:

external-link copy
67 : 26

إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَةٗۖ وَمَا كَانَ أَكۡثَرُهُم مُّؤۡمِنِينَ

67. በዚህ ውስጥ ታላቅ ተዐምር አለበት፤ አብዛሀኞቻቸዉም ትክክለኛ አማኞች አልነበሩም። info
التفاسير:

external-link copy
68 : 26

وَإِنَّ رَبَّكَ لَهُوَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلرَّحِيمُ

68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላህ እርሱ አሸናፊና አዛኝ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
69 : 26

وَٱتۡلُ عَلَيۡهِمۡ نَبَأَ إِبۡرَٰهِيمَ

69. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም (በህዝቦችህ) ላይ የኢብራሂምን ወሬ አንብብላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
70 : 26

إِذۡ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوۡمِهِۦ مَا تَعۡبُدُونَ

70. ለአባቱና ለህዝቦቹ «ምንን ትገዛላችሁ?» ባለ ጊዜ። info
التفاسير:

external-link copy
71 : 26

قَالُواْ نَعۡبُدُ أَصۡنَامٗا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ

71. «ጣኦታትን እንገዛለን:: እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
72 : 26

قَالَ هَلۡ يَسۡمَعُونَكُمۡ إِذۡ تَدۡعُونَ

72. ኢብራሂም አለ፡- «በጠራችኋቸው ጊዜ ይሰሟችኋልን? info
التفاسير:

external-link copy
73 : 26

أَوۡ يَنفَعُونَكُمۡ أَوۡ يَضُرُّونَ

73. «ወይስ ይጠቅሟችኋልን? ወይስ ይጎዷችኋልን?» info
التفاسير:

external-link copy
74 : 26

قَالُواْ بَلۡ وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا كَذَٰلِكَ يَفۡعَلُونَ

74. «የለም! ነገር ግን አባቶቻችን ልክ እንደዚሁ ሲሰሩ አገኘን(ና እኛም እነርሱን እንከተላለን።») አሉት። info
التفاسير:

external-link copy
75 : 26

قَالَ أَفَرَءَيۡتُم مَّا كُنتُمۡ تَعۡبُدُونَ

75. እርሱም አለ: «ትገዙት የነበራችሁትን አስተዋላችሁን? info
التفاسير:

external-link copy
76 : 26

أَنتُمۡ وَءَابَآؤُكُمُ ٱلۡأَقۡدَمُونَ

76. «እናንተም የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁም እየተገዛችሁት ያለውን። info
التفاسير:

external-link copy
77 : 26

فَإِنَّهُمۡ عَدُوّٞ لِّيٓ إِلَّا رَبَّ ٱلۡعَٰلَمِينَ

77. «እነርሱም ጣኦቶቹ ለእኔ ጠላቶች ናቸው:: የዓለማት ጌታ ብቻ ሲቀር:: እርሱማ ወዳጄ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
78 : 26

ٱلَّذِي خَلَقَنِي فَهُوَ يَهۡدِينِ

78. «እርሱ ያ የፈጠረኝ ነው:: እርሱም ይመራኛል። info
التفاسير:

external-link copy
79 : 26

وَٱلَّذِي هُوَ يُطۡعِمُنِي وَيَسۡقِينِ

79. «ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝም ነው። info
التفاسير:

external-link copy
80 : 26

وَإِذَا مَرِضۡتُ فَهُوَ يَشۡفِينِ

80. «በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል። info
التفاسير:

external-link copy
81 : 26

وَٱلَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحۡيِينِ

81. «ያም የሚገድለኝ ከዚያም ህያው የሚያደርገኝ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
82 : 26

وَٱلَّذِيٓ أَطۡمَعُ أَن يَغۡفِرَ لِي خَطِيٓـَٔتِي يَوۡمَ ٱلدِّينِ

82. «ያም በፍርዱ ቀን ኃጢአቴን ሊምርልኝ የምከጅለው ነው።» (አለ) info
التفاسير:

external-link copy
83 : 26

رَبِّ هَبۡ لِي حُكۡمٗا وَأَلۡحِقۡنِي بِٱلصَّٰلِحِينَ

83. (ኢብራሂምም) «ጌታዬ ሆይ! እውቀትን ስጠኝ በደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ። info
التفاسير: