クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー

ጣሃ

external-link copy
1 : 20

طه

1. ጧሃ፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 20

مَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡقُرۡءَانَ لِتَشۡقَىٰٓ

2.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቁርኣንን አንድትቸገር ባንተ ላይ አላወረድንም:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 20

إِلَّا تَذۡكِرَةٗ لِّمَن يَخۡشَىٰ

3. አላህን ለሚፈራ ሁሉ መገሠጫ ይሆን ዘንድ እንጂ info
التفاسير:

external-link copy
4 : 20

تَنزِيلٗا مِّمَّنۡ خَلَقَ ٱلۡأَرۡضَ وَٱلسَّمَٰوَٰتِ ٱلۡعُلَى

4. ቁርኣን ምድርንና የላይኛዎቹን (የተከበሩ) ሰማያትን ከፈጠረ አምላክ ተወረደ:: info
التفاسير:

external-link copy
5 : 20

ٱلرَّحۡمَٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰ

5.እርሱ አዛኙ ጌታ (አር-ረህማን) በዐርሹ ላይ ከፍ አለ:: info
التفاسير:

external-link copy
6 : 20

لَهُۥ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا وَمَا تَحۡتَ ٱلثَّرَىٰ

6. በሰማያት፤በምድርና በመካከላቸዉም ያለው ከአፈር በታችም ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 20

وَإِن تَجۡهَرۡ بِٱلۡقَوۡلِ فَإِنَّهُۥ يَعۡلَمُ ٱلسِّرَّ وَأَخۡفَى

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በንግግር ብትጮህ (አላህ ከጩኸቱ የተብቃቃ ነው።) እርሱ ምስጢርን ከዚያም በጣም የተደበቀንም ያውቃልና:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 20

ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ لَهُ ٱلۡأَسۡمَآءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ

8.አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ለእርሱ መልካሞች የሆኑ አያሌ ስሞች አሉት:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 20

وَهَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ مُوسَىٰٓ

9.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሙሳ ወሬ (ታሪክ) መጥቶሃልን (ደርሶሃልን)? info
التفاسير:

external-link copy
10 : 20

إِذۡ رَءَا نَارٗا فَقَالَ لِأَهۡلِهِ ٱمۡكُثُوٓاْ إِنِّيٓ ءَانَسۡتُ نَارٗا لَّعَلِّيٓ ءَاتِيكُم مِّنۡهَا بِقَبَسٍ أَوۡ أَجِدُ عَلَى ٱلنَّارِ هُدٗى

10. እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ «(እዚህ) ቆዩ:: እኔ እሳትን አየሁ፤ ከእርሷ ችቦን ላመጣላችሁ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪን ላገኝ እከጅላለሁ።» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: info
التفاسير:

external-link copy
11 : 20

فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِيَ يَٰمُوسَىٰٓ

11. እናም ወደ እርሷ በመጣ ጊዜ (እንዲህ) በማለት ተጠራ: «ሙሳ ሆይ! info
التفاسير:

external-link copy
12 : 20

إِنِّيٓ أَنَا۠ رَبُّكَ فَٱخۡلَعۡ نَعۡلَيۡكَ إِنَّكَ بِٱلۡوَادِ ٱلۡمُقَدَّسِ طُوٗى

12. «እኔ ጌታህ ነኝ። ጫማዎችህን አውልቅ፤ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና። info
التفاسير: