クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - アフリカ・アカデミー

ページ番号:close

external-link copy
203 : 2

۞ وَٱذۡكُرُواْ ٱللَّهَ فِيٓ أَيَّامٖ مَّعۡدُودَٰتٖۚ فَمَن تَعَجَّلَ فِي يَوۡمَيۡنِ فَلَآ إِثۡمَ عَلَيۡهِ وَمَن تَأَخَّرَ فَلَآ إِثۡمَ عَلَيۡهِۖ لِمَنِ ٱتَّقَىٰۗ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَ وَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّكُمۡ إِلَيۡهِ تُحۡشَرُونَ

203. (ሙስሊሞች ሆይ!) በእነዚያ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ አላህን አውሱ:: በሁለት ቀናት ውስጥ ለመሄድ የተቻኮለ ሰው በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም:: የቆየም ሰው ኃጢአት የለበትም:: ይህም (ምህረት) አላህን ለፈራ ሰው ሁሉ ነው:: አላህንም ፍሩ:: እናንተ ወደ እርሱ የምትሰበሰቡ መሆናችሁንም እወቁ:: info
التفاسير:

external-link copy
204 : 2

وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يُعۡجِبُكَ قَوۡلُهُۥ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَيُشۡهِدُ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا فِي قَلۡبِهِۦ وَهُوَ أَلَدُّ ٱلۡخِصَامِ

204. ከሰዎችም መካከል እርሱ ክርክረ ብርቱ ሲሆን በቅርቢቱ ሕይወት ንግግሩ የሚያስደስትህ (የሚደንቅህ) ፤ በልቡ ውስጥ በሚያጠነጥነውም አላህን የሚያስመሰክር ሰው አለ። info
التفاسير:

external-link copy
205 : 2

وَإِذَا تَوَلَّىٰ سَعَىٰ فِي ٱلۡأَرۡضِ لِيُفۡسِدَ فِيهَا وَيُهۡلِكَ ٱلۡحَرۡثَ وَٱلنَّسۡلَۚ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلۡفَسَادَ

205. (ካንተ) በዞረ ጊዜ በውስጧ ሊያበላሽና አዝመራንና እንሰሳዎችን ሊያጠፋ በምድር ላይ ይሮጣል:: አላህም ጥፋትን አይወድም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
206 : 2

وَإِذَا قِيلَ لَهُ ٱتَّقِ ٱللَّهَ أَخَذَتۡهُ ٱلۡعِزَّةُ بِٱلۡإِثۡمِۚ فَحَسۡبُهُۥ جَهَنَّمُۖ وَلَبِئۡسَ ٱلۡمِهَادُ

206. ለእርሱ “አላህን ፍራ” በተባለም ጊዜ ትዕቢት (በኃጢአት ስራ ላይ) ይገፋፋዋል። ገሀነምም ለእሱ በቂው ናት:: እርሷም በእርግጥ የከፋች ምንጣፍ ናት:: info
التفاسير:

external-link copy
207 : 2

وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَشۡرِي نَفۡسَهُ ٱبۡتِغَآءَ مَرۡضَاتِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ رَءُوفُۢ بِٱلۡعِبَادِ

207. ከሰዎችም ውስጥ የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲል ነፍሱን የሚሸጥም ሰው አለ:: አላህም ለባሮቹ በጣም ሩህሩህ ነው። info
التفاسير:

external-link copy
208 : 2

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱدۡخُلُواْ فِي ٱلسِّلۡمِ كَآفَّةٗ وَلَا تَتَّبِعُواْ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيۡطَٰنِۚ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ

208. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም ወደ አላህ መንገድ እስልምና ጠቅልላችሁ ግቡ:: የሰይጣንን እርምጃዎችም አትከተሉ፤ እርሱም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና። info
التفاسير:

external-link copy
209 : 2

فَإِن زَلَلۡتُم مِّنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَتۡكُمُ ٱلۡبَيِّنَٰتُ فَٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

209. ግልጽ ማስረጃዎች ከመጡላችሁ በኋላ እውነትን ከመቀበል ብታፈገፍጉ አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቁ። info
التفاسير:

external-link copy
210 : 2

هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن يَأۡتِيَهُمُ ٱللَّهُ فِي ظُلَلٖ مِّنَ ٱلۡغَمَامِ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ وَقُضِيَ ٱلۡأَمۡرُۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ

210. አላህ በዳመና ጥላዎች ዉሥጥ ሆኖ እና መላዕክቱ ከያቅጣጫው ወደ እነርሱ እንዲመጡና ጉዳዩ እንዲወሰን እንጂ ሌላ ምንን ይጠባበቃሉ:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ። info
التفاسير: