クルアーンの対訳 - アムハラ語対訳 - Muhammad Sadeq

ページ番号:close

external-link copy
53 : 3

رَبَّنَآ ءَامَنَّا بِمَآ أَنزَلۡتَ وَٱتَّبَعۡنَا ٱلرَّسُولَ فَٱكۡتُبۡنَا مَعَ ٱلشَّٰهِدِينَ

«ጌታችን ሆይ! ባወረድኸው አመንን፤ መልክተኛውንም ተከተልን፤ ከመስካሪዎችም ጋር መዝግበን» (አሉ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
54 : 3

وَمَكَرُواْ وَمَكَرَ ٱللَّهُۖ وَٱللَّهُ خَيۡرُ ٱلۡمَٰكِرِينَ

(አይሁዶችም) አደሙ አላህም አደመባቸው፡፡ አላህም ከአድመኞች ሁሉ በላጭ ነው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
55 : 3

إِذۡ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّي مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ إِلَيَّ وَمُطَهِّرُكَ مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَجَاعِلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوكَ فَوۡقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِۖ ثُمَّ إِلَيَّ مَرۡجِعُكُمۡ فَأَحۡكُمُ بَيۡنَكُمۡ فِيمَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ

አላህም ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዒሳ ሆይ! እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡ ከነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ እነዚያንም የተከተሉህን እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ ከነዚያ ከካዱት በላይ አድራጊ ነኝ፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ በርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
56 : 3

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَأُعَذِّبُهُمۡ عَذَابٗا شَدِيدٗا فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَمَا لَهُم مِّن نَّٰصِرِينَ

«እነዚያማ የካዱትን ሰዎች በቅርቢቱ ዓለምና በመጨረሻይቱ ዓለም ብርቱን ቅጣት እቀጣቸዋለሁ፡፡ ለእነርሱም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡» info
التفاسير:

external-link copy
57 : 3

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَيُوَفِّيهِمۡ أُجُورَهُمۡۗ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

እነዚያም ያመኑትማ መልካም ሥራዎችንም የሠሩት ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ አላህም በዳዮችን አይወድም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
58 : 3

ذَٰلِكَ نَتۡلُوهُ عَلَيۡكَ مِنَ ٱلۡأٓيَٰتِ وَٱلذِّكۡرِ ٱلۡحَكِيمِ

ይህ ከተዓምራቶችና ጥበብን ከያዘው ተግሳጽ ሲኾን በአንተ ላይ እናነበዋለን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
59 : 3

إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٖ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለርሱ (ሰው) «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
60 : 3

ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلۡمُمۡتَرِينَ

ይህ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት ነው፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
61 : 3

فَمَنۡ حَآجَّكَ فِيهِ مِنۢ بَعۡدِ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلۡعِلۡمِ فَقُلۡ تَعَالَوۡاْ نَدۡعُ أَبۡنَآءَنَا وَأَبۡنَآءَكُمۡ وَنِسَآءَنَا وَنِسَآءَكُمۡ وَأَنفُسَنَا وَأَنفُسَكُمۡ ثُمَّ نَبۡتَهِلۡ فَنَجۡعَل لَّعۡنَتَ ٱللَّهِ عَلَى ٱلۡكَٰذِبِينَ

ዕውቀቱም ከመጣልህ በኋላ በርሱ (በዒሳ) የተከራከሩህን ሰዎች «ኑ፤ ልጆቻችንንና ልጆቻችሁን፣ ሴቶቻችንንና ሴቶቻችሁንም፣ ነፍሶቻችንንና ነፍሶቻችሁንም እንጥራ፡፡ ከዚያም አጥብቀን አላህን እንለምን፤ የአላህንም ቁጣ በውሸታሞቹ ላይ እናድርግ» በላቸው፡፡ info
التفاسير: