Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Accademia d'Africa

ጋፊር

external-link copy
1 : 40

حمٓ

1. ሓ፤ ሚይም፤ info
التفاسير:

external-link copy
2 : 40

تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡعَلِيمِ

2. የመጽሐፉን መውረድ አሸናፊው አዋቂው ከሆነው ከአላህ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 40

غَافِرِ ٱلذَّنۢبِ وَقَابِلِ ٱلتَّوۡبِ شَدِيدِ ٱلۡعِقَابِ ذِي ٱلطَّوۡلِۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ إِلَيۡهِ ٱلۡمَصِيرُ

3. ኃጢአት መሀሪና ጸጸትን ተቀባይ፤ ቅጣተ ብርቱ፤ የልግስና ባለቤት ከሆነው አላህ ብቻ የተወረደ ነው:: ከእርሱ በስተቀር (እውነተኛ) አምላክ የለም:: መመለሻዉም ወደ እርሱ ብቻ ነው:: info
التفاسير:

external-link copy
4 : 40

مَا يُجَٰدِلُ فِيٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ فَلَا يَغۡرُرۡكَ تَقَلُّبُهُمۡ فِي ٱلۡبِلَٰدِ

4. በአላህ አንቀጾች እነዚያ የካዱት ቢኾኑ እንጅ ማንም (በመዝለፍ) አይከራከርም፡፡ በያገሮችም ውስጥ መዘዋወራቸው አይሸንግልህ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
5 : 40

كَذَّبَتۡ قَبۡلَهُمۡ قَوۡمُ نُوحٖ وَٱلۡأَحۡزَابُ مِنۢ بَعۡدِهِمۡۖ وَهَمَّتۡ كُلُّ أُمَّةِۭ بِرَسُولِهِمۡ لِيَأۡخُذُوهُۖ وَجَٰدَلُواْ بِٱلۡبَٰطِلِ لِيُدۡحِضُواْ بِهِ ٱلۡحَقَّ فَأَخَذۡتُهُمۡۖ فَكَيۡفَ كَانَ عِقَابِ

5. ከእነርሱ በፊት የኑህ ህዝቦች ከኋላቸዉም አህዛቦች አስተባበሉ:: ህዝቦችም ሁሉ መልዕክተኛቸውን ሊይዙ አሰቡ፤ በውሸትም በእርሱ እውነትን ሊያጠፉበት ተከራከሩ:: ያዝኳቸዉም። ታዲያ ቅጣቴ እንዴት ነበር? info
التفاسير:

external-link copy
6 : 40

وَكَذَٰلِكَ حَقَّتۡ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَنَّهُمۡ أَصۡحَٰبُ ٱلنَّارِ

6. ልክ እንደዚሁም የጌታህ ቃል በእነዚያ በአላህ በካዱት ላይ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው ማለት ተረጋገጠች:: info
التفاسير:

external-link copy
7 : 40

ٱلَّذِينَ يَحۡمِلُونَ ٱلۡعَرۡشَ وَمَنۡ حَوۡلَهُۥ يُسَبِّحُونَ بِحَمۡدِ رَبِّهِمۡ وَيُؤۡمِنُونَ بِهِۦ وَيَسۡتَغۡفِرُونَ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْۖ رَبَّنَا وَسِعۡتَ كُلَّ شَيۡءٖ رَّحۡمَةٗ وَعِلۡمٗا فَٱغۡفِرۡ لِلَّذِينَ تَابُواْ وَٱتَّبَعُواْ سَبِيلَكَ وَقِهِمۡ عَذَابَ ٱلۡجَحِيمِ

7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፤ በእርሱም ያምናሉ። ለነዚያ ላመኑትም (እንዲህ እያሉ) ምህረትን ይለምኑላቸዋል: «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በእውቀት ከበሃል፤ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምህረት አድርግላቸው፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፤ info
التفاسير: