Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Accademia d'Africa

Numero di pagina:close

external-link copy
39 : 35

هُوَ ٱلَّذِي جَعَلَكُمۡ خَلَٰٓئِفَ فِي ٱلۡأَرۡضِۚ فَمَن كَفَرَ فَعَلَيۡهِ كُفۡرُهُۥۖ وَلَا يَزِيدُ ٱلۡكَٰفِرِينَ كُفۡرُهُمۡ عِندَ رَبِّهِمۡ إِلَّا مَقۡتٗاۖ وَلَا يَزِيدُ ٱلۡكَٰفِرِينَ كُفۡرُهُمۡ إِلَّا خَسَارٗا

39. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ በምድር ውስጥ ምትኮች ያደረጋችሁ ነው:: የካደም ክህደቱ በእርሱው ላይ ብቻ ነው:: ከሓዲያንም ክህደታቸው ከጌታቸው ዘንድ መጠላትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም:: ከሓዲያንም ክህደታቸው ክስረትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
40 : 35

قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ شُرَكَآءَكُمُ ٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُواْ مِنَ ٱلۡأَرۡضِ أَمۡ لَهُمۡ شِرۡكٞ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ أَمۡ ءَاتَيۡنَٰهُمۡ كِتَٰبٗا فَهُمۡ عَلَىٰ بَيِّنَتٖ مِّنۡهُۚ بَلۡ إِن يَعِدُ ٱلظَّٰلِمُونَ بَعۡضُهُم بَعۡضًا إِلَّا غُرُورًا

40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ተጋሪዎቻችሁ አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ? ወይስ ለእነርሱ በሰማያት ውስጥ ሽርክና አላቸውን? ወይስ ለእነርሱ መፅሀፍ ሰጠናቸውና ከእርሱ በግልፅ አስረጂ ላይ ናቸውን? አይደለም በደለኞች ከፊላቸው ከፊሉን ማታለልን እንጂ አይቀጥሩም» በላቸው:: info
التفاسير:

external-link copy
41 : 35

۞ إِنَّ ٱللَّهَ يُمۡسِكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ أَن تَزُولَاۚ وَلَئِن زَالَتَآ إِنۡ أَمۡسَكَهُمَا مِنۡ أَحَدٖ مِّنۢ بَعۡدِهِۦٓۚ إِنَّهُۥ كَانَ حَلِيمًا غَفُورٗا

41. አላህ ሰማያትንና ምድርን እንዳይወገዱ ይይዛቸዋል:: ቢወገዱም ከእርሱ ሌላ አንድም የሚይዛቸው የለም:: እነሆ እርሱ ታጋሽና መሃሪ ነውና:: info
التفاسير:

external-link copy
42 : 35

وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَئِن جَآءَهُمۡ نَذِيرٞ لَّيَكُونُنَّ أَهۡدَىٰ مِنۡ إِحۡدَى ٱلۡأُمَمِۖ فَلَمَّا جَآءَهُمۡ نَذِيرٞ مَّا زَادَهُمۡ إِلَّا نُفُورًا

42. አስፈራሪም ቢመጣላቸው ከህዝቦች ሁሉ ከአንደኛዋ ይበልጥ የተመሩ ሊሆኑ የመሃላቸውን ዲካ አድርሰው በአላህ ማሉ:: አስፈራሪም በመጣላቸው ጊዜ መበርገግን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም:: info
التفاسير:

external-link copy
43 : 35

ٱسۡتِكۡبَارٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَكۡرَ ٱلسَّيِّيِٕۚ وَلَا يَحِيقُ ٱلۡمَكۡرُ ٱلسَّيِّئُ إِلَّا بِأَهۡلِهِۦۚ فَهَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّا سُنَّتَ ٱلۡأَوَّلِينَۚ فَلَن تَجِدَ لِسُنَّتِ ٱللَّهِ تَبۡدِيلٗاۖ وَلَن تَجِدَ لِسُنَّتِ ٱللَّهِ تَحۡوِيلًا

43. በምድር ላይ ኩራትንና በክፉ ተንኮል መዶለትንም እንጂ አልጨመረላቸዉም:: ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም:: የቀድሞዎቹን ደንብ እንጂ ይጠብቃሉን? በመሆኑም ለአላህ ደንብ መለወጥን አታገኝም፤ ለአላህ ደንብም መዛወርን (መቀየር) አታገኝም። info
التفاسير:

external-link copy
44 : 35

أَوَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ وَكَانُوٓاْ أَشَدَّ مِنۡهُمۡ قُوَّةٗۚ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُعۡجِزَهُۥ مِن شَيۡءٖ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِي ٱلۡأَرۡضِۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَلِيمٗا قَدِيرٗا

44. በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ አይመለከቱምን? ከእነርሱም በኃይል የበረቱ ነበሩ:: አላህም በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም ነገር የሚያቅተው አይደለም:: እርሱ ሁሉን አዋቂና በሁሉ ላይ ቻይ ነውና:: info
التفاسير: