Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Accademia d'Africa

አል አንቢያ

external-link copy
1 : 21

ٱقۡتَرَبَ لِلنَّاسِ حِسَابُهُمۡ وَهُمۡ فِي غَفۡلَةٖ مُّعۡرِضُونَ

1. ለሰዎች እነርሱ በዝንጋታ ውስጥ መሰናዳትን የተዉ ሆነው ሳሉ ምርመራቸው ቀረበ:: info
التفاسير:

external-link copy
2 : 21

مَا يَأۡتِيهِم مِّن ذِكۡرٖ مِّن رَّبِّهِم مُّحۡدَثٍ إِلَّا ٱسۡتَمَعُوهُ وَهُمۡ يَلۡعَبُونَ

2. ከጌታቸው አዲስ የተወረደ ቁርኣን አይመጣላቸዉም:: እነርሱ የሚያላግጡበት ሆነው ፤ የሚያዳምጡት ቢሆኑ እንጂ:: info
التفاسير:

external-link copy
3 : 21

لَاهِيَةٗ قُلُوبُهُمۡۗ وَأَسَرُّواْ ٱلنَّجۡوَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُواْ هَلۡ هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡۖ أَفَتَأۡتُونَ ٱلسِّحۡرَ وَأَنتُمۡ تُبۡصِرُونَ

3.ልቦቻቸው ዝንጉዎች ሆነው። እነዚያም የበደሉት ሰዎች መንሾካሾክን ደበቁ:: «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጂ ሌላ ነውን? እናንተም የምታዩ ስትሆኑ ድግምትን ለመቀበል ትመጣላችሁን?» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
4 : 21

قَالَ رَبِّي يَعۡلَمُ ٱلۡقَوۡلَ فِي ٱلسَّمَآءِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ

4. (ሙሐመድም) «ጌታዬ ቃልን ሁሉ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለ ሲሆን ያውቃል:: እርሱም ሰሚና አዋቂ ነው።» አለ። info
التفاسير:

external-link copy
5 : 21

بَلۡ قَالُوٓاْ أَضۡغَٰثُ أَحۡلَٰمِۭ بَلِ ٱفۡتَرَىٰهُ بَلۡ هُوَ شَاعِرٞ فَلۡيَأۡتِنَا بِـَٔايَةٖ كَمَآ أُرۡسِلَ ٱلۡأَوَّلُونَ

5. በእውነቱ «ቁርኣኑ የሕልሞች ቅዠቶች ነው። ይልቁንም ቀጠፈው፤ እንዲያዉም እርሱ ቅኔን ገጣሚ ነው:: የቀድሞዎቹም እንደ ተላኩ ሁሉ መልዕክተኛ ከሆነ በተዓምር ይምጣብን።» አሉ። info
التفاسير:

external-link copy
6 : 21

مَآ ءَامَنَتۡ قَبۡلَهُم مِّن قَرۡيَةٍ أَهۡلَكۡنَٰهَآۖ أَفَهُمۡ يُؤۡمِنُونَ

6. ከእነርሱ በፊት ያጠፋናት ከተማ አላመነችም:: ታዲያ እነርሱ ያምናሉን? info
التفاسير:

external-link copy
7 : 21

وَمَآ أَرۡسَلۡنَا قَبۡلَكَ إِلَّا رِجَالٗا نُّوحِيٓ إِلَيۡهِمۡۖ فَسۡـَٔلُوٓاْ أَهۡلَ ٱلذِّكۡرِ إِن كُنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ

7.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከአንተም በፊት ወደእነሱ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፡፡ የማታውቁ ከሆናችሁ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ:: info
التفاسير:

external-link copy
8 : 21

وَمَا جَعَلۡنَٰهُمۡ جَسَدٗا لَّا يَأۡكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَمَا كَانُواْ خَٰلِدِينَ

8.ምግብን የማይበላ አካልም አላደረግናቸዉም:: ዘውታሪዎችም አልነበሩም:: info
التفاسير:

external-link copy
9 : 21

ثُمَّ صَدَقۡنَٰهُمُ ٱلۡوَعۡدَ فَأَنجَيۡنَٰهُمۡ وَمَن نَّشَآءُ وَأَهۡلَكۡنَا ٱلۡمُسۡرِفِينَ

9.ከዚያ ቀጠሮን ሞላንላቸውና እነርሱንና የምንሻውን ሰው አዳንናቸዉም:: ወሰን አላፊዎችንም አጠፋን:: info
التفاسير:

external-link copy
10 : 21

لَقَدۡ أَنزَلۡنَآ إِلَيۡكُمۡ كِتَٰبٗا فِيهِ ذِكۡرُكُمۡۚ أَفَلَا تَعۡقِلُونَ

10. (ሙስሊሞች ሆይ!) ክብራችሁ በውስጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደእናንተ በእርግጥ አወረድን፡፡ አታውቁምን? info
التفاسير: