Traduzione dei Significati del Sacro Corano - Traduzione Amarica - Muhammed Sadeq

Numero di pagina:close

external-link copy
87 : 12

يَٰبَنِيَّ ٱذۡهَبُواْ فَتَحَسَّسُواْ مِن يُوسُفَ وَأَخِيهِ وَلَا تَاْيۡـَٔسُواْ مِن رَّوۡحِ ٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ لَا يَاْيۡـَٔسُ مِن رَّوۡحِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلۡقَوۡمُ ٱلۡكَٰفِرُونَ

«ልጆቼ ሆይ! ሂዱ፤ ከዩሱፍና ከወንድሙም (ወሬ) ተመራመሩ፡፡ ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ እነሆ ከአላህ እዝነት ከሓዲዎች ሕዝቦች እንጂ ተስፋ አይቆርጥም» (አለ)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
88 : 12

فَلَمَّا دَخَلُواْ عَلَيۡهِ قَالُواْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡعَزِيزُ مَسَّنَا وَأَهۡلَنَا ٱلضُّرُّ وَجِئۡنَا بِبِضَٰعَةٖ مُّزۡجَىٰةٖ فَأَوۡفِ لَنَا ٱلۡكَيۡلَ وَتَصَدَّقۡ عَلَيۡنَآۖ إِنَّ ٱللَّهَ يَجۡزِي ٱلۡمُتَصَدِّقِينَ

በእርሱም ላይ በገቡ ጊዜ «አንተ የተከበርከው ሆይ! እኛንም ቤተሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን፡፡ ርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል፡፡ ስፍርንም ለኛ ሙላልን፡፡ በኛም ላይ መጽውት አላህ መጽዋቾችን ይመነዳልና» አሉት፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
89 : 12

قَالَ هَلۡ عَلِمۡتُم مَّا فَعَلۡتُم بِيُوسُفَ وَأَخِيهِ إِذۡ أَنتُمۡ جَٰهِلُونَ

«እናንተ የማታውቁ በነበራችሁ ጊዜ በዩሱፍና በወንድሙ ላይ የሰራችሁትን ግፍ ዐወቃችሁን» አላቸው፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
90 : 12

قَالُوٓاْ أَءِنَّكَ لَأَنتَ يُوسُفُۖ قَالَ أَنَا۠ يُوسُفُ وَهَٰذَآ أَخِيۖ قَدۡ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَيۡنَآۖ إِنَّهُۥ مَن يَتَّقِ وَيَصۡبِرۡ فَإِنَّ ٱللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجۡرَ ٱلۡمُحۡسِنِينَ

«አንተ በእርግጥ አንተ ዩሱፍ ነህን» አሉት፡፡ «እኔ ዩሱፍ ነኝ፡፡ ይህም ወንድሜ ነው፡፡ አላህ በኛ ላይ በእርግጥ ለገሰልን፡፡ እነሆ! የሚጠነቀቅና የሚታገስ ሰው (አላህ ይክሰዋል)፡፡ አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
91 : 12

قَالُواْ تَٱللَّهِ لَقَدۡ ءَاثَرَكَ ٱللَّهُ عَلَيۡنَا وَإِن كُنَّا لَخَٰطِـِٔينَ

«በአላህ እንምላለን፡፡ አላህ በኛ ላይ በእርግጥ አበለጠህ፡፡ እኛም በእርግጥ አጥፊዎች ነበርን» አሉ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
92 : 12

قَالَ لَا تَثۡرِيبَ عَلَيۡكُمُ ٱلۡيَوۡمَۖ يَغۡفِرُ ٱللَّهُ لَكُمۡۖ وَهُوَ أَرۡحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ

«ዛሬ በናንተ ላይ ወቀሳ የለባችሁም፡፡ አላህ ለእናንተ ይምራል፡፡ እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው» አላቸው፡፤ info
التفاسير:

external-link copy
93 : 12

ٱذۡهَبُواْ بِقَمِيصِي هَٰذَا فَأَلۡقُوهُ عَلَىٰ وَجۡهِ أَبِي يَأۡتِ بَصِيرٗا وَأۡتُونِي بِأَهۡلِكُمۡ أَجۡمَعِينَ

«ይህንን ቀሚሴን ይዛችሁ ሂዱ፡፡ በአባቴ ፊት ላይ ጣሉት የሚያይ ሆኖ ይመጣልና፡፡ ቤተሰቦቻችሁንም ሰብስባችሁ አምጡልኝ» (አላቸው)፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
94 : 12

وَلَمَّا فَصَلَتِ ٱلۡعِيرُ قَالَ أَبُوهُمۡ إِنِّي لَأَجِدُ رِيحَ يُوسُفَۖ لَوۡلَآ أَن تُفَنِّدُونِ

ግመል ጫኞቹም (ምስርን) በተለዩ ጊዜ አባታቸው «እኔ የዩሱፍን ሽታ በእርግጥ አገኛለሁ፡፡ ባታቄሉኝ ኖሮ (ታምኑኝ ነበር)» አለ፡፡ info
التفاسير:

external-link copy
95 : 12

قَالُواْ تَٱللَّهِ إِنَّكَ لَفِي ضَلَٰلِكَ ٱلۡقَدِيمِ

«በአላህ እንምላለን፡፡ አንተ በእርግጥ በቀድሞው ስህተትህ ውስጥ ነህ» አሉት፡፡ info
التفاسير: